Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30653
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by Horus » 17 Jun 2021, 03:01

እኔ እዚህ ፎረም ላይ ብዙ ሺ አስተያየትና ሃሳቦችን ለጥፊያለሁ። ደግሜ ደጋግሜ ተማርኩ አወቅኩ ለሚል ሁሉ ያልኩትን ደግሜ ልበለው ። የጎሳ ሕገ መንግስት፣ የጎሳ ክልል ፣ የጎሳ መንግስት ፣ የጎሳ ፌዴሬሽን፣ የጎሳ ፓርቲዎች፣ የጎሳ ትምሀርት፣ የጎሳ ባንክ፣ የጎሳ ሁልም ነገር በተንሰራፋበት አገር ዘመናዊ መንግስት፣ ዴሞክራሲያዊ ነገር፣ ዴሞክራሳዊ ምርጫ በፍጹም ሊኖር አይችልም። ይህ የጎሳ ሲስተም እስካለ ድረስ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የሚባል ነገር በፍጹም አይኖርም ።

ኢትዮጵያ የውነት ዴሞክራሳዊ ዘመናዊ የዜጋዎች መንግስት እንዲፈጠር የሚሹ ሁሉ ከዚህ ምርጫ ማግስት ጀምሮ ይህን የዘር ፖለቲካ ለመለወጥ ትግል መጀመር ግዴታ ይላቸዋል ። በነገው ምርጫ ዴሞክራሲ ይመጣል ብለው ሚያስቡ ካሉ እነሱ የፖለቲካ መሃይሞች ናቸው ።

የነገው ምርጫ ኢትዮጵያ ጠንካራ መንግስት፣ አገሪቱን ከውስጥ ተገንጣዮችና ከውጭ ወራሪዎች መከላከል የሚችል ቁመና ያለው መንግስት ያመጣል ብዬ አምናለሁ። ያም ስለሆነ ኢትዮጵያ ይበልጥ ጠንካራ አገር ሆና ትወጣለች ። ይህ ምርጫ ለብልጽግና ፓርቲ መንግስት የተወሰነ ሌጂቲሜሲ ሰጥቶ ህጋዊ ገጽታ ይሰጣል ። ስለዚህ አገር አንድ አድርጎ የሚገዛ ፓርቲና መንግስት መኖር ደሞ ቁጥር አንድ ያገር ጉዳይ ነው። ይህ ነው የነገው ምርጫ ትርጉም ።

ከዚያ ባልፈ ከምርጫው ማግስት ጀምሮ ለሚነሳው ወሳኙ ኢጎሳዊ ለሆነ ሲስተም ትግል እርሾ ጥሎ የሚሄድ ምርጫ ነው ። በእኔ ግምት ቁጥሩ ምንም ይሁን ምን እነኢዜማ፣ እነእናት አይነት ፓርቲዎች የሚይዙት የፓርላማ ሆነ ሌላ ቢሮ ለዚያ ለድህረ ምርጫው የሲቪልና የዜጋ ትግል እርሾ አድርጌ ነው የማየው ።

ይህ ምርጫ የወያኔና ኦነግ አገር የማፍረስ ፕላን ያፈረሰ ምርጫ ተብሎ ወደ ፊት ታሪክ ይመዘግበዋል ። የኢትዮጵያ ሕዝብ አገርና መንግስት ካረጋጉ በኋላ ወደ ዴሞክራሲና እውነተኛ በግለሰቦች ጥረት ለሚነዳ ብልጽግና ይተጋሉ ማለት ነው ። የልማታዊ (ብልጽግና) መንግስት በብድር የሚፈጠር እድገት ዞሮ ዞሮ ፌክ እድገት ነው የሚሆነው።

ስለሆነም በሰኞው ምርጫ ላይ ጠለቅ ያለ ህሳቤና ትንተና ማድረግ ይገባናል !

ሆረስ አይነ ኩሉ ዘኢትዮጵያ
Last edited by Horus on 23 Jun 2021, 13:17, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30653
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by Horus » 17 Jun 2021, 13:33

የስልጡን ፖለቲካ ዘመን የተጀመረ ይመስላል !

Horus
Senior Member+
Posts: 30653
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by Horus » 17 Jun 2021, 18:15

እኔ ምን ግዜም ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ እምነት ነበርኝ፣ ፍርሃቴ መንግስት ሲገፋት ወግዱ ብላ ስራውን ታስረክባቸውና ነገሩ ሁሉ ተምልሶ ወያኔያዊ ኦነጋዊ ሆኖ ይጨቀያል የሚል ነበር ፍርሃቴ። አቢይ አህመድ የብርቱካንን ነጻነት አለመንካቱ ያስመሰግነዋል ፣ በሕግ ሰር መኖርን እየተማረ ነው ። ይህ አንድ ድል ነው

ይህ ምርጫ ምዕራቦች ንቀው የተዉት ነገር ነው። ይህም የሆነው ያው የብልጽግና አንድ ፓርቲ ፌክ ውድድር ነው በሚል ነው። ስለሆነም ጭነቱ በፒፒ ላይ ነው ። ምርጫውን አውከው ስጥን ከደፉ ድምጽ ከሰረቁ የምዕራብን ትንቢት (ፕሪዲክሽን) ልክ ያደርጋሉ ። በተቃራዚው በምርጫ ሕግ ስር ከተገዙ መልካም ስም አትርፈው ያለም አድናቆት ያገኛሉ ።

እንዲያውም ወያኔ በትግሬ ዙሪያ የሚሰብከውን ዉሸት ሊገድል የሚችለው የተሳካ ምርጫ ከተደረገ ነው ። ለዚህ ነው አቢይና ፓርቲው ትልቅ እድል በእጃቸው ላይ አላቸው ። ይህም ይህን ምርጫ በሚያሳምን ደረጃ በትክክል ካካሄደ ያቢይ መንግስት ባብዛኛው ከምዕራብ ሚነሳበት ግፊት ይቆማል ።

ስለዚህ ለነአቢይ ይህ ምርጫ ትልቅ እስትራተጂክ ዋጋ አለው ።

ለነኢዜማም እንዲሁ አገርና መንግስት ካረጋጉ በኋላ አገሪቱ ወደ ዲሞክራሳዊ ካልቸር የምታደርገው ኢቮሉሽን እንዴት እንደ ሚቀጥል አዲስ አጀንዳ የሚቀይሱበት እጅግ አጓጊ አምስት አመታት ውስጥ ይወስደናል !

ግ ን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ምርጫው ቢበላሽ ትልቁ ተሸናፊ ፒፒ እንጂ ኢዜማ ወይ ሌሎች ተፎካካሪዎች አይደሉም !

Horus
Senior Member+
Posts: 30653
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by Horus » 18 Jun 2021, 16:02

ሰላም ቁጥር 1 የሕዝቡ ጥያቄና የምርጫው ገፊ ችግር ነው

sun
Member+
Posts: 9312
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by sun » 18 Jun 2021, 16:50

Horus wrote:
17 Jun 2021, 03:01
እኔ እዚህ ፎረም ላይ ብዙ ሺ አስተያየትና ሃሳቦችን ለጥፊያለሁ። ደግሜ ደጋግሜ ተማርኩ አወቅኩ ለሚል ሁሉ ያልኩትን ደግሜ ልበለው ። የጎሳ ሕገ መንግስት፣ የጎሳ ክልል ፣ የጎሳ መንግስት ፣ የጎሳ ፌዴሬሽን፣ የጎሳ ፓርቲዎች፣ የጎሳ ትምሀርት፣ የጎሳ ባንክ፣ የጎሳ ሁልም ነገር በተንሰራፋበት አገር ዘመናዊ መንግስት፣ ዴሞክራሲያዊ ነገር፣ ዴሞክራሳዊ ምርጫ በፍጹም ሊኖር አይችልም። ይህ የጎሳ ሲስተም እስካለ ድረስ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የሚባል ነገር በፍጹም አይኖርም ።

ኢትዮጵያ የውነት ዴሞክራሳዊ ዘመናዊ የዜጋዎች መንግስት እንዲፈጠር የሚሹ ሁሉ ከዚህ ምርጫ ማግስት ጀምሮ ይህን የዘር ፖለቲካ ለመለወጥ ትግል መጀመር ግዴታ ይላቸዋል ። በነገው ምርጫ ዴሞክራሲ ይመጣል ብለው ሚያስቡ ካሉ እነሱ የፖለቲካ መሃይሞች ናቸው ።

የነገው ምርጫ ኢትዮጵያ ጠንካራ መንግስት፣ አገሪቱን ከውስጥ ተገንጣዮችና ከውጭ ወራሪዎች መከላከል የሚችል ቁመና ያለው መንግስት ያመጣል ብዬ አምናለሁ። ያም ስለሆነ ኢትዮጵያ ይበልጥ ጠንካራ አገር ሆና ትወጣለች ። ይህ ምርጫ ለብልጽግና ፓርቲ መንግስት የተወሰነ ሌጂቲሜሲ ሰጥቶ ህጋዊ ገጽታ ይሰጣል ። ስለዚህ አገር አንድ አድርጎ የሚገዛ ፓርቲና መንግስት መኖር ደሞ ቁጥር አንድ ያገር ጉዳይ ነው። ይህ ነው የነገው ምርጫ ትርጉም ።

ከዚያ ባልፈ ከምርጫው ማግስት ጀምሮ ለሚነሳው ወሳኙ ኢጎሳዊ ለሆነ ሲስተም ትግል እርሾ ጥሎ የሚሄድ ምርጫ ነው ። በእኔ ግምት ቁጥሩ ምንም ይሁን ምን እነኢዜማ፣ እነእናት አይነት ፓርቲዎች የሚይዙት የፓርላማ ሆነ ሌላ ቢሮ ለዚያ ለድህረ ምርጫው የሲቪልና የዜጋ ትግል እርሾ አድርጌ ነው የማየው ።

ይህ ምርጫ የወያኔና ኦነግ አገር የማፍረስ ፕላን ያፈረሰ ምርጫ ተብሎ ወደ ፊት ታሪክ ይመዘግበዋል ። የኢትዮጵያ ሕዝብ አገርና መንግስት ካረጋጉ በኋላ ወደ ዴሞክራሲና እውነተኛ በግለሰቦች ጥረት ለሚነዳ ብልጽግና የተጋሉ ማለት ነው ። የልማታዊ (ብልጽግና) መንግስት በብድር የሚፈተር እድገት ዞሮ ዞሮ ፌክ እድገት ነው የሚሆነው።

ስለሆነም በሰኞው ምርጫ ላይ ጠለቅ ያለ ህሳቤና ትንተና ማድረግ ይገባናል !

ሆረስ አይነ ኩሉ ዘኢትዮጵያ
Hmm.... :P

Now that olf and wayane are learning the democratic process the hard way then they may go back and contemplate changing their methods and thinking for helping themselves in to the far future.

On the other hand if olf and Wayane may not visibly and invisibly offer strong counter balance for Ezema and Ennaat parties it may be so that these two parties may run wild all over the places and through that make life impossible, to say the least.

Didn't Dr. Berhanu Nega the leader of Ezema party promise death sentences for corruption if he happens to win election. I thought that he has lost his mind completely. How about if he himself happens to be found guilty of corruption? Hope all the best for that country.
:roll:

Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by Wedi » 18 Jun 2021, 17:02

Horus wrote:
17 Jun 2021, 03:01
የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

The world is laughing with Abiy Ahmed's FAKE election.

If FAKE elections could have created strong governments, woyane could not have been removed from power after 2 years it conducted another FAKE election. Abiy Ahmed will not be different :P

Horus
Senior Member+
Posts: 30653
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by Horus » 18 Jun 2021, 17:52

ወዲ የሚባል ሰው ወይም ሮቦት ወይም ፓሮት ነው! አይሰለችም እንዴ አንድ የኢኮኖሚስት ደደብ የሆነ መጣጥፍ ሺ ግዜ መለጠፍ! አቢይ አህመድ እንደ አንኛውም ተወዳዳሪ የማሸነፍ የመሸነፍ እድል አለው። ነገ ሕግ ጥሶ ድምጽ ሲሰርቅ ያኔ የምንለው ይኖራል ። አሁን ኳሱ ያለው በብርቱካን እጅ ነው፣ ጥሩ አድርጋ እያጫወተች ነው። ፒፒ የሚያሸንፈው (ካሸነፈ) ያ የሚሆንበት ምክ ኛት ሁሉ ይታወቃል። ምንም ድራማ አያሻውም ። ዴምክራሲ ሂደት ነው፣ በቃ! ዛሬ የኢትዮጵያ ጠላቶች ወያኔ ኦነግ የምራብ ኮሎኒሊዝምና ያረብ ቦርጫሞች ባዶ ትንኮሳ ነው።

አው ብርሃኑ ነጋ ሙስና በሞት የሚያቀጣ ወንጀር አደርጋለሁ ብሏል !! ሙስና አገርን መስረቅ ስለሆነ !!

ኢትዮጵያ አንድ ሕዝብ፣ አንድ አገር፣ አንድ መንግስት !!

Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by Wedi » 18 Jun 2021, 18:01

Horus wrote:
18 Jun 2021, 17:52
ወዲ የሚባል ሰው ወይም ሮቦት ወይም ፓሮት ነው! አይሰለችም እንዴ አንድ የኢኮኖሚስት ደደብ የሆነ መጣጥፍ ሺ ግዜ መለጠፍ! አቢይ አህመድ እንደ አንኛውም ተወዳዳሪ የማሸነፍ የመሸነፍ እድል አለው። ነገ ሕግ ጥሶ ድምጽ ሲሰርቅ ያኔ የምንለው ይኖራል ። አሁን ኳሱ ያለው በብርቱካን እጅ ነው፣ ጥሩ አድርጋ እያጫወተች ነው። ፒፒ የሚያሸንፈው (ካሸነፈ) ያ የሚሆንበት ምክ ኛት ሁሉ ይታወቃል። ምንም ድራማ አያሻውም ። ዴምክራሲ ሂደት ነው፣ በቃ! ዛሬ የኢትዮጵያ ጠላቶች ወያኔ ኦነግ የምራብ ኮሎኒሊዝምና ያረብ ቦርጫሞች ባዶ ትንኮሳ ነው።

አው ብርሃኑ ነጋ ሙስና በሞት የሚያቀጣ ወንጀር አደርጋለሁ ብሏል !! ሙስና አገርን መስረቅ ስለሆነ !!

ኢትዮጵያ አንድ ሕዝብ፣ አንድ አገር፣ አንድ መንግስት !!
ከብርሃኑ ነጋ የባሰ ሀገር ከሃዲ አለ እንዴ? ከኢትዮጵያ ጠላት ከሆነችው ከግብጽ እኮ 500000 ዶላር እንደተቀበለ የነገረን ራሱ ብርሃኑ ነጋ ነው!! :P

Horus
Senior Member+
Posts: 30653
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by Horus » 18 Jun 2021, 18:20

ኢትዮጵያ አይበገሬ አገር፣ ሕዝቧም ዲሽታ ጊና እየመታ ነው !! በቃ !!!!!!

sun
Member+
Posts: 9312
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by sun » 18 Jun 2021, 18:48

Wedi wrote:
18 Jun 2021, 17:02
Horus wrote:
17 Jun 2021, 03:01
የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

The world is laughing with Abiy Ahmed's FAKE election.

If FAKE elections could have created strong governments, woyane could not have been removed from power after 2 years it conducted another FAKE election. Abiy Ahmed will not be different :P

Wedi kelbi,

Not only the world but I am also laughing loud at all of those clueless laughable fools like you who are waiting for the second coming of Jesus Christ in order to collect the tplf remnants from the ToRaBora caves and place them in the new renovated King Menelik's palace located in Finfinne.

Even my donkey joins me in a sweet laughing loud laughter at your laughable comment and other laughable baboon comments you seem to misquote. Last but not least, this election is going to be the mother and father of all elections in Ethiopia which have never been seen and or heard in over 3000 years of Ethiopian history. YES WE CAN! :P

Say BINGO! and go to roll all over the places in the kitchen and pray for the election to come and stay for ever to come because then you have nothing to lose except your wretchedness and back breaking poverty with which you are familiar enough
.
:lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 30653
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by Horus » 19 Jun 2021, 03:55

በቃ! ትህነግና ሸኔ እስከ ተደመሰሱ ድረስ፣ ምርጫ ቀጥሎ የሚመጣ ነገር ነው !! ትልቁ ነገር እነዚህን 2 ካንሰሮች ማጥፋት ነው !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30653
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by Horus » 22 Jun 2021, 07:30

የዛሬ ሳምንት ያልኩት ይህ ነውን ነው። በዚህ ምርጫ አሸናፊ ስልጡኑ የኢትዮጵያ ህዝብና የብርቱካን ሚደቅሳ የምርጫ ቦርድ ናቸው ። ሌላ የለም ። ምርጫው ፍንትው አድርጎ ያሳየን ነገር የጎሣ የዘር የብሄር ንቃተ ህሊና ወይም ኮንሺየስነስ ምን ያህል ባበሻ አንጎል ውስጥ እንደ ተንሰራፋ ነው።

ትልቁ የሰሞኑ ትርክት ስህተት የሚሆነውና ከፖለቲካ ሳይንስ ውጭ የሚሆነው ይህን ምርጫ ከዴሞክራሲ ጋር ማመሳሰል ይሆናል ። ይህ ምርጫ በጎሳ ክልል፣ በጎሳ ንግፈ ሃሳብ፣ በጎሳ ቀመር ላይ የቆመ ነው ። እሱ ኤትኖክራሲ ይባላል ። በዜጋ ፖለቲካ ፣ በዜጎች ሃሳብና ጥቅም ቀመር ላይ ሲቆም ብቻ ነው ከዴሞክራሲ ጋር የሚመሳሰለው።

ይህን ምርጫ የምናወድሰው ኢትዮጵያ በራሷ የማደራጀት አቅም በሰላም በራሷ አስመራጭና ታዛቢ በራሷ ጸጥታ ሃይል ያደረገው የህዝብና አገር ጥንካሬ መለኪያ ስለሆነ ነው ።

ብዙ ግዜ እንዳልኩት ምናልባት የዚህ ምርጫ ውጤት ወደ ዜጋ የፖለቲካ ሲስተም ለመሄድ ውይይት መጀመሪያ ይሆናል !

Horus
Senior Member+
Posts: 30653
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by Horus » 22 Jun 2021, 08:35

ፍሬንች 24 ክርክ፣ ልብ በሉ ለምን የኢትዮጵያ አንድነትና መንግስት የግዜው ቁልፍ እንደ ሆነ ። የቅኝ ገዦችን ልብ በሉ !

Horus
Senior Member+
Posts: 30653
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ2013 ምርጫ ጠንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት የሚያቆም እንጂ ዴሞክራሲ የሚያያመጣ ነገር አይደለም!

Post by Horus » 23 Jun 2021, 12:37

ኢዜማ የረባ የፖለቲካ ተጽዕኖ ለመፍጠር ወደ 20% የሚጠጋ ወንበር እንደ ሚፈልግ አስልቼ ከ70 እስከ 100 ወንበር እንዲኖረው ማስፈለጉን ተስፋ አድርጌ ያለኝ አስፐሪሽን ከላይ ብያለሁ ። ይህ የኔ የግል አስፐሬሽን ነበር ። በመሬት ላይ አገር ቤት ያለው ሪያሊቲ ከኔ ምኞት የተለየ ሆነ ። በቃ ሌላ ነገር የለውም ። መሰረታዊ ትንተናዬ በዚያቅ ቀን ብዬዋለሁ ። ያስገረመኝ ነገር ቢኖር ሕዝቡ ድምጹን ይህን ያህል መንፈጉ እንጂ እኔ ኢዜማ አቢይን ያሸንፋል የሚል እምነትም ሃሳብም ኖሮኝ አላቅም ።

እኔ ሆረስ ነኝ፣ ቃል አልፈጥርም! የኢትዮጵያ 2013 ምርጫ ሙሉ ግምገማ ገና አልተደረገም። ነገር ግን በብዙ ብዙ መንገድ ይህ ምርጫ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚለውጥ ስለሆነ በአንጎሌ ጫፍ ላይ ሳይሆን በልቤ ስር ጥልቅ ደስታ ተሰምቶኛል ። ለምን?

እኔ የማምንበት ነገር አለ፣ ቲኦሪ ሃሳብ ነው፣ ምናብ ነው። ያ ቲኦሪ የሚፈተነው በተግባር ነው ። ጥሩ ቲኦሪ ብቻውን ጥሩ ተግባር አይሆንም። ጥሩ ተግባር የራሱ ሕግ አለው ። እሱን የተግባር ፍልስፍና፣ ዘ ፊሎሶፊ ኦፍ አክሽን ወይም ሆነ ብለን የምናደገው ተግባር ፍልስፍና ይባላል።

ፖለቲካን እንዲሁ የተግባር ህግ አለው ። ላንድ ፖለቲካኛ የፖለቲካ ተግባሩ ቁልፍ ቁም ነገር ቁልጭ አግድርጎ በአንድ ቃል ለማስቀመጥ መቻል አለበት ።

የ2013 ምርጫ አላማ ምንድን ነው ለሚለው ቁጥር አንድ ጥያቄ እኔ ደግሜ ደግሜ እንዳልኩት የዚህ ምርጫ ግብ በሕዝቡ እይታና ፍላጎት አንድ ያለን መንግስት ለመለወጥ፣ አንድ ሪጂም ወይም አስተዳደር ካንዱ ቡድን ወደ ሌላ ቡድን ለመለወጥ አይደለም ብያለሁ ። የህዝቡ ፍላጎ በወያኔ ተሰባብሮ ተፍረክርኮ ያለውን መንግስት ማጠንከር፣ አገር አንድ አድርጎ ማጠንከር ነው የህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄና ፍላጎት ።

ይህ ነው የዚህ ምርጫ ተግባር ፍልስፍና መቆሚያ ! ስለሆነም በምርጫው ከተካፈሉት ዋና ዋና ፓርቲዎች ስንቶቹ ይህን ፍልስፍና እንደሚገባቸው አላቅም ። ኢዜማ አንድም ግዜ በዚህ ምርጫ ሲወዳደር አላማው የአቢይን መንግስት አውርዶ ሌላ አዲስ የኢዜማ መንግስት ለማምጣት ነው ብሎ አያውቅም ። ስለዚህ ኢዜማ በዚህ ምርጫ የብልጽግና አጋር እንጂ ተቃራኒ አልነበረም ።

ይህ አቋም ትክክል ነበር ። ሕዝቡ ዛሬ የመሰከረው ያንን ነው ። ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ያላቸው ፍላጎት ጠንካራ፣ ሰላም የሚያስጠብቅ፣ አገር የሚያስቀጥል መንግስት ማደራጀት እንጂ የአቢይን መንግስት አውርዶ አዲስ መንግስት ለመሆን አይደለም። ይህን የማያውቅ ፖለቲከኛ ወደ ሌላ ስራ መሄድ አለበት ።

ከሁሉም አስቀድሞ ህዝቡ ፖለቲከኞችን ያስተማረው ትምህርት ይህ ነው። እያንዳንዱ ምርጫ የዚያን ወቅት ግብና አጀንዳ አለው ፣ የዛሬ ምርጫ አጀንዳ ሰላም ማስፈን እንጂ መንግስት መለወጥ አይደለም ፤ የሆነውም ያ ነው ።

እነኢዜማ ፣ አብን ፣ ባልደራስ ፣ ምናምን ለምን የሕዝብ ድምጽ ተከለከሉ? ከላይ ብዬዋለሁ! የተሳሳተ የመሪዎች ቲኦሪ በትክክለኛ የህዝብ ተግባር ይታረማል ይባላል።
እኔ ላለፈው 30 አመት በኢትዮጵያ ከ4 ወይ 5 ፓርቲዎች በላይ መኖር የለባቸውውም ብያለሁ፤ አሁንም እላለሁ ። ዛሬ ህዝቡ የላከው ትምህርት ያ ነው። ወይ አንድ ሁኑ ወይ ወግዱ ነው ያለው ሕዝቡ ።

በኢትዮጵያ አንድ በጎሳ ቀመር የቆመ ፓርቲ አለ፣ እሱም ብልጽግና ነው ። በዜጋ ፖለቲካ ቀመር የሚቆሙ አንድ ሊብራል ፣አንድ ሶሺያል ዴሞክራሲ ፣አንድ ወግ አጥባቂ ፓርቲዎች ሊኖሩ ይችላሉ ። ሌላ አንድ አረንጓዴ ፓርቲ ሊኖር ይችላል። በቃ ከዚህ አልፈው በግለሰቦች ምኞትና ድንቁርና ላይ የቆሙ 50፣ 1000 ፓርቲዎች በህዝብ እንደ ሚወገዱ ይህው አየን፣ አበቃ !

ሶስተኛው፣ ኢዜማ ለምን ድምጽ ተነፈገ የሚለው ቀላል ጥያቄ ነው! ፈረንጆች ፖለቲካ የሰፈር ጨዋታ፣ የሰፈር ትግል ነው ይላሉ ። ይህም ማለት በዴሞክራሲ ውስጥ አንድ ግለሰብ ምረጡኝ ለማለት እሱ ወይም እሷ በዝርዝር ለዚያ ሰፈር፣ ለዚያ መራጭ ህዝብ ሊያደርግ፣ ምን ሊያሻሽል እንዳቀደ እና ያም ዝርዝር የሰፈር ግብ ከሌላው ፓርቲ ፕላን እንዴት እንደ ሚሻል በፋክት፣ በግልጽ ህዝቡን ማሳመን አለበት ።

ኢዜማ አንድም ቦታ ይህን ሲያደርግ አልታየም፣ ኢዜማ በፍልስፍና በዜጋ ፖለቲካ ንድፈ ነገር ከብልጽግና መለየቱ ቢታወቅም ሪቴይል ፖለቲካ ወይም የፖለቲካ ችርቻሮ የሚባለው ጭብጥ፣ የሚዳሰስ፣ የሚቀመስ ጥቅም ለህዝብ ስላላቀረበ ህዝቡ ድምጹን የሚስጥለት ምክንያት አልነበረም። ይህው ነው ሌላ ምስጢር የለውም ።

ስለሆነም ይህ ምርጫ የብዙሃኖች ጥበብ ወይም ዊዝደም ኦፍ ዘ ማስስ የተረጋገጠበት ልምድ ነው ። ይህ ማለት በተለይ ብልጽግናና ኢዜማ ግልጽ የሆነ የአጭር ግዜ ልዩነት ስለሌላቸው ፣ ፈረንጅ እንደ ሚለው ለአንድ ስራ ሁለት ሰው ከቀጠርክ አንዱን አባርር ፣ ሰዉ ብልህ፣ ብልጥ ስለሆነ ሰላምና ጸጥታ ላይ ያለውን ቡድን አጠናክሮ ጠንካራ አገር እና መንግስት እንዲኖር ድምጹን ለዚያ ሰጠ ። ይህ ነው ምስጢሩ !!

ኢዜማ አልተሸነፈም ፣ ያልጠየቀውን ሊሰጠው አይችልም ። የጎሳው ሲስተም፣ የጎሳው መዋቅር ላይ ኢዜማ ቦታ እንደሌለው ፣ኢዜማ ሊመራው ሊቆጣጠረው የሚችል እስትራክቸር እንዳልሆነ ከኢዜማ በላይ ህዝቡ አውቆ የተሳሳተውን ቲኦሪ አርሞላቸዋል ። ኢዜማ በኤትኖክራሲ ላይ ዴሞክራሲ ለተገብር አይችልም ። ኢጎሳዊ ሲስተም እስከሌለ ድረስ ኢዜማ መንግሳትዊ ስልጣን ልይዝ አይችልም ። ይህ የፖልቲካ ሕግ ነው።

የኢዜማ አላማና ስራ ኢጎሳዊ የሆነ የዜጎች ሲስተም መፍጠር ስለሆነ ወደዚያ ተግባሩ ይሄዳል ማለት ነው።

ይህ ምርጫ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ህይወት ላንዴም ለሁሌም ይለውጣል የሚል እምነት አለኝ ። በሌላ ፖስት ላይ እንዳልኩት የዜጋ ፓርቲዎች ቢያንስ 20% ወንበር ካላገኙ የብልጽግና ማጣፈጫ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ ስለማይኖራቸው ፓርላማ ከመቀመጥ አለመግባታቸው የተሻለው ነው። የዛሬ አምስት አመት 2 ወይም 3 አገር አቀፍ ፓርቲ ሆነው ይምጡ። እስከዚያ ኢትዮጵያ አባይን ትሙላ !! በቃ
Last edited by Horus on 23 Jun 2021, 14:16, edited 1 time in total.

Post Reply