Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በህግ ማሰከበር ስም ከሌላ ብሄር የተውጣጡትን የሰራዊት አባላት፤ በሕገመንግስት የትግራይ ተብሎ የተደነገገው መሬት በጦርነት የአማራ ለማድረግ ሊሞቱ ነው? ዸረጀ ገረፋ ቱሉ

Post by sarcasm » 06 Jul 2021, 19:57

ህገ መንግስታዊ ያልሆኑ የተሳሳቱ አመለካካቶች !!

1 በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አባሳደር ታዬ ሰሞኑን በመድረኩ ላይ ያቀረቡት ንግግርም ሆነ ለጋዘጠኞች የሰጡት ምላሽ በአብዛኛው ጥሩ የሚባል ነው። በአንድ ነገር ላይ ግን ከህግም ሆነ ከፖለቲካ እንዲሁም ከሞራል አንፃር እጅግ ተሳስተዋል አምባሳደር ታዬም ሆኑ ሌላ ማንኛውም የኢትዮጵያ ባለስልጣን በኢትዮጵያ ህገመንግስት ውስጥ የተካተቱ የተወሰኑ አንቀፆችን ላይቀበሉ ይችላሉ።ነገር ግን እነዚህ አንቀፆች ስራ ላይ እስካሉ ድረስ እና ማንኛውም ባለስልጣን ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ በዓለምም ሆነ በየትኛውም መድረክ ያንን ተቀርኖ የግሉን ወይም የቡድኑን ፋላጎት አንፀባርቆ ማቅረብ ስህተት ነው።
ከዚህ አንፃር በአማራ ክልል እና በትግራይ መካከል አወዛጋቢ ሆነው የቀረቡት አከባቢዎች የፌደራል መንግስት የአማራ መሆናቸውን ያምናል ማለት በፍፁም ስህተት ነው። የፌደራል መንግስትም እንደዚያ የሚያምን ከሆነ እጅግ የተሳሳተ ነው።

በኢትዮጵያ ህገመንግስት መሰረት እነዚህ አከባቢዎች በትግራይ ክልል ስር መሆናቸውን እያወቅን እና ህገመንግስቱን ተከትለው ወደ አማራ ክልል አለመመለሳቸው እየታወቀ ወይም ህገመንግስቱ እስካልተቀየረ ድረስ የፌደራል መንግስቱ ያንን የሚፃረር አቋም መያዝም ሆነ ማራመድ በፍፁ አግባብነት የለውም።

የፌደራል መንግስት ህገመንግስቱ ላይ የተቀመጡትን አንቀፆች ቢያንስ በመሪህ ደረጃ ካላከበረ እጅግ አደገኛ ነው።ባለፈው ዓመትም ምርጫን ለማረዘም ህገመንግስቱ ክፍተት አለበት ተብሎ ያ ሁሉ የህገመንግስት ትርጉም ጋጋታ አያስፈልገውም ነበር። በአጭሩ የመንግስት ባለስልጣናት አጣብቂኝ ውስጥ ስለገቡ ብቻ ህገመንግስቱን ጥሰው እንደፈለጉት መሬት ቆርሰው ለዘመዶቻቸው መስጠት ከጀመሩ ነገ ተነገወዲያ መውጫ መንገድ የለንም። ሌላ ቀውስ መፈጠሩ አይቀርም።

እሄ ከህግ አንፃር ነው። ከፖለቲካ አንፃር ካየነው ደግሞ ሌላ መዘዝ አለው። ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጣው የኢትዮጵያ ሰራዊት አሁን ሰፍሮ ያለው በነዚህ አከባቢዎች ነው። እሄ መብቱ ነው። ነገ ተነገወዲያ በዚህ አከባቢ የሰፈረው የኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ በህወሃት እሄ መሬቴ ነው ተብሎ ጥቃት ቢሰነዘርበት ሰራዊቱ የሚዋጋው ምን ብሎ ነው? የአማራን መሬት ከህወሃት ለመከላካል ነው ወይስ ህግን ለማስከበር ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ቤሄርተኝነት ጣራ በነካበት በዚህ ሰዓት ሰራዊቱ ያ አከባቢ በህገመንግስቱ መሰረት ምን ማለት እንደሆነ በግልፅ እያወቀ ነገ ውጊያ ቢካሄድ እየተዋጋህ ያለሀው የአማራን ሪስት ለማስጠበቅ ነው እያተባለ የአምባሳደሩን ንግግር በመጥቀስ በብሄርተኞች ፕሮፓጋንዳ ቢሰራ መንግስት ከሌላ ብሄር የተውጣጡትን የሰራዊት አባላት በምን መልኩ ሊያሳምን ነው ?

ስለዚህ የመንግስት ባለስልጣናት የሚያደርጉአቸው ንግግሮች አንድን ክፍተት ለመሙላት እጅግ ብዙ ክፍተት መፍጠር እንዳሌላባቸው መጠንቀቅ አለባቸው።

እሳቸው ያደረጉት ንግግሮች የአማራ ክልል ተወላጆችን እንዲሚያበረታታ እና ድጋፍ እንደሚያስገኝ ቢታወቅም በህግ ማሰከበር ስም ያሰማራነው ሰራዊት የሚዋጋለትን ዓላማ እየከለከሉት እና ለሽንፈት እያዘጋጁት መሆኑን ማወቅ አለባቸው።

https://www.facebook.com/derejegerefa.t ... 2318509158

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: በህግ ማሰከበር ስም ከሌላ ብሄር የተውጣጡትን የሰራዊት አባላት፤ በሕገመንግስት የትግራይ ተብሎ የተደነገገው መሬት በጦርነት የአማራ ለማድረግ ሊሞቱ ነው? ዸረጀ ገረፋ ቱሉ

Post by sarcasm » 06 Jul 2021, 20:57

"Changing internal borders of Ethiopia using the war as excuse is wrong" Ethiopian Defense Minister in agreement with U.S and international community position. Why is the Ethiopian Ambassador to UN not following the Defense Ministry and ENDF position? Person wishes and positions should not be confused with stated state positions.

The Defense Ministry and ENDF position on internal borders of Ethiopia is crystal clear! If any member of ENDF wants to die fighting against the publicly declared position of ENDF, they are on their own!

fast forward to 2:26

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: በህግ ማሰከበር ስም ከሌላ ብሄር የተውጣጡትን የሰራዊት አባላት፤ በሕገመንግስት የትግራይ ተብሎ የተደነገገው መሬት በጦርነት የአማራ ለማድረግ ሊሞቱ ነው? ዸረጀ ገረፋ ቱሉ

Post by sarcasm » 15 Jan 2022, 17:26

sarcasm wrote:
06 Jul 2021, 19:57
ህገ መንግስታዊ ያልሆኑ የተሳሳቱ አመለካካቶች !!

1 በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አባሳደር ታዬ ሰሞኑን በመድረኩ ላይ ያቀረቡት ንግግርም ሆነ ለጋዘጠኞች የሰጡት ምላሽ በአብዛኛው ጥሩ የሚባል ነው። በአንድ ነገር ላይ ግን ከህግም ሆነ ከፖለቲካ እንዲሁም ከሞራል አንፃር እጅግ ተሳስተዋል አምባሳደር ታዬም ሆኑ ሌላ ማንኛውም የኢትዮጵያ ባለስልጣን በኢትዮጵያ ህገመንግስት ውስጥ የተካተቱ የተወሰኑ አንቀፆችን ላይቀበሉ ይችላሉ።ነገር ግን እነዚህ አንቀፆች ስራ ላይ እስካሉ ድረስ እና ማንኛውም ባለስልጣን ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ በዓለምም ሆነ በየትኛውም መድረክ ያንን ተቀርኖ የግሉን ወይም የቡድኑን ፋላጎት አንፀባርቆ ማቅረብ ስህተት ነው።
ከዚህ አንፃር በአማራ ክልል እና በትግራይ መካከል አወዛጋቢ ሆነው የቀረቡት አከባቢዎች የፌደራል መንግስት የአማራ መሆናቸውን ያምናል ማለት በፍፁም ስህተት ነው። የፌደራል መንግስትም እንደዚያ የሚያምን ከሆነ እጅግ የተሳሳተ ነው።

https://www.facebook.com/derejegerefa.t ... 2318509158

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: በህግ ማሰከበር ስም ከሌላ ብሄር የተውጣጡትን የሰራዊት አባላት፤ በሕገመንግስት የትግራይ ተብሎ የተደነገገው መሬት በጦርነት የአማራ ለማድረግ ሊሞቱ ነው? ዸረጀ ገረፋ ቱሉ

Post by sarcasm » 28 Aug 2022, 14:22

ይሄ ጦርነት ኦሮምያን አይመለከትም። የኦሮሞ ሕዝብ ኣይሳተፍበትም። እኛ ልማት ላይ ነን። - በሽመልስ አብዲሳ የሚመራው የብዙሃኑ ኦሮሞ ብልጽግና ቡድን

Post Reply