Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Horus
Senior Member
Posts: 19271
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ሙፈሪያት ከሚል የስልጤ ንግሥት ተባለች !!

Post by Horus » 11 Jun 2021, 01:41

የዛሬ ሁለት ቀን የስልጤ ማህበረ ሰብ ሙፈሪያ ከሚልን የጊሥትነት ማዕረግ ሾሞዋታል! ደስ የሚለ ነው! ይገባታል!! እንኳን ደስ ያለሽ እላለሁ !!

ይህን ሃረግ የከፈትኩት ይህ ሹመት (ማዕረግ) የመላ ጉራጌ ታሪካዊ ባህል መሆኑና ትክክለኛ ትርጉሞቹን ለማያውቁ መረጃ እንዲሆን ብዬ ነው ። በቅድሚያ ሌላ ንትርክ ውስጥ ለመግባት ሳይሆን ስልጤ በግንዱም ሆነ በባህሉ፣ በታሪኩም ሆነ በሳይኮሎጂው ጉራጌ መሆኑን የጉራጌ አንዱ ጎሳ መሆኑን መጥቀስ እውዳለሁ ።

ጊሥቴ ምንድን ነው? ምን ማለት ነው? በጉራጌ ባህል ውስጥ ዛሬ አጠቃቀሙ እንዴት ነው?

ጊሥት ወይም ጊሥቴ ማለት በጥሬ ትርጉሙ ንግሥት ማለት ነው ። ቃሉ በመላ የኢትዮጵያ ሴም ቋንቋ ያለ ሲሆን ጋዝ፣ አጋዝ፣ ገዥ፣ ነጋሲ፣ ንጉሥ፣ ንግሥት ማለት ነው። በታሪክ ብዙ የጉራጌ ጎሳዎች ክስታኔን፣ ስልጤን ጨምሮ ሴቶችን ያነግሱ ነበር ። በጉራጌኛ ጋስ ማለት ጦርነት፣ ዘመቻ ማለት ሲሆን አጋስ፣ አጋሲ፣ ኣጋዝ ጦር አዛዥ ማለት ነው ። የጦር ጌታ አበጋዝ (አባ ጋዝ) ይባላል። ያው ድሮ የጦር አዛዥ ንጉሱ ነበር። ይህ የንጉስና የጦር ጌታ ወደ ሴቶቹ (እንሺታተ) ሲመጣ ጊሥቴ ይባላሉ ።

አሁን የነጋሲ ሴራ በሌለበት ዘመን ይህ የክብር ስም ለታላላቅ ሰዎች፣ ያገር አባት ለሆኑ መሪዎች የክብር ስም ነው ። በቤተሰብ ደረጃ እጅግ ባሊቅ የሆኑት ለምሳሌ አንጋፋ አያት አጋ ሲባል ሴት አያት ደሞ ጊስቴ ብለን እነቆላምጣቸዋለን፣ ጌቶች፣ እሜቴ፣ ንግስቴ፣ ክብርት እንደ ማለት ነው ።

በጉራጌ ወጣቶች ዘንድ በተለይ በክስታኔዎች ዘንድ ልጃገረድ ጓደኞች በክብር እርስ በርስ ሲቆላመጡ በስማቸው አይጠራሩም፤ ዬጎስቴ ተባብለው ነው የሚጣሩት ። ወንድ ጎረምሶች አጉሽት ይባላሉ ። የቃሉ ስር ያው ጋስ ጎሽ፣ ጉሽት፣ አጉሽት ጉሽቴ፣ ጊስቴ የሚለው ነው።

ስለሆነም ጊስቴ የሚለው የንግስትነት፣ የመሪነት ማዕረግ ለክብርት ሙፈሪያት ከሚል ይገባታል ። ባህሉ ግን የመላ ጉራጌ ባህል ነው። ያው እንደ ሚባለው ስልጤ ከጉራጌ ተለየ እንጂ ባህልና ታሪኩ ጉራጌ ነው ።

ሆረስ ዐይነ ኩሉ ዘአማውቴ

Guest1
Member
Posts: 1809
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ሙፈሪያት ከሚል የስልጤ ንግሥት ሆነች !!

Post by Guest1 » 11 Jun 2021, 02:52

ጊሥቴ ምንድን ነው? ...
ስለሆነም ጊስቴ የሚለው የንግስትነት፣ የመሪነት ማዕረግ ... ባህሉ ግን የመላ ጉራጌ ባህል ነው።
በምስራቅ ጊስቲ well-mannered/ምናልባት ጨዋ ወይም ታዛዥ የሆነች ልጅ/ ወጣት ሴት ጊስቲ ይላሉ። በማቆላመጥም ጊስቲኤ (የኔ ጊስቲ) ሁልጊዜ የሚጠቀሙበት ማለት ባህላቸው እንደሆን ተረድቻለሁ።
ለሴት ጊስቲ = ጊስቲኤ= የኔ ጊስቲ
ለወንድ ጌሲ። ጌሲኤ = የኔ ጌሲ
ጊስቴ = ጊስትኤ የኔ ጊስት ማለት እንደሆን ይፋ ይደረግ! እፋ! ክክክክክክክክክ

በምስራቅ ምናልባት ጊስቲ የንግስት ስም ነበር (አላውቅም) ከነበርም የህዝብ ልጅ ስም ከተቀየረ ቆይቷል። የህዝብ ልጅ መጠሪያ ነው! አሁን ስልጤዎቹ ማንገስ ሲፈልጉ ጊስቲ ቢሉ a move forward ሳይሆን backward ነው። ክክክክክክክክክ

ንጉስና ንግስት

በምስራቅ ሀረጌ wezir wezirit ወዚርና ወዚሪት ንጉስና ንግስት ነበሩ። በአሚርና አሚርት ሲተኩ ማለት እነዝህ የበላይ ሲሆኑ ክክክክክክክክክክክክክክክ ከንጉስ በታች ያለ ማኧረግ ሆኖ ቀረ ክክክክክክክክክክክክክክክክክክ። ታሪካዊ ሽግግር ነበር።

ሆረስ
በስልጤ ጉራጌ ወይዘሪትና ወይዘሮ የለም? ወይ ጉድ!!! ክክክክክክክክክክክክክ

Noble Amhara
Member+
Posts: 5345
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia

Re: ሙፈሪያት ከሚል የስልጤ ንግሥት ተባለች !!

Post by Noble Amhara » 11 Jun 2021, 02:58

______
___________
—-___________

Abiy should open Shewa cultural Center in Addis Ababa the real Ethiopia can be shown by bringing diverse Showa Gurage Shewa Amhara and showa Oromo together true Origin of Ethiopianism this idea represents majority of Addis Ababa and will be most popular cultural Center in Ethiopia if we look at PPs artificial Oromia and Amhara cultural Centers in Addis Ababa they are dead and abandoned because Addis Ababa is Shewa multicultural mixed city unity is what brings blessing to Shewa people the marginalized pride of Ethiopia Abiy must be self destructive not to follow my idea which brings prosperity and blessing to the greater region
Last edited by Noble Amhara on 11 Jun 2021, 03:57, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member
Posts: 19271
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሙፈሪያት ከሚል የስልጤ ንግሥት ተባለች !!

Post by Horus » 11 Jun 2021, 03:51

Guest 1

ነገርኩህኮ! አደሬ በኦቶማን ቱርክ ባህላቸው ከመጥፋቱ በፊት የጉራጌኛ ወንድም ህዝብ ነበሩ ። እኔ ከ100 አመት በፊት የተጻፈ የሃረሬ ቃላት መዝገብ አለኝ። 30% ያክሉ አደሬ ቃላትና ክስታኔ ቃላት አንድ ናቸው። ስለ ጊስቴ ነገርኩህ የክስታኔ ልጃገረዶች እርስበርሳቸው ሚጣሩት ዬጎስቴ (የግስቴ) ተባብለው ነው። ስለዚህ ትክክል ነው !

ዋዚር እና ዋዚሪት ለየት ይላል ። ቃሉ አረብኛም ፋርሲም ነው። በጉራጌኛ ያለው የድሮ ትርጉሙ ነው ። ዋዛራ የሚባለው አረብኛ እኛ ወዘላ እንለዋለን እሱም ስራ፣ ተግባር፣ ታስክ ማለት ነው የቃሉ መሰረት ፤ ስራ ማለት ነው ፣ ይህ ስራ፣ ተግባር አለብኝ ለማለት የምንጠቀመው ቃል ነው።

በአረቡ አለም የንጉስ ወይን የሻህ አገልጋይ፣ ሰራተኛ፣ መልክተኛ እንደ ራሴ ነው እንጂ ራሱ ንጉስ ወይም ንግስት አይደለችም። ዋዚር እንደ ራሴ ማለት ነው ።

Guest1
Member
Posts: 1809
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ሙፈሪያት ከሚል የስልጤ ንግሥት ተባለች !!

Post by Guest1 » 11 Jun 2021, 03:54

Abiy should open Shewa cultural Center in Addis Ababa the real Ethiopia can be shown by bringing diverse Showa Gurage Shewa Amhara and showa Oromo together true Origin of Ethiopianism this idea represents majority of Addis Ababa and will be most popular cultural Center in Ethiopia
የሸዋ የባህል ማዕከል? ክክክክክክክክክክ :lol: :lol: :lol: :lol:
የሞቱላት ጎንደሬዎችስ? የሞቱላት ሶማሌዎችስ? የገነቧት ሃራሪዎችስ? ዘይገርም ነገር! የኢትዮጵያ የባህል ማእከል ማለት ከበደህ አይደል? ድንበርተኛ! ክክክክክክክክ

Horus
Senior Member
Posts: 19271
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሙፈሪያት ከሚል የስልጤ ንግሥት ተባለች !!

Post by Horus » 11 Jun 2021, 18:21

በጉራጌና ስልጤ ያለው ነቃ ነቃ እንዲያ የምርጫ ሰሞን ግርግር ሆኖ እንዳይቀር እንሰጋለን


Horus
Senior Member
Posts: 19271
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሙፈሪያት ከሚል የስልጤ ንግሥት ተባለች !!

Post by Horus » 11 Jun 2021, 21:07

ልብ በሉ በአንድ ቀን ውስጥ ቃሉን አበላሽተወት 'ጊስቲት ' ሲሉት ታሳዝናል ። ጊስቴ ማለት ትክክለኛ አባባሉ ነው። አማርኛ ወይም ግዕዝ መጠቀም ከፈለጉ ንግስት ሊሉ ይችላሉ ። ንግስቲት አይባልም፣ ንጉስ ወንድ ተባዕታይ ስሙ ነው ። ንግስት (ጊስቴ) አነስታይ (የእንስት) ስም ነው።

Post Reply