Page 1 of 1

"ሁሉም ጓደኞቼ የሕወሓት ኣባላት ኣይደሉም። እንዲያውም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኣመራር ናቸው። ግን ሁሉም ወደ ትጥቅ ትግል በረሃ ወርደዋል፤ ብቻየን ቀረሁ።" የዓረናው አመራር ዓምዶም ገብረስላሴ

Posted: 10 Jun 2021, 18:33
by sarcasm
ዛሬ ጥዋት የሳወት ሊቀ መንበር የሆነው ሃያሉ ጎድፋይ ለትጥቅ ትግል ወደ በረሃ መውረዱ ሰማው።

የኔ ትውልድም እንደ "ያ ትውልድ" ከሰለማዊ ትግል ወደ ትጥቅ ትግል እያዳላ ይገኛል።

በፎቶው የምንታየው ደስታ ገረመድህን፣ መሓሪ ይሃንስ፣ ሃያሉ ጎድፋይና እኔ ዓምዶም ገብረስላሴ ስንሆን በሃያሉ ልደት የተነሳነው ነበር።
ከነዚህ ወጣቶች መሃል ማንም የህወሓት ኣባል ኣይደለም። ታድያ የትጥቅ ትግሉ ዓላማ "ነፃ ሃገረ ትግራይን ለመመስረት ነው" ይባላል።
ከነዚህ 4 ጓደኛሞች በሰለማዊ ትግል ተስፋ ያልቆረጥኩ እኔ ብቻ ነኝ።

ከግዜ ወደ ግዜ የትጥቅ ትግሉ ታላቅ ህዝባዊ ተቀባይነት እያገኘ ያለው ትግል እየሆነ መጥተዋል።

ይሄ ትጥቅ ትግል በኢትዮጵያና በቀጣናው ብዙ ጉዳት ሳያደርስ ያለ ቅድመ ሁኔታ ሰለማዊ ውይይትና ድርድር መካሄድ ብቸኛው መፍትሄ ነው።

በሰላም ተመለስ ጓድ ሃያሉ።

*ድርድር ብቸኛው የችግሮቻችን መፍትሄ ‼️

*ተጋሩ ይመውኡ ❗️[facebook]



https://www.facebook.com/amdom.gebresla ... 4390254183