Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member
Posts: 19331
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

Post by Horus » 10 Jun 2021, 22:38

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጉራጌዎችን ለመፎገር ሁለት ጉራጌኛ ቃላት እንኳን በትክክል ለማለት አልቻለችም !! የተምቢ (የተንቢ) አለች1 ከዚያ ደሞ በላለዲ ዬምጣ ለማለት ስትሞክር ተሳሳተች ። አስተማሪዋ ያደረገው ስህተት ይመስለኛል ።

በሰባት ቤት ዪተምቢ የሚለው በክስታኔ ዬምጣቢ ይሏል። እንዲያውም ድሮ ዬተምቢ (ዬተንቢ) የሚለው የምተቢ ነበር የሚባለው ። የቃሉ አባባል አስቸጋሪ ስለሆነ የተምቢ፣ የተንቢ ተባለ ። የቃሉ ጥሬ ትርጉም እንኳን ደህና መጣህ! ይምጣብኝ! እንኳን መጣህልኝ፣ መጣህብኝ ማለት ነው !!

በላለዲ ዬምጣ ማለት ሲያጥር ነው ዬምጣቢ ወይም ዬተምቢ (ዬተንቢ) የሆነው !


Horus
Senior Member
Posts: 19331
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

Post by Horus » 11 Jun 2021, 13:35

መቼም ያዲሳባ ሰው አይሰለቸው! ይህው በዚህ ሳምንት ብቻ በቀን አንድ የልማትና ባህል ማጠቃለያ የሚባል የብልጽኛ ፓርቲ የምርጫ ፕሮፓጋንዳ እየተጋትን ነው። ህዝባችን ግን የወንዝ ዉሃ ነው የሚጠጣ !


Horus
Senior Member
Posts: 19331
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

Post by Horus » 11 Jun 2021, 17:17

ጉራጌ ነጋ ጠባ ለመጣው መሪ መዘፈንና የነሱን ዲስኩር መስማት ሳይሆን ይህን አይነት ራስ ገምቢነት ባህሉን መመለስ ነ ያለበት ! ኬር !!

Horus
Senior Member
Posts: 19331
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

Post by Horus » 11 Jun 2021, 18:05

መቼም ይህ የሰሞኑ የሺመልስ አብዲሳና የጉራጌ ፒፒ ፓርቲ ሰዎች ሽር ጉድ በነገው ምርጫ ኢዜማ ጉድ እንዳያደርጋቸው ፈርተው ነው ክል መለስ እንደሆነው ማለት ነው።

ዞሮ ዞሮ በምርጫው ማግስት ወይ የጎሳ ክልልሎች ይፈርሳሉ ወይ ጉራጌ የራሱን ክልል ያቆማል ። ይህ የማይቀር ነው !! ጉራጌ በቅቶታል በነዚህ ዎያኔና ደሞ አሁን በብልጽግና መታለል !


Horus
Senior Member
Posts: 19331
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

Post by Horus » 12 Jun 2021, 15:34

የዚህ ዘፈን ዘፋኝ (የዚ ደርስ ደራሲ) ማን እንደ ሆነ ባላቅም ድምጹ የሃይሉ ፈረጃን አይመስልም። ይህ ዜማ በነአብራሃም ወልዴና ሙሉ ባንድ በደንብ ታሽቶ ከቪዶዮ ጋር ቢሰራ እጅግ እጅግ ውብ የሆነ ቱባ የጉርጌ ሜሎዲ፣ የጉራጌ እንግርጉሮ ነው !! የጉራጌኛ ዘፋኞች ችግር የሚዚቃ ባህላችን በሙዚቃ ህግጋት መሰረት አለመቀመራቸው ነው። ኬር


Horus
Senior Member
Posts: 19331
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

Post by Horus » 12 Jun 2021, 17:10

እኔ ይህን ሃሳብ ብዙ ግዜ ደጋግሜ ብዬዋለሁ ። ጉራጌ በየግዜው ከሚነሱ አገር አቀፍ ፓርቲዎች ውስጥ አጃቢ ከመሆን አልፎ የራሱ አላማ፣ የራሱ ፋይዳ፣ የራሱ ፐርፐዝ እና የራሱ እስትራተጂ መርምሮና ቀርጾና ይህ ነው የሚባል የጉራጌ አጀንዳ ከሌለው የዉሃ ላይ ኩበት ይሆናል ።

ጉራጌ የሚፈልገው የጉራጌ ሕዝብ አንድነት፣ እድገት፣ በልጽኛ፣ ትብብር፣ መገስገሻ ድርጅት ነው። ሁሉንም የጉራጌ ሕዝብ የሚያቅፍ፣ ሁሉንም የጉራጌ ሕዝብ ጉዳዮችን የሚያስተናግድ የጉራጌ ሕዝብ እድገት ድርጅት መፈጠሩ የግድ አስፈላጊ ነው።

የእድገት ድርጅት ለምን? የውክልና ድርጅት ለምን?

አንድ ህዝብ ራዕይና አጀንዳ፣ እስራተጂና ግብ ከሌለው እንደ ህዝብ ጠፊ ነው ።

አጭር የመላ ጉራጌ አጀንዳ ...

የጉራጌ ሕዝብ ቢያንስ የሚከተሉት 4 አላማዎች አሉት።

አንደኛ፣

ጉራጌ አንድነቱ የጠነከረ፣ የተረጋጋ፣ ሴራው የጸና፣ ጠንካራ ሕዝብ መሆን መስራት፤

ጉራጌ ነጻ፣ ዲሞክራሲ፣ ፍትህ፣ እኩልነት የጸናበት ራስ ገዝ ማህበረስብ እንዲሆን መስራት፤

የጉራጌ ሕዝብ በኢኮኖሚ የበለጸገ፣ በትምህርት በቴክኖሎጂ በሳይንስ በጥበባት የዳበረ የላቀ እንዲሆን መስራት፤

ጉራጌ በፈጠራ፣ በኪነት፣ በስነት የዳበረ ለኢኮሎጂው ደህንነት የቆመና በመንፈሳዊነት በኬርነት የጸና ባህል ወይም ካልቸር እንዲኖረው መትጋት ናቸው

ጉራጌ የራሱ የሆነ በራሱ ለራሱ የሆነ የእድገት እና ውክልና ድርጅት ያስፈልገዋል።

ሁለተኛ፣

በማነኛውም ማዕከላዊ መንግስት ውስጥ የሚወከልበትም ሆነ የሚካፈልበት የራሱ መወከያና ራሱን ማስተዳደሪያ ድርጅት ያስፈልገዋል። ይህም ማለት ጉራጌ በአንድ የብልጽኛ ፓርቲ ወስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ግዥ ፓርቲዎች እንደ ኢዜማ ባሉት ውስጥም መወከል አለበት ።

ብልጽግና ለጉራጌ ምን ያደርጋል? ኢዜማ ለጉራጌ ምን ያደርጋል እያልን መፈተን ና በስራቸው መመዘን አለብን።
Last edited by Horus on 12 Jun 2021, 23:19, edited 1 time in total.


Horus
Senior Member
Posts: 19331
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው

Post by Horus » 13 Jun 2021, 14:11

የኢዜማ ፓርቲ በጉራጌ ሕዝብ ከተመረጠ ለጉራጌ ምን ፋይዳል አለው? ምን ፕላን አለው? ምን ጥቅም አለው? ፖለቲካ ማለት ይህ ነው! ለጉራጌ ሕዝብ ኢዜማ ከብልጽግና የተሻለ ምን ፕላን ይዟል?

Horus
Senior Member
Posts: 19331
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል፤ የብሄር ድርጅት ተልዕኮ እድገትና ባህል ነው፤ ብልጽግና ወይስ ኢዜማ?

Post by Horus » 16 Jun 2021, 19:34

የ1987ቱ እንዳይደገም እጅግ ፈርተዋል። ለ30 አመት ተረስቶ የዉሃ ጉድጓድ ያልተቆፈረለት ጉራጌ በሁለት ሳምንት ውስጥ የተገባለትን ማባበያ (ማታለያ) ልብ በሉ!

አንድ፣ ሺመልስ አብዲሳ አንድ ቀን ብድግ ብሎ የጉራጌኛ ቋንቋ ፕሮግራም በኦኤማኤን ላይ ከፈትኩ አለ ። ለነገሩ አንድ ጉራጌ ዞር ብሎ የሚያየው የሚሰማው ነገር አይደለም ። እኔ አንድ ቀን እንኳ ከፍቼው አላቅም!

ሁለት፣ ሺመልስ አብዲሳ በኦሮሞ ወጪ አንድ ጥ/ ቤት ሊሰጠን መሰረተ ድንጋይ አስቀመጠ!

ሶስት፣ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ የጉራጌ ማዕከል ማሰሪያ መሬት ለመስጠት ቃል ገባች! ልብ በሉ በአዲስ አበባ ከአማራ ቀጥሎ ያለው የህዝብ ብዛት ጉራጌ ሆኖ ሳለ ወያኔ ግ ን ጉራጌን ለ27 አመት ሲበታትን ማለት ነው ።

አራት፣ የጉራጌ ብልጽኖች በወልቂጤ ታላቁ ሩጫ አዘጋጁ !

አምስት፣ ታከለ ኡማ የመጀመሪያው የሆነ የማዕድን ፋብሪካ በአበሽጌ ጉራጌ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ!

ስድስት፣ አቢይ አህመድ በጉራጌ የክልል ጥያቄ ላይ ለ3 አመት ሲቀልድ ከርሞ በቀደም ጉራጌዎቹ በቤተ መንግስቱ አጠገብ ሲዘፍኑ በራሱ ጋባዥነት ብቅ ብሎ የተምቢ፣ ዬምጣቢ፣ በላለዲ ዬምጣ አለ!

ይህ ሁሉ የሆነው አንድ ወር ባልሞላው ግዜ ነው !

እንግዲስ በመላ ኢትዮጵያ ያሉት ጉራጌዎች ስንቱ ህሊናቸውን ስንቱ ለማባበያው ድምጽ እንደ ሚሰጡ የሚታይ ይሆናል! ለነገሩ ፖለቲካ ሁሉ ይህን መሰል የማባበያ ጨዋታ ነው ፣

የብልጽግናዎች ብቸኛ አላማ በግልጽ ይታወቃል፤ ስልጣን፣ ገንዘብ፣ ዝና፣ ና ክብር ፍለጋ ነው !!

Post Reply