Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12530
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

ናትናኤል መኮንን(ሰርዲኑ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስም ማጥፋት ወንጀል ሊከሰስ ነው

Post by Thomas H » 19 Jun 2021, 14:47

Commercial Bank of Ethiopia
8h ·
በማህበራዊ ሚዲያ የተላለፈ ሀሰተኛ መረጃን ስለማሳወቅ
=========
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦሌ ተርሚናል ቅርንጫፍ ከሚሰጠው የውጭ ምንዛሪ እና የኢሚግሬሽን ቪዛ ክፍያ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ፌስቡክ ላይ ሀሰተኛ መረጃ ተለቋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ ሀሰተኛ መረጃዎችን በተመለከተ ባንካችን በደንበኞቻችን ዘላቂ እምነት ከመገንባቱ አንፃር እና እነዚህን ሀሰተኛ መረጃዎች ህብረተሰቡ አስቀድሞ የሚገነዘባቸው በመሆኑ ለሁሉም ምላሽ መስጠቱ አስፈላጊ ባይሆንም ከሰሞኑ በተለቀቀው ሀሰተኛ መረጃ ዙሪያ ግን ትንሽ ማለት ወደናል፡፡
ከሰሞኑ አንድ ከውጭ የመጡ ግለሠብ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በሚገኘው ቅርንጫፋችን ተገኝተው ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ወር ለሚያቆያቸው ቪዛ 50 ዶላር ከፍለዋል፡፡ ቅርንጫፉም ለገዙት የቆይታ ቪዛ የሚሆን ደረሰኝ በኢሚግሬሽን መስኮት ላይ ቆርጦላቸዋል፡፡
ይህ የ50 ዶላር ክፍያ በባንካችን ቅርንጫፍ እየተሰጠ ላለው የኢሚግሬሽን ቪዛ ክፍያ አገልግሎት መሆኑ እየታወቀ ናትናኤል መኮንን የተባለ ውሸታም የፌስቡክ ተጠቃሚ ግለሠብ ግን እውነታውን በመደበቅ መንገደኛው 200 የአሜሪካን ዶላር መመንዘራቸውንና ይህን አገልግሎት የሰጠው ሰራተኛ ግን የሰጣቸው ደረሰኝ የ50 ዶላር ነው የሚል የሀሰት መረጃ በፌስቡክ ገጹ ላይ አሰራጭቷል፡፡
ይህ ሀሰተኛ መረጃ የተሰራጨው በእለቱ ከውጭ የመጡት ግለሰብ 200 ዶላር በመመንዘር የተሰጣቸውን ደረሰኝ ወደጎን በመተው ለ50 ዶላር የቪዛ አገልግሎት ክፍያ የተሰጣቸውን ደረሰኝ ለ200 ዶላር ምንዛሬ እንደተሰጣቸው በማስመሰል ነው፡፡ ይህ የሀሰት መረጃ ባንካችን ህግና ስርዓት አክብሮ የሚሰጠውን አገልግሎት ለሚያውቁት ደንበኞቻችን የባንካችንን ስም ለማጥፋት ታጥቀው የተነሱ ግለሰቦች እንዳሉ የሚያስረዳ አንድ አጋጣሚ ነው፡፡ ይሁንና በባንካችን ቅርንጫፍና ሰራተኞቻችን ላይ ግን አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡
በመሆኑም ክቡራን የባንካችን ደንበኞች፣ የሥራ አጋሮቻችን፣ ባለድርሻዎቻችን እና መላው ህብረተሰብ እንደዚህ አይነት በባንካችን ላይ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች ሲያጋጥማችሁ በጥንቃቄ በመመልከት መሰል ድርጊቶች የሚፈጥሩትን አሉታዊ ተጽእኖዎች በጋራ እንድንከላከል ጥሪያችንን እያቀረብን፣ ከውጭ ለመጡት ግለሰብ በባንካችን የተሰጣቸውን የ200 ዶላርና የ50 ዶላር ደረሰኞች ለማስረጃነት አያይዘናል፡፡
ጠበቆቻችን ናትናኤል መኮንን የተባለን ግለሠብ በስም ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ ዝግጅት ላይ ናቸው ::