Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30844
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ሰላም፤ በምርጫው ብቸኛ የሕዝብ ጥያቄ !! ተሸናፊዎች፤ ኦነግ፣ ትህነግ፣ አሜሪካ!

Post by Horus » 22 Jun 2021, 23:46

የ2013 ምርጫ እኛንም የውጭ አለምን አስገርሟል፤ ለምን? ሰላማዊ ስለነበረ!

ምርጫው በአንደኛ ደረጃ ፍንትው አድርጎ ያሳየው ነገር ምንድን ነው?

ከዚህ በኋላ ሁሉም ነገር ፍትሃዊ፣ ሁሉም ነገር ርትአዊ፣ ሁሉም አልጋ ባልጋ ይሆናል፣ ነገ በየቀበሌው፣ ወረዳው፣ በክልሉ ነጻነት እና ፍትሃዊነት ይሰፍናል ማለት አይደለም።

ነገር ግን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከሰሜን እስከ ሱማሌ በነቂስ እየጠየቀ ያለው ሰላምና ደህንነት፣ ከአመጻ ነጻ የሆነ ህይወት መንኖርን ነው። ሰላም፣ ሰላም፣ ሰላም!!!

ስለዚህ ይህ የሕዝብ ጥያቄ ማዕበል በማን ላይ ነው ያነጣጠረው?

አንደኛ፣ ሰላም የሚያሰጠብቅ መንግስት እንዲኖር መላ ኢትዮጵያዊያን ጠይቀዋል ! ከዚህ በኋላ አቢይ በትግሬ፣ በኦሮሞና በቤኒ ሻንጉል የህዝብና ያገር ሰላም የነሱ ያመጽ አሸባሪዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ካልወሰደ ሕዝባዊ ጎርፉ ሁሉንም ጠራርጎ መወሰዱ አይቀሬ ነው።

ሁለተኛ፣ የዚህ መራጭ ሕዝብ የሰላም ጥያቄ ጎርፍ በቀጥታ የቀረበው በዎያኔ፣ ኦነግ፣ ሌሎች አሸባሪዎች ላይ ነው ። የጎሳ ፖለቲካና የጎሳ አመጽ መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቋቅ በቃን አንገሸገሸን ብሏል ። አሁን አቢይ በነዚህ ካንሰሮች ላይ መሽኮርመም የለበትም፣ በቃ መሸ !!

ሶስት፣ ይህ ግዙፍ የሕዝብ ማዕበላዊ መልዕክት የተላከው ላሜሪካ፣ ላውሮፓ ህብረትና ግብጽ ነው ። ሕዝቡ ምን አለ? ኢትዮጵያን አትንኩ ! እጃችሁን ከኢትዮጵያ አንሱ ብሏል፣ መልክቱ ከገባቸው ማለት ነው ።

ይህ ነው የዚህ ምርጫ ትክክለኛ ትርጉምና መልዕክት!!

የዚህ ምርጫ ተልዕኮ መንግስት መቀየሪያ አልነበረም! ስንት ሰው ይህን ጉዳይ እንደ ገባው አላቅም !!


Last edited by Horus on 23 Jun 2021, 00:08, edited 3 times in total.




Post Reply