Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member
Posts: 19421
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው፤ ብልጽግና ወይስ ኢዜማ?

Post by Horus » 09 Jun 2021, 14:13

  በዚህ የምርጫ ዙር የጉራጌ ሕዝብ ግልጽ የሆነ ሁለት የድምጽ አማራጮች አሉት ፣ ኢዜማና ብልጽግና ። እስቲ እነዚህ 2 ፓርቲዎች ስንት ስንት ወኪል እንደ ሚያገኙ ይታላል። ከዚያ ባለፈ ስራ፣ ኢንዱስትሪ፣ እድገት፣ ህብረት፣ ጥረትና ፍቅር ጉራጌን ማስተማር እናትን ምጥ ማስተማር ነው ።

  አቢይ እንደ ምኒልክ በታሪክ ለመታወስ ካሻው ኢትዮጵያን በጉራጌ ሞዴል ማዘመን ብቻ ነው ያለበት ሌላ አዲስ ካልቸር አይፈልግም ። የምዕራብ ስልጣኔ የተወለደው ከስራ ክቡርነት ፍልስፍናና ስነምግባር ነው ። ልመና አጸያፊ የሆነበት የኢንዱስትሪ፣ ሰላምና ኬርነት ካልቸር የሰረጸባት ኢትዮጵያ ማብቀሉን እንትጋበት ። የቀረው ሁሉ ጊዜያዊ የፖለቲካ ግርግርና እጅ መንሻ ነው ይገባናል ። ይሁን ያው ፖለቲካም የሚዘወረው በዚህ መንገድ ስለሆነ !!
  Last edited by Horus on 13 Jun 2021, 14:32, edited 7 times in total.

  Horus
  Senior Member
  Posts: 19421
  Joined: 19 Oct 2013, 19:34

  Re: የጉራጌ ማህበር፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል እንጂ ፖለቲካ አይደለም

  Post by Horus » 09 Jun 2021, 14:32

  በሚቀጥለው 5 አመት ውስጥ ኢትዮጵያን ከጎሳ ፖለቲካ ነጻ እናወጣታለን ! የኢትዮጵያ ቁጥር 1 ችግር የጎሳ 'ፖለቲካ ' ነው !!

  Last edited by Horus on 10 Jun 2021, 13:29, edited 1 time in total.  Guest1
  Member
  Posts: 1822
  Joined: 28 Dec 2006, 01:02

  Re: የጉራጌ ማህበር፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል እንጂ ፖለቲካ አይደለም

  Post by Guest1 » 09 Jun 2021, 15:09

  የምዕራብ ስልጣኔ የተወለደው ከስራ ክቡርነት ፍልስፍናና ስነምግባር ነው ።
  የምዕራብ ስልጣኔ የተወለደው በመዝረፍ፤ በሌብነት በሙስና በባሪያ ንግድ፤ በርካሽ ጉልበት... በደሃው ደምና ትከሻ ላይ ነው!! ስውዬው! ደም ፍላት!
  የቀረው ሁሉ ጊዜያዊ የፖለቲካ ግርግርና እጅ መንሻ ነው ይገባናል ። ይሁን ያው ፖለቲካም የሚዘወረው በዚህ መንገድ ስለሆነ !!
  ፓለቲካና ኢኮኖሚ መለያየት አይቻልም። ጉራጌ ኢኮኖሚ ካወቀ የግዴታ ፓለቲካም ተምሯል። ፓለቲካ እንዳያውቅ ከተደረገ ከሰረ። የጉራጌ ታታሪነት፤ ስራ አለመናቅ ጋር አታምታታው። ትግሬዎች ስራ የማይንቁ ታታሪዎች ናቸው። ሌላም በደቡብ ህዝቦች ውስጥ መጥቀስ ይቻላል። ሶማሌዎች በቆላው ከብት እየጠበቁ ጥርስ መፋቅ ይወዳሉ :lol: ከብት መዝረፍም ባህላቸው ሳይሆን አይቀርም ክክክክክክ....በከፊልም ቢሆን የአካባቢ አየርም አስተዋጾ አለው።

  ዘርፈው በሙስና የተጨማለቁ የአፍሪካ አገሮች ያላደጉበት ምክንያት ምንድነው? conspicuous consumption ይባላል... ዘልዛላ ስለሆኑ ክክክክክክክ

  Horus
  Senior Member
  Posts: 19421
  Joined: 19 Oct 2013, 19:34

  Re: የጉራጌ ማህበር፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል እንጂ ፖለቲካ አይደለም

  Post by Horus » 09 Jun 2021, 15:36

  አቢይ አህመድ በንግግሩ ላይ አጋሮ ከተማን ጠቅሶ ነበር ! ይህ ያርጋው ዘፈን (ፖሊስ ባንድ) ከዛሬ 60 አመት በፊት! አጋሮ ከተማ !!!

  Last edited by Horus on 10 Jun 2021, 13:31, edited 1 time in total.


  TGAA
  Member
  Posts: 2868
  Joined: 07 Apr 2019, 20:34

  Re: የጉራጌ ማህበር፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል እንጂ ፖለቲካ አይደለም

  Post by TGAA » 09 Jun 2021, 21:54

  Horus wrote:
  09 Jun 2021, 15:36
  አቢይ አህመድ በንግግሩ ላይ አጋሮ ከተማ ጠቅሶ ነበር ! ይህ ያርጋው ዘፈን (ፖሊስ ባንድ) ከዛሬ 60 አመት በፊት! አጋሮ ከተማ !!!

  I remeber Argaw Bedaso dancing standing on his head.. It was a uniquely his Own . Just Getachew Mekuria used to like kneeling down when he play his saxophone. It was a treat . Looking from cultural aspect of it Gurageas have a great culture asset to be proud of and share it abundantly with all Ethiopans, take ketfo , Ethiopian staple food; can't live with out it! Having said that I don't think Guragas will be impressed by the political spin of triablist of all sort -- where the culture of praticality is the norm the tribal fluff just doesn't cut it.

  Horus
  Senior Member
  Posts: 19421
  Joined: 19 Oct 2013, 19:34

  Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

  Post by Horus » 09 Jun 2021, 22:36

  TGAA,

  The tribal fluff these days is our version of pork barrel politics perfected by Adanech Abebe and Abiy. Adanech is doling out cultural centers to every tribe in Addis and Abiy has been either laying new foundations or cutting ribbons!!! It is election time !! That is how I see it - all these frantic activities only 2 weeks to the election.

  This is why I attached Berhanu's campaign stop in Gurage to show the kind of challenge PP is facing there . After 30 years of marginalization and neglect, Gurage 'gets' a piece of land for a cultural center exactly 12 days to a critical vote !!!! Interesting indeed!

  Horus
  Senior Member
  Posts: 19421
  Joined: 19 Oct 2013, 19:34

  Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

  Post by Horus » 09 Jun 2021, 23:22

  በሰባት ቤት ጀፎረ የሚባለው በክስታኔ ጌፎለ ይባላል፤ እሱም ከቤት ጅርባ ያለ ክፍት ቦታ ሲሆን ጌፊት ወይም ግፍት (ከቤቶች ፊት ለፊት ያለ የጋራ ቦታ ነው። ከቤቶች ፊት ለፊት እንደ መንገድ የጋርዮሽ የሚሆነው ጠበብ ካል ጥቅሙ መንገድነት ነው ። ሰፊ ከሆነ እና በተለይ በጣም ሰፊ ከሆነ የጋርዮሽ ከብት መገጃ፣ ለበዓል፣ ለግ ና መጫወቻ ፣ ፈረሰ ጉግስ መጫወቻ ሁሉ ይሆናል ። ጀፎረ ወይም ጌፎለ እንግሊዞች ኮመንስ (የጋራ ቦታ) የሚሉት አይነት ነው። ከብት ማገድም በደቦና በተራ ስለሆነ ተራ የደረሰበት እረኛ ከያንዳዱ ቤት ደጅ ከብቶችን ሰብስቦ እዚያ ሲያግድ ውሎ ሲመሽ በዚያ መልክ በየደጁ ከብትቹን ለየባለቤቱ ያከፋፍላል። ከብቶች ቤራቸውን ያውቃሉ ። ይህ የእረኞች ደቦ (ተራ) ዎጀ ይባላል። በደቦ፣ በጅጊ፣ በዉሳቻ የሚሰሩ አዋቂዎች ብቻ አይደሉም ። እረኞች ሁሉም በቀኑ ከብት ከመጠበቅ አንዱ አንድ ቀን አንዱ ሌላ ቀን ይጠብቃሉ፤ ያ ዎጀ ይባላል!
  Last edited by Horus on 10 Jun 2021, 13:37, edited 1 time in total.

  Horus
  Senior Member
  Posts: 19421
  Joined: 19 Oct 2013, 19:34

  Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

  Post by Horus » 09 Jun 2021, 23:42

  አቢይ አልተጋበዝኩም ይላል! አልገባኝም ። ስለ ኩርፊያ ሁለቴ አንስቷል? አልገባኝም?  Horus
  Senior Member
  Posts: 19421
  Joined: 19 Oct 2013, 19:34

  Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

  Post by Horus » 10 Jun 2021, 02:53

  ይህ የጉራጌ ባህል ማዕከል (ጉብማ) የሚያርፍበት ቦታ ስፋት ምን ያህል እንደ ሆነ አላውቅም ፤ ነገር ግን ማዕከሉ ቢያንስ አራት (4) የተለያዩ ህንጻዎች እንዲኖሩት ያስፈልጋል፤

  1. ቤተ ጉራጌ፣
  ይህ ምንም ምስማርና ብረት የሌለው ቱባው ትልቁ የጉራጌ ባህላዊ የሳር እልፍኝ በቃጫ ገመድ፣ በጎርደና እንጨትና በችባን የሚሰራው ክብ ቤት ነው። ጥቅሙ ላንዳንድ ትላልቅ ጉዳዮች ካልሆነ በተቀር የቤት ሞዴል ሆኖ አንድ ቤት መኖር ያሉባቸውን ቁሳቁሶች እና ዲዛይን ይዞ የሚቀመጥ ነው።

  2. የመስቀል አዳራሽ፣
  ይህ ዘመናዊ ህንጻ ሲሆን አገልግሎቱም መሰብሰቢያ፣ ትራኢት ማሳያ፣ ግብዣና ሰርግ ማድረጊያ፣ ዘፈን፣ ቲያትር እና ሌሎቾ ሶሺያል ዝግጅቶች ማድረጊያ ነው ።

  3. ቤተ መዘክር (ሚዩዚየም)፣
  የመላ ጉራጌ ህዝብ የሚዳሰስ፣ የሚታይ፣ ቁሳዊ፣ ሳይንሳዊ፣ ኪነታዊ፣ ታሪካዊ የካልቸር እና ታሪክ ውጤቶችን መሰብሰቢያና ማሳያ ህንጻ ነው።

  4 የጉራጌ ሴራ መንበር፣
  ይህ ህንጻ ሳይሆን አገር ቤት ያሉት የጆካ፣ የጎርደና፣ ሌሎች የሴራና ህግ መፈጸሚያ፣ መሰብሰቢያ በትልቅ ዛፍ ስር ሚሰራ የሸንጎ፣ የሳቡኘት መንበር ወይም ቦታ ነው ።

  5. ቦታው ሰፊ ከሆነ አንድ ሌላ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የምርምር፣ የሚዲያ እስቱዲዮና የሬኮርዲንግ እስቱዲዮ ህንጻ ይኖረዋል


  ሆረስ ዐይነ ኩሉ ዘአማውቴ !

  Guest1
  Member
  Posts: 1822
  Joined: 28 Dec 2006, 01:02

  Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

  Post by Guest1 » 10 Jun 2021, 04:46

  ይህ የጉራጌ ባህል ማዕከል (ጉብማ) የሚያርፍበት ቦታ ስፋት ምን ያህል እንደ ሆነ አላውቅም ፤ ነገር ግን ማዕከሉ ቢያንስ አራት (4) የተለያዩ ህንጻዎች እንዲኖሩት ያስፈልጋል፤
  Horus
  ጥያቄ አለኝ። ብዙ።
  የባህል ማእክሉ አዲስ አበባ ላይ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ምንድነው? የአማራና የኦሮሞ የባህል ማእከል ስለገነቡ ፍክክር መሆኑ ነው? ወይስ አዲስ አበባ የአማራ ብቻ አይደለችም ለማለት?

  የባህል ማእክል ስራው ምንድነው? ባህል ማስተዋወቅ። አዲስ አበባ ላይ ለማን ለማስተዋወቅ? ለአዲስ አበባ ህዝብ? የውጭ አገር ጎብኚዎች የአዲስ አበባን የጉራጌ ማእከል ከጎበኙ ብኋላ እንደገና ጉራጌ አገር ያለውን ሊጎበኙ ወይስ ጉራጌ አገር ማእከል የለም? ቢኖርም አይጎበኙም። በጉራጌ አገር ገንዘባቸውን እንዳያፈሱ ይሆናል።

  የተሻለ አማራጭ በጉራጌ አገር ሆቴሎችም ለመገንባት የሚያስችል ሰፊ ቦታ እንዲሰጣቸው መጠየቅ። የውጭ ጎብኚዎችን ወደ አገራቸው መሳብና ለጉራጌ ህዝብ ስራ መፍጠር። በአዲስ አበባ ላይ በስማቸው ቤተ መጽሃፍት ወይም ት/ቤት በቂ ነበር። ከዝህ ያለፈ ደረቅ ፓለቲካና ኢኮኖኦሚ አይደለም? :lol:

  Horus
  Senior Member
  Posts: 19421
  Joined: 19 Oct 2013, 19:34

  Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

  Post by Horus » 10 Jun 2021, 10:37

  የኦሮሞ ባህል ማዕከል ይህን ይመስላል።


  Guest1
  Member
  Posts: 1822
  Joined: 28 Dec 2006, 01:02

  Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

  Post by Guest1 » 10 Jun 2021, 11:33

  Horussssssssssss kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk
  የኦሮሞ ማእከል ሌላ ከተማ የላቸውምና አዲስ አበባን መረጡ ክክክክክክክክክ ተው! ወዴት ወዴት!

  የተሻለው አዲስ አበባ ላይ በጉራጌ ስም ት/ቤት ወይም መጽሃፍት ቤት። ት/ቤት መጽሃፍት ቤትም ስለሚኖረው የኔ ምርጫ ት/ቤት። የጉራጌ ልጆችን በትምህርት ማስታጠቅም ትርጉም ይሰጣል? አይሰጥም? የጉራጌ ባህል ማእክል በከተማቸው የጉራጌ ህዝብ በባህሉና ታሪኩ ተጠቃሚ እንዲሆን። ሌላ ምሳሌ ትግራይ ብዙ ታሪካዊ ቦታዎች እያሉ አዲስ አበባ ላይ የባህል ማእከል? የወላይታ ታሪክ አዲስ አበባ ላይ???? ግልጽ አይደለም እንዴ!!! ክክክክክክክ

  Horus
  Senior Member
  Posts: 19421
  Joined: 19 Oct 2013, 19:34

  Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

  Post by Horus » 10 Jun 2021, 13:05

  Guest 1 (ethioash)

  ለምን አትተወኝም? አንተ ግዙፉን የወገኖችህ የትግሬ ችግር ላይ ብታተኩር ይበልጥ ትከበራለን! የጉራጌን ጉዳይ ለጉራጌዎች ተውልን! እያረረ እየተንጫረረ ያለው ያንተ ድስት ነውና!

  Guest1
  Member
  Posts: 1822
  Joined: 28 Dec 2006, 01:02

  Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

  Post by Guest1 » 10 Jun 2021, 13:26

  Guest 1 (ethioash)
  ጉራጌ የሆነ ሰው ሁሉ ለጉራጌ የሚጠቅም ይሰራል እያልክ ነው? በጉራጌ ጉዳይ ሌላው አያገባውም ነው? አረ ባክህ? ክክክክክክክክክክክክክክክክክክክ
  ይህ አስተያየት የሚሰጥበት መድረክ ነው።
  የሚጠቅመውን መውሰድ። የማይጠቅመው መተው።  Post Reply