Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Sadacha Macca
Senior Member
Posts: 12335
Joined: 22 Feb 2014, 16:46

A quick Gurage history lesson/interesting tidbit

Post by Sadacha Macca » 13 Jun 2021, 20:19

‘’Powerful Gurage clan chiefs and warriors had made several attempts to create a centralized state. Most notable was Azmach Sebeate, who at the end of the 16th century put down Oromo incursions into Gurage territory and declared himself king of Gurage-land.
Throughout Gurage history, tribes and clans paid tribute annually to successive reigns of Ethiopian Kings in gold, figurines, hides, and cattle, thereby retaining some form of political independence. Despite this payment of tribute, however, incursions from the neighboring peoples never ceased altogether, and there was no letup in the continual raiding of Gurage for slaves until the extension of the Ethiopian Empire government rule over all Gurage communities, finally, in 1889.
It is possible that the name Gurage was given by the Amhara--- Ethiopia’s dominant people group—to all the languages spoken by the people on their southern periphery. In Amharic, Gurage means ‘’area of the Gura.’’ Gura is another name for Hararghe, the traditional name for the area around Harar.’’

[Encyclopedia of the World's Minorities
By Carl Skutsch; pages 531-533]

Horus
Senior Member+
Posts: 30844
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: A quick Gurage history lesson/interesting tidbit

Post by Horus » 13 Jun 2021, 21:19

ሳዳቻ መጫ
አስተያነቴን በአማርኛ አደርገዋለሁ። ጉራ ስለ ሚለው ቃል ትርጉምና ሰረ ቃል ሌላ ግዜ እመለስበታለሁ። ጌ የሚለው ቃል ግን ምንም ክርክር የለበትም። ቃሉ ሙሉ በሙሉ የጥንት ግብጽ ቀምጥ ሲሆን ምድር ወይም መሬት ማለት ነው ። ግሪኮች ተውሰው ጌዎ፣ ጌያ፣ ጂኦ የሚሉትን ስረ ቃል ሆኖ ዛሬ ጂኦግራፊ፣ ጂኦሎጂ፣ ጂኦፖለቲካ የምንለው ነው ። ለምሳሌ ጆርጅ የሚለው ስም የመሬት ሰራተኛ ወይም ገበሬ ማለት ነው ። አልፎ አልፎ የላቲን ዝርያ ቋንቋዎች ጌ የሚለው ቤት (ሃውስ፣ መኖሪያ) ለማለት የጠቀማሉ።

በሴም ቋንቋዎች ውስጥ ቤት ለማለት ጌ የሚጠቀም ጉራጌና በጥቂቱ ያማርኛ ተናጋሪዎች ናቸው። የአረብና ያይሁድ አለም ጌ ለማለት ቤ ነው የሚሉት ። ቤ ሲበዛ ቤት ነው ። ስለዚህ ቤት ነጠላ ስም አይደለም ። ለምሳሌ አርጎባ (አርጎቤ)፣ በስልቴ ዎራቤ፣ አደሬዎችም ቤ ነው የሚሉት ። አማርኛ፣ ሌሎች የሰሜን ልሳኖች የሚሉት ቤት ነው ። ቤት ማለትና ቦታ ማለት አንድ ቃል ነው።

ጌ ወደ ቤ የለወጡት ግሪኮች ይመስሉኛል፣ ሌሎች ብዙ ኬህ ድምጽ የነበራቸው ስረቃላት ወደ ፔ እና ፌ ለውጠውታል፤ ለምሳሌ ፊዚካል፣ ፕስይኪ ወዘተ ።
ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ በሁሉም ጉራጌ ዘንድ ጌ ማለት ቤት ማለትና እንዳልከው ቦታ፣ ምድር፣ አገር ማለት ነው ። ጌ ነጠላ ስም ነው፣ ሲበዛ ጌት፣
ጌይት፣ ጌያት ይባላል ። ጌያት ወይም ዛሬ ገየት ማለት ቤቶች፣ ሰፈር ማለት ነው ። ትልቁ ቃል ከተማ ከጌያት የወረደ ነው ።

ለዚህ አርጎቤ ማለት አርጎጌ፣ ወራቤ፣ ወራጌ እንደ ማለት ነው። በጉራጌ ዘንድ ጌ ቤት፣ ቦታና አገር ብቻ ሳይሆን የጎሳ መለያም ነው ። ለምሳሌ የሸዋ አማራ አዲስጌ እንደ ሚሉት በጉራጌ አረትጌ፣ አንገትጌ ወዘተ የጎሳ መሰየሚያ ነው ። ስለዚህ ጌ የጉራጌ እጅግ ጥንታዊ ቃል ነው፣ ሌላ ሰው የሰጣቸው ስም አይደለም።

ጉራ
በጥሬ ትርጉሙ ጉራ ማለት ግራ ማለት ነው ። እርግጥ በግራ በኩል ያለ ነገር ማለት ነው ። ያንን ነው አለቃ ታየ በጦር ሰፈሩ ግራ በኩል ወይም ግራ ዘማቾች፣ ነበሩ ያለው። ግምት ነው ። በመሬቱ አቀማመጥ ግራ የሚለው ሃሳብ ትርጉም አይሰጥም። ሙሉ ዝርዝሩን ሌላ ግዜ አመጣዋለሁ። ጉራ ተብሎ ለወጥ የተደረገው ጎራ የተሰኘው ቃል ነው። ጎራ በጉራጌኛ ጎሳ ማለት ሲሆን ጉራጌ ራስ ገዝ በነበሩበት ዘመን ያስተዳደር ሴራቸው አጉራጠነ፣ ጎራጠነ ይባል ነበር። ይህ ቱባ ጉራጌኛ ሲሆን ራስገዝ፣ ራሱን የቻለ አስተዳደር ማለት ነው ። ለምስሌ በነሱሰንዮስ የኢትዮጵያ ጦር አዛዥ የበሩት ራስ ዘስላሌ ግዜ ጉራጌ አጉራተነ (ጎራጠነ) ነበር ።

ያ ነው ምስጢሩ፣ ሁሉም ወደ ፊት ይጻፋል። ኬር

Post Reply