Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Kuasmeda
Member+
Posts: 6387
Joined: 26 Mar 2015, 08:47

20 ሰኔ፣ ዘላእለማዊ ክብር ለጀግኖች ሰማእቶቻችን!

Post by Kuasmeda » 17 Jun 2021, 13:55

በኤርትራ ሰማያት ስር ያልታለመ ክፋት፣ ያልተሰራ በደል፣ ያልተፈጸም ግፍ፣ ያልተተኮሰ የጦር መሳሪያ የለም። የኤርትራ ህዝብ በሰላም ወዳድነቱና በእንግዳ ተቀባይነቱ የሚታወቅ፣ ትጉህና ታታሪ ህዝብ በመሆኑ፣ በእንግድነት ተቀብሎ ያላስተናገዳቸው የኣካባቢው ህዝቦች የሉም ብንል የተጋነነ ኣይሆንም። የኤርትራ ህዝብ በእንግድነት ከተቀበላቸው ህዝቦች ገሚሶቹ ግን የህዝቡን መልካምነትና የዋህነት አንደ ሞኝነት በመቁጠር፣ ልክ ከእሾህ ጋር እንደተጠጋች ኣጋም ለዘመና ሲያቆስሉት ቆይተዋል።

በዚህ የዘመናት ሂደት፣ የኤርትራ ህዝብ በጣም ኣሰልቺ እና እልህ ኣስጨራሽ ትግሎችን ኣልፎ፣ ብዙ መስዋእቶችን ከፍሎ ኣሁን የምናያትን ተጠንካራና የኣፍሪካ ተምሳሌት ለመሆን የምትበቃ ሃገረ ኤርትራን ለመትከል በቃ።

እንደ ኣውሮጳውያን ኣቆጣጠር ከ 1961 እስከ 1991 በተደረገው የነጻነት ትገል፣ ትግሉን ይመራ የነበረው ህግሓኤ ከዘር፣ ከሃይማኖትና ከብሄርና ነጻ የሆነ፣ በኣንድ የልብ ህርማት የምትራመድ ኤርትራዊ ማንነትን መገንባት ቻለ። ከሁሉ በላይ ግን በራሱ የሚተማመን፣ ሃገሩን በስራ መቀየር እንደሚችል የሚያምን፣ ለወሬና ኣሉባልታ ጊዜ የማይሰጥ፣ ተመጽዋችነትን ይሚጸየፍ ዜጋ መኮስኮሱ ለብዙ ጭቁን ህዝቦች ምሳሌ ሲሆን፥ ለተቀሩት መዝባሪ ቡርዝዋዎች ደግሞ ራስምታት ሆኖባቸ ቆይቷል።

ኤርትራዊያን አርስ በሳቸው ”ደቂ ሓደ ልቢ” (የአንድ ልብ ልጆች) በመባባል ይግባባል፡፡ በፍቅር ኣና በሰላም ከጎረበቶቻቸው ጋር ለመኖር እና ለመስራትም ሁለም ዝግጁ ናቸው። የኤርትራ መንግስት በትእግስቱና በዝምታው የሚትወቅ ሲሆን፣ የዝምታው ጥበብ ተገማች እንዳይሆን ለብዙ ፖለቲካዊ ጉዳይ ቢጠቅመውም፡ በምዕራቡ ዓለም ህብረተሰብ ዘንድ ግን ይህ ዝምታው እንደ ዲፕሎማሲ ስራ ጉድለቶች ተቖጥሮ ነጋ ጠባ የጋዜጦች ጫጨታው ርእሰ-ዓንቅጾች ኣደርገውታል፡፡

ለነገሩ ሲወራ ቢዋል የትኛውን ግድብ ተሰርቶ ውሃ ሊይዝልን? የትኛውን አስፋልት ተዘርግቶ መንገድ ሊሆናን? የትኛውን እርሻ ለምቶ ዘር ይሰጣል? የህንን በመገንዘብ ይመስላል የኤርትራ መንግስት ዝምታን የመረጠው።

ቴክኖሎጂ ሰማይ ጥግ በደረሰበት ዘመን: ዓለም በአንዲት ጠባብ መስኮት ተሰብስባ አፍ ለአፍ ገጥማ ስታወጋ በምትውልበት ዘመን፣ ምንጩ ያልተረጋገጠ ዜና በቅጽበት በሚሰራጪበት በዚህ ዘመን፣ እውነት ከሃሰት መለየት ኣስቸጋሪ የሆነበት ሁነታ ተፈጥሮኣል፡፡ ያልተፈጠሩንና ያልሆኑ ነገሮች እንደተፈጸሙ ክውንነቶች ኩሎ በማቅረብ በፍጥነት ሰው ጆሮ ውስጥ መሰካት፤ በሃሰት ህዝብን ከህዝብ ማጋጨት፤ መሪዎችን ማጠልሸት፤ በግብር ከተሸነፉ በወሬና በውሸት ማስረጃ አገር አለሙን ማመስ የመሳሰሉትን እኩይ ተግባራት በአጭር ግዜ ለማራባት ብዙ ስራ የማይጥይቅበ ዘመን ሆኖኣል፡፡

የኤርትራ ህዝብ ላለፉት 80 ዓመታት የምዕራብ ሓይሎችን በሎሌነት በሚያገለግሉ በጎረቤት ሃገራት መንግስታት በተሰነዘሩበት ጦርነቶች፥ ሃገሩን በጦር መሳሪያውች ሺያጋዩበት፣ ህዝቡን በመድፍ፣ በታንክና፣ በናፓል ቦምብ ሲያነዱት፤ የዲፕሎማሲ ተነጥሎ ጫናና የተቀነባበረ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ጥቃቶችን ተቋቁሞ፥ 30 ዓመታት የፈጀ ረጅምና ውስብስብ ትግል ኣካሂዶ ሰንደቅ-ዓላማውን ለመትከል የበቃ ሰላማዊ ህዝብ በመሆኑ ኩራት ሊሰማው ይገባል።

ኤርትራ የከፈለቻቸው እነዛ ቁመናቸው የሚያማልል ወጣቶች፡ ኮረብታ ላይ ሰንዳቅ-ዓላማቸውን ከፍ ኣድርገው ሲተክሉ፣ ፎቶውን ለሚታዘበው ሰው ምናልባትም በድሎት የሚኖሩ እስካውቶች ሊመስሉት ይችሉ የሆናል። ዛላቸውና ቅርጻቸው የተሸከሙትን የሃገር እዳ ደብቆላቸው፤ ያለፉትን ሰቆቃ ሽሮላቸው እንደ ዋዛ ጀርባቸውን ሰጥተው የተከሏት የምትመስለው ሰንዳቅ-ዓላማ፣ የብዙ ዘመናት የግፍ ቀንበርን ቀብራና የብዙ ወጣቶችን ደም ጠይቃ ነው በኩራት ደረቷን ወድራ ከፍ ያለችው፡፡

ኤርትራ 30ኛውን የነጻነት በዓሏን ስታከብርና፣ ለ30ኛ ጊዜ የሚታሰበው የሰማእታት ቀንን ለብሳና ተንተርሳ ነው። ይህን የክብር ካባ ላልበሱን፣ ኤርትራዊነትን በአንድ ህርመት አጣምረው ለተሰዉት ወገኖቻችንን የምናስብበትና ቃለ-ማሓላችንን በድጋሚ የምናድስበት ግዜም ነው፡፡ ላለፉት 20 ዓመታት ኤርትራ እንዳትለማና እንዳንበልጽግ ተጭኞኗት የነበረውን ጠፍር በጣጥሳ የምትመኘውን ብልጽግና የመታየበት ዘመን ጀምሯል፡፡

ከሁሉም በላይ በምዕራባዊያን የሚመራውና ለሆዳቸው ያደሩ ርዝራዦን በመሳሪያነት እየተጠቀመ በተቀናጀ መልኩ የሚቃጣውን ባዶሽ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ፊት ለፊት ገጥመን የኤርትራን ነጻነት ዋጋ የመናስተምርበትና የምናሳይበት ምዕራፍ ነው፡፡ በድል የተወጣነውን ድምቀታችንን ማስረዳት እንደሆን አያቅተን።

Kuasmeda
Member+
Posts: 6387
Joined: 26 Mar 2015, 08:47

Re: 20 ሰኔ፣ ዘላእለማዊ ክብር ለጀግኖች ሰማእቶቻችን!

Post by Kuasmeda » 17 Jun 2021, 15:07

Kuasmeda wrote:
17 Jun 2021, 13:55

Post Reply