Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ከብዙ መከራና ስቃይ በኃላ "ቆም ማለታችን አይቀርም!" ዛሬ "ቆም" ብንል ግን ቀጣዩ ሊደርስ ያሰበውን ጥፋት ማዳን እንችላለን ነው፣"

Post by sarcasm » 17 Jul 2021, 10:14

ክብሮም ባይቶና
(ለአንባቢዎቼ)
Kibrom Zebib Sibhatleab የሰላማዊ ፓለቲካ ታጋይ ነው። በእኛ ዕድሜ ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለ ዴሞክራሲ፣ ስለ ፌደራሊዝም፣ ስለ የህዝቦች መከባበርና ፍቅር የሚታገል የባይቶና ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ዘርፍ ሃላፊ በእስር ላይ ይገኛል። በእርግጥ የት ቦታ እንደታሰረ ማወቅ አልተቻለም። ፍርድቤት ስለ መቅረቡም አልተነገረም።
~~~~

Note: ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለ ዴሞክራስያዊና ሰብአዊ መብት የተማራችሁ ሁሉ፤ በሰብአዊና ዴሞክራስያዊ መብቶች ዙርያ የምትሰሩ ሁሉ፣ በፓለቲካ ድርጅት ተደራጅታችሁ ሆነ ሳትደራጁ ስለ መብት ስለ ዴሞክራሲ፣ ስለ ሰላማዊ ትግል ጊዚያችሁ ጉልበታችሁ የምታበረክቱ ሁሉ... የሃይማኖት ሰዎችና አማኞች፣ የስነፅሑፍ ሰዎች፣ የሚድያ ሰዎችና ጋዜጠኞች ሁሉ ዛሬ ስለ አንድ ንፁህ ሰላማዊ የፓለቲካ ታጋይ ስለ ክብሮም ዘቢብ መታሰርን ጠይቁ ፃፉ። መንግስትን ጠይቁ፣ "ግፍን ፍራ ተው!" በሉ፤
ከሰሞኑ በሺዎች ተጋሩ የንግድ ቤታቸው ታሽጎባቸዋል፣ በሺዎች በመኪኖች እየተጫኑ ተወስዷል... ስለሁሉም justice እንጠይቅ...


የንግድቤት መዝጋት ጉዳቱ የነጋዴው ብቻ አይደለም፣ ሰራተኞቹም ስራ አጥ ይሆናሉ፣ በዙርያቸው ያለውም ሁሉ ተጎጂ ነው፣ የአከራይ ገቢም እንዲሁ ይቀንሳል ወይም ይጠፋል፣ ሌላ ጭቅጭቅ ይፈጠራል፣ የመንግስት የግብር ገቢውም ይወርዳል፣ ለተጨማሪ የቢሮክራሲ ጉዳዮችም ይዳረጋል፣ የኑሮ ውድነቱም ከመሻሻል ይልቅ ይባባሳል ጉዳቱም ለሁሉም ዜጋ ይሆናል፣

ባጭሩ ጉዳቱ አንድ ቦታ ላይ የሚቆም ጉዳት አይደለም... ልባም መንግስት:- ስራ ፈጣሪ ነጋዴዎችን እያበረታታ፣ ስራ ዕድል እየፈጠረ ዳጎስ ያለ ግብር ይሰበስባል እንጂ በአንድ ሳምት ውስጥ ባልተጠና መንገድ፣ የችኮላ ውሳኔ በመወሰን ዜጋውና ሃገሩ ለተደራራቢ ጉዳት አይዳርግም። ፍራቻና ጥርጣሬ ካለም'ኮ በማህበር እያደራጁ ማሰራትና መከታተል ይቻላል። እና ይታሰብበት።

Anyways, ለአንባብያኖቼ የምለው: ያለው መካረሩ፣ መጠላላቱ፣ ጣት መቀሳሰሩ ወዴት እንዳደረሰን አይተናል... ከዚህ በላይ እንዲቀጥል አናድርግ፣ I know ከብዙ መከራና ስቃይ በኃላ "ቆም ማለታችን አይቀርም!" ዛሬ "ቆም" ብንል ግን ቀጣዩ ሊደርስ ያሰበውን ጥፋት ማዳን እንችላለን ነው፣ ነው።

እናንተ ስለ ንፁሃንና ስለ ሰላማዉያን ተጋሩ ፍትህ ስትጠይቁ ሌላውም በየቤቱ ስላለው አጥፊ መጠየቅ እንጀምራል፣ ሆኖም ግን በቀጥታ በማጥቃትም ይሁን በዝምታ የዚህ ግፍ ተባባሪ ስትሆኑ ነገሩ ይከራል፣ የከረረም ይበጠሳል እንጂ ሊድን አይችልም... አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳ፣ ዳሩ ሲረበሽ መሃሉ ዳር ይሆናል፣ ሰው ሰውን የሚረዳው አንድም አዝኖለት ነው ሌላም ግን ነግ በኔ እያለ ነውና እንተባበር... መተባበርን ከዚሁ እንጀምር፣ አዳዲስ መሪዎች እንፍጠር☝
ፍትህ በግፍ ታስረው ላሉ ሁሉም ዜጎችና ንግድ ቤቶች፤ ፍትህ ለውድ ወንድማችን ክብሩ 💕
ሠላም

https://www.facebook.com/thomas.hailu.5 ... 5411330870

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "ከብዙ መከራና ስቃይ በኃላ "ቆም ማለታችን አይቀርም!" ዛሬ "ቆም" ብንል ግን ቀጣዩ ሊደርስ ያሰበውን ጥፋት ማዳን እንችላለን ነው፣"

Post by sarcasm » 27 Jul 2021, 09:58

ኤሊቱ ቢነጋገር የማይፈታ ከባድ ችግር ኖሮ አይደለም

ከብዙ ሞት በኋላ መደራደራቸው አይቀርም

መደራደራችን ላይቀር ህዝቡን አናፋጀው የሚል አንድ ብርቱ ነው የጠፋው




Please wait, video is loading...

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "ከብዙ መከራና ስቃይ በኃላ "ቆም ማለታችን አይቀርም!" ዛሬ "ቆም" ብንል ግን ቀጣዩ ሊደርስ ያሰበውን ጥፋት ማዳን እንችላለን ነው፣"

Post by sarcasm » 28 Jul 2021, 18:55

በሁለቱም ወገን ያለው ትርምስና ድንፋታ በድርድር እና በፖለቲከኞቹ መጨባበጥ እንደሚደመደም ለመናገር ነብይነት አይጠይቅም። (ያው አገራችን በሰላም ከቀጠለች ነው።) አሁን በሰሞንኛ የጀብደኝነት ስሜት ለመዋጋት የተነሳው.... ያንንም የሚደግፈው ብዙ ነውና ለመስማት ቢያንቅም፣ ሀቁ ይኼ ነው። ይልቅ in the mean time ለምን አበበ በለውን አዋጥተን ወደ ጦር ግንባር አንልከውም? 🤔

Please wait, video is loading...

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "ከብዙ መከራና ስቃይ በኃላ "ቆም ማለታችን አይቀርም!" ዛሬ "ቆም" ብንል ግን ቀጣዩ ሊደርስ ያሰበውን ጥፋት ማዳን እንችላለን ነው፣"

Post by sarcasm » 10 Aug 2021, 18:22

የእርስበርስ ጦርነት መጨረሻም ሆነ አሸናፊ የሌለው ትግል ነው። ትርፉ ሞት ፣ ለቅሶውም የፈረቃ ነው። ቋሚ ደስታ የሚያገኝ ሃይል አይኖርም። ከዚህ ወደባሰ እልቂትና ረሃብ ሳንገባ ጉዳዩ በድርድር የሚፈታበት መንገድ ይፈለግ። አላህ ንፁሃንን ይጠብቅልን። ሰላምችንን ይመልስልን ❤

ዮሐንስ አድማሱ
መንግስት ቢደራደር ወታደሩ ነዉ መፈንቅለ መንግስት የሚያደርግበት ያንን ደሞ ህዝብም ይደግፈዋል ።


Author
ሙስተጃብ ነኝ
ዮሐንስ አድማሱ አንተ ደግሞ ምን ያለህው ደነዝ ነህ ? ወታደሩና ህዝቡ እንዲሁ መተላለቁን እንደ አንተ የሚፈልጉ ደንቆሮ አረካቸው እንዴ? የአንዳንዶቻችሁ የጦርነት ፍቅር የሰው ደም የምትጠጡ ነው የምትመስሉት 😕
Please wait, video is loading...


Post Reply