Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 33275
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

JUST IN: አሸባሪው የህወሀት ቡድን የሽብር አድማሱን ወደ አፋር በማስፋት የአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 17 Jul 2021, 09:26

Natnael Mekonnen
tSponia1shodred ·
አሸባሪው የህወሀት ቡድን የሽብር አድማሱን ወደ አፋር በማስፋት የአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል።

#Ethiopia : ይህ እኩይ ቡድን በዳር ድንበር አስከባሪው በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው ጀግናው የአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ በፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል የከፈተውን ጦርነት መንግስት ከህዝባችን ጋር በመተባበር ይመክታል ሲል የአፋር ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፋት ቤት ማሳወቁን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

ሰላማዊ ክልላችንን ለማተራመስ ህወሀት የለኮሰው ጦርነት በአጭሩ እንዲገታ አርብቶ አደር ህዝባችንም አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት ማድረግ የሚጠበቅ ሲሆን አካባቢውንም በንቃት ሊጠብቅ ይገባል።

ሚሊሺያችንና አጠቃላይ የፀጥታ ሀይላችን ይህን በህዝባችን ላይ የተሠነዘረውን ጥቃት የመከላከል ስራ በቁርጠኝነት የሚተገብር ይሆናል።

መላው የኢትዮጵያ ህዝብም እንደ አበደ ውሻ እዚያና እዚህ ለመንከስ የእብደት ስራ እየሰራ ያለውን ይህን እኩይ ቡድን በፍጥነት ግብአተ መሬቱ እንዲፈፀም እንደወትሮው ሁሉ እጅ ለእጅ በመያያዝ በጋራ በመታገል እስትንፋሱ እንዲቋረጥ ማድረግ ይጠበቅብናል ሲል ፅህፈት ቤቱ ማሳወቁን ሰምተናል።