Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በመስከረም የተለያዩ ፓርቲዎች ቅይጥ ፓርላማ ይሰየማል! ከዚያም ወደ ኢጎሳዊ ፌዴሬሽንና ፕሬዚዳንታዊ ሲስተም ያ5 አመት ጉዞ እንጀምራለን!!

Post by Horus » 19 Jun 2021, 18:23


እኔ በነገው ምርጫ ስንት ብልጽግና ያልሆኑ የፓርላማ ወኪሎች እንደ ሚያሸንፉ በውል አላቅም አንድ መቶ የሚደርሱ ከሆነ ትልቅ ሚዛን ደፊ ቁጥር ይሆናል ። አስር ወይም ሃያ ያንሳል ፣ ከ547 ወምበር ማለት ነው።

ግን እስከ አንድ መቶ የዜጋ ፖለቲካ አራማጆች ከተወከሉ ቀጥሎ የምናየው የቅጭ ጉዳይ፣ የፍርድና፣ የትምህርት ሚኒስቴር መቀየጥና መጠንከር ነው ።

ቀጥሎ የሚነሳው ግዙፉ የሕገ መንግስት ማሻሻያ አገር አቀፍ ውይይት፣ ክርክር እና ከዚያ ጋር አብረው የሚመጡት የኢርትዮጵያ ፌዴራል ጠ/ግዛቶች አከላለል፣ እና በዚያ መሰረት የሚመጣው አዲስ አገር አቀፍ ያልተማከለ ፖለቲካዊ እስትራክቸር ነው

በመጨረሻም የሚቀጥለው ፕሬዚዳንታዊና ፓርላማዊ ምርጫ ህግጋት ይሆናል ።

የነገው ምርጫ ግን ምዕራብና ያረቡን አለም የሚያስደንቅ እና ኢትዮጵያን የሚያስከበር ፣ ሕዝባችንን የሚያስኮራ እንደ ሚሆን አልጠራጥርም !


ለምን ቢባል? ምልክቶች እያየሁ ስለሆነ ነው !!





Post Reply