Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የትግራይ ጦርነትና የታዛቢ ሕሊና ፍርድ - ተጻፈ በእንዳሻው ለጠራ (በትግራይ የሚኖር ኢትዮጵያዊ)

Post by sarcasm » 17 Jun 2021, 08:56

የትግራይ ጦርነትና የታዛቢ ሕሊና ፍርድ

(ለማታውቁኝ ፍሬንዶች ግልፅ እንዲሆንላችሁ፦ እኔ ተወልጄ ያደኩት አዲስኣባ፣ ብሔሬ ኦሮሞ ፣ አፍ የፈታሁት በአማርኛ፣ ኮሌጅ የበጠስኩት በእንግሊዝኛ፣ እንጀራና ቤተሰብ መስርቼ እየኖርኩ ያለሁት በመቐለ ዩኒበቨርስቲ ትግራይ ነው። Judge my post accordingly)

የትግራይ ጦርነት ወታደር ከወታደር መጋጠም አልፎ የመንደር ነዋሪዎችን በየገጠር ሰፈር ውስጥ የሚታወቁ ንፁሃኖችን ሰለባ ማድረግ ሲጀምር የሕሊና ቀይ መስመሬ ተጣሰ።

በአማራ ክልል በምናምን ገጠር ወረዳዎች ብዙ ሺዎች አማራ ስለሆኑ ብቻ ተገደሉ ፣ አማራ ስለሆኑ ብቻ ተደፈሩ ፣ አማራ ስለሆኑ ብቻ ከመሬታቸው ላይ እንዲፈናቀሉ ተገደዱ፣ አማራ ስለሆኑ ብቻ ለረሀብ እንዲጋለጡ ተደረጉ የሚል መረጃ እና ማስረጃ ከውጪም ከውስጥም ሚዲያ ቢደርስህ ሕሊናህ ምን ይላል? ወይም ሲደርስህ ሕሊናህ ምን ብሏል?

ትግራይ ውስጥ ይህ ነው ተከስቶ ያለው። ይሄኔ ኢትዮጵያዊነት? ኦሮሞነት? ትግራዋይነት? ወዘተ የማለት ጉዳይ ከመሆን ከፍ ይልና የሰውልጅነትን የሚያጠይቅ የሕሊና ጉዳይ ይሆናል። ከፍ ብለህ መለስ ስትል ግን ጥቃቱ በፍላይ የዘር ጥቃት ነውና you get down real and hold on to your roots.
ሕዝቡ ውስጥ በመኖር የማውቀው ወቅታዊ እውነታ ማንነትን የመከላከል ስሜት ነው። ትግራዋይነትን አንበርክኮ ለመጨቆን የሚደረግ ርብርብን የመቀልበስ የሞራል ግዴታ ነው።

አደጋ ላይ የወደቀው ትግራዋይነት ማን ማንን ይመለከታል?


የትግራይ መሪ ድርጅትን ፣ የትግራይ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ፣ የትግራይ ሕዝብን፣ የትግራይ ዳያስፖራን ምሁርን፣ የትግራይ ባጃጅ ነጂን፣ የትግራይ ቢንጎ አጫዋችን ተጫዋችን. . . ተጋሩን በሙሉ።

እነዚህ ተጋሩ እህ ብለህ ስትሰማቸው ምንድነው የሚሉት?

በሰውም ሆነ በግዜር ፍርድ ከታየ ሊገልህ የመጣን ገዳይ ሳይገድልህ ቀድመህ እራስህን ብትከላከል ምንድነው ወንጀሉ ነው የሚሉት። የምታቀው ሰው እስከነ ግብርአበሮቹ ዛሬ ገዳይህ ሆኖ ከመጣ ወዳጅነቱ ቀድሞም አልነበረም፣ አብሮነቱም አብቅቷል እና ተጋሩ ያለን ብቸኛ አማራጭ መኸተ ብቻ ነው ይሉሃል።
አሁን በዚህ ሳምንት ጭምር የማውቃቸው የቅርብ ጓደኞቼ ወደ በረሃ ሄደው ትግሉን እንደተቀላቀሉ መረጃ አለ።


እያንዳንዱ ወንድ ሴት ወጣት ጎልማሳ የሚያራምደው አቋም ምንድነው ቢባል ከሞላ ጎደል ይህ ነው፦

'ትግራይ በኢትዮጵያ መንግስት አና በሸሪኮቿ ተወራለች፤ ማንነትን መከላከል፣ ራስን መከላከል ተፈጥሮአዊ ኃላፊነት ነው፤ ለዚህም እያንዳንዱ ትግራዋይ መስዋዕትነት ይከፍላል፤ በሒደቱም ትግራይ ታሸንፋለች፤ ትግራይ ትስዕር!'

Conduct a random interview on the streets of Mekelle, that's how any Tigrayan would go down right now.
አይሆንም አይባልም እና ይህ ሁሉ ፀገም በዚህ ደረጃ ኦሮሞ ላይ ቢፈፀም ምንድነው የምወስደው አቋም? ልክ የትግራይ ልጆች የወሰዱትን አቋም ዓይነት። በኦሮሞነት ብቻ መገደል፣ በኦሮሞነት ብቻ መደፈር ፣ በኦሮሞነት ብቻ ከርስት ከመሬት ላይ መፈናቀል ከመጣ ዱቢን ዱኡ'ሜ! የኦነግ ጉዳይ፣ የሸኔ ጉዳይ ሳይሆን ኦሮሞነትን የመከላከል ጉዳይ ይሆንና ትግሉ ይቀጥላል።በሒደቱም ልክ እንደ ትግራይ ኦሮምያ ትስዕር!
Please wait, video is loading...


Post Reply