Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

አሸባሪው ትህነግ አትርሱኝ ብሏል!

Post by Ejersa » 18 Jun 2021, 07:30

የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ከእነ ድክመቱ ምርጫው ላይ ትኩረት አድርገዋል። ሚዲያዎችም ሕዝብ ትኩረቱን ሚዲያ ላይ እንዲጥል አድርገውታል። በዚህ መሃል ትህነግ ተረስቷል። ድሮ ራሱ ምርጫ ደጋሽ፣ አፍራሽ የነበረ ኃይል በምርጫው ወቅት ስሙ አይነሳም። የእሱን የቀድሞ ወንበር የያዘው ሌላ ኃይል ነው። ጫካ ላለው ትህነግ ምርጫ አጭበረበረም ተብሎ ሲወገዝበት የኖረው ጮማ የሆነ ትውስታው ነው። ጫካ ሆኖ ሲያስታውሰው ምላስና ከንፈሩን አጋጭቶ ያጣጥመዋል።

ግን ደግሞ መረሳትም አልፈለገም። ትኩረት ምርጫ ላይ ሲሆን በርሃ ሆኖ "እኔም አለሁ" እያለ ነው። ታደሰ ወረደና ሌሎች ፀሐይ የመታው ኮት ላይ ኮከብ ቅርፅ ያላት አዝራር ያደረጉ ጀኔራሎቹን በፌስቡክ ሚዲያዎቹ እያቀረበ ነው። እንደ አዝራር ትክሻቸው ላይ የሚለጥፏት ነገር የጫካ ማዕረግ መሆኗ ነው። አይቅርብን ብለው ነው።
ትህነግ ከበርሃ የሚልካቸው ቃለ መጠይቆች እንደ ፉጨት ናቸው። የቀደመውንና የአሁኑን እያስታወሱ የሚቆዝሙት፣ በትዝታ የሚሰቃዩበት፣ አንዳንዴ ደግሞ እምበር ተጋዳላይን በፉጨት የሚገልፁበት ነው። ትህነግ ሰሞኑን በተደጋጋሚ የሚለቃቸው ቃለ መጠይቆች የአትርሱኝ ፉጨቶች ናቸው።

ሰሞኑን ደግሞ ሌላ አጀንዳ ይኖራቸዋል። የትግራይ ሕዝብ በሚዲያዎች ምርጫውን ሲከታተል የሞት ሞት ነው የሚመስላቸው። ስለሆነም ከኋላቸው ያለውን ተራራ እንኳን ለማሳየት ፈርተው እንጨት እየተደገፉ የሚሰጧትን ፉጨት አይነት መግለጫ ሲያኝክ እንዲሰነብት ይልኩለታል። ስንዴ እየዘረፉ የገረረውን ፉጨት መሰል ቃለ መጠይቁን ቆርጥም ይሉታል።