Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30681
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የአሜሪካ ፖሊሲ በሱዳን ውስጥ ያለበት ቀውስ! ሱዳን በአመጽና ወታደራዊ አገዛዝ መሃል!!

Post by Horus » 08 Jun 2021, 13:48

ሱዳን በጄነራሎች ቁጥጥር ስር ያለች አገር ነች ።

ያሜሪካ አላማ የሱዳን ሚሊተሪ አንድ ማድረኛ የሲቪል መንግስቱን ማጠንከር ነው ። ግን ሚሊተሪው በሲቢል ስር ከገባ ወንጀላ ጄኒራሎች ይያዛሉ፣ የጄኔራሎች ሃብትና ሃይል ይመታል ። ስለዚህ ሚሊታሬም አንድ አይሆንም፣ አንድ ከሆነ መፈንቅል አድርጎ የመንግስት በላይ እንጂ ከሲቪል ስር አይገባም ።

የሲቪል ሚሊታሪ ፍጥጫው ሁለት ዉጤት ያመጣል ፤ አንዱ አንዱ የሚሊታሪው ክንፍ ከሲቪል ጋር አብሮ ሌላውን ክንፍ ይመታል ። ይህ የጦሩ እርስ በርስ ጦርነት ከህዝባዊ አመጹ ጋር ይያያዛል ።

ሕዝቡ ካሸነፈና ያው በደጋፊው የጦር ክንፍ ጥገኛ ከሆነ ሱዳን በግድቡ ላይ ያላት አቋም ያው አሉታዊ ይሆናል ። ግን ወታደሩ በህዝቡ አመጽ ሳቢያ ከተከፋፈለና ጄኒራሎቹ ከተወገዱ የሱዳን አቋም በግድቡ ላይ አዎንታዊ ይሆናል ።

ግ ን ግብጽና አሜሪካ ለጽጥታ ሲሉ የሚደግፉት ጄኒራሎቹን ስለሆነ የሱዳን ሚሊታሪ አንድነት ቢፈጥርም የህዝቡ አመጽ ጸረ አሜርካ፣ ጸረ ግብጽና ጸረ ጄኒራሎች ይሆናል ።

ይህ ሁሉ ኢትዮጵያ ግድቡን ለማጠናቀቅ ግዜ ይሰጣል ።

ይህን ሁሉ ቀውስ በቀላሉ ለመፍታት ኢትዮጵያ አቢይን ደግፋ ሱዳን ኢትዮጵያ አፍቃሪ መንግስት እንዲኖር መስራት ነበረባት ። አሁንን ሌላ አማራጭ የላትም ።

አሚርካ ሱዳን እና ግብጽ ኢትዮጵያ ላይ እንዲነሱ ከደረገች ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ሆነ ቀጠናውን የማመስ ችሎታ ስላላት !!!!

ባለም ላይ 4 አይነት መፈንቅለ መንግስት የሚመጣባቸው መንገዶች አሉ ።
አንድ፣ ሚሊታሪው የሲቪል መንግስቱን በድርጅት፣ ዘመናዊነት ፣ ብሎታ ብልጦ ሲገኝ መንግስትን ለማዘመን ብለው መፈቅል ያደርጋሉ።

ሁለት፣ ሚሊታሪው ድርጅታዊና እልውናውን ለማፍረስ የወታደሩና የአዛዦቹን የኖሮ ዋስትና አደጋ ላይ ሚያደርስ ስራ በሲቪሉ መንግስት ከታሰበ ሚሊተሪ ድርጅታዊ ተቋማዊ ህይልውናውን ለመጠበቅ መፈንቅል ያደርጋል።

ሶስት፣ ግለሰብ ጄኒራሎች ለስልጣን፣ ሃብት ፣ ዝና ሲሉ ተከታይ ሰራዊት አዘጋጅተው መፈንቅል ያደርጋሉ ።

አራት ፣ ሕዝብ በአመጽ ተነስቶ አሮጌውን መንግስት ሲያወርድ በዝቡ ውስጥ ያለው የፖለቲካና የጎሳ ክፍፍል በሚሊታሪውም ውስጥ ይነሳና የሲቪሉ አመጽ ብቻውን መንግስት ማቆም ሲያቅተው ልክ እንደ ኢትዮጵያ 1966 ግዜ ሕዝብ ደጋፊ ሚመስል መፈንቅል ይደረጋል ።

በዛሬ ሱዳን በቁጥር 2፣ 3፣ 4 ያሉት ሁኔታዎች አሉ ። ለምሳሌ የጃንጀዊቱ ጄኔራል የራሱና ጥቅም ለመጠበቅ የፈጥኖ ደራሽ ህልውናን ይጠብቃል። አል ቡህራን በቁጥር 2 ና 3 መሰረት መሪ መሆን ይፈልጋል። ግብጽም አሜርካም ይደግፉታል ።

አራተኛ መፈንቅል በሲቪሉ መንግስት ዙሪያ ያለ ነው። ሃምዶግ ጸረ ህዝብ ሆኖ ከቀጠለ ወይ የበታች ኦፊሰሮች ከህዝብ አብረው ጄኒራሎቹንና ሃሞድኝ ያስወግዳሉ ወይም ሃምዶግ ከወታደሩ ጋር ሆኖ የህዝቡን አመጽ ይመታል ።

ዞሮ ዞሮ ሱዳን ወይ ወደ ሬቮሉሽን ወይ ወደ ወታደራዊ አገዛዝ ነው የምትሄደው ።

Last edited by Horus on 08 Jun 2021, 19:36, edited 3 times in total.

Aba
Member
Posts: 4018
Joined: 15 Apr 2011, 17:52

Re: የአሜሪካ ፖሊሲ በሱዳን ውስጥ ያለበት ቀውስ

Post by Aba » 08 Jun 2021, 14:19

Too bad, UAE has fled the scene of the crime.

Horus
Senior Member+
Posts: 30681
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአሜሪካ ፖሊሲ በሱዳን ውስጥ ያለበት ቀውስ

Post by Horus » 08 Jun 2021, 14:33

ባለም ላይ 4 አይነት መፈንቅለ መንግስት የሚመጣባቸው መንገዶች አሉ ።
አንድ፣ ሚሊታሪው የሲቪል መንግስቱን በድርጅት፣ ዘመናዊነት ፣ ብሎታ ብልጦ ሲገኝ መንግስትን ለማዘመን ብለው መፈቅል ያደርጋሉ።

ሁለት፣ ሚሊታሪው ድርጅታዊና እልውናውን ለማፍረስ የወታደሩና የአዛዦቹን የኖሮ ዋስትና አደጋ ላይ ሚያደርስ ስራ በሲቪሉ መንግስት ከታሰበ ሚሊተሪ ድርጅታዊ ተቋማዊ ህይልውናውን ለመጠበቅ መፈንቅል ያደርጋል።

ሶስት፣ ግለሰብ ጄኒራሎች ለስልጣን፣ ሃብት ፣ ዝና ሲሉ ተከታይ ሰራዊት አዘጋጅተው መፈንቅል ያደርጋሉ ።

አራት ፣ ሕዝብ በአመጽ ተነስቶ አሮጌውን መንግስት ሲያወርድ በዝቡ ውስጥ ያለው የፖለቲካና የጎሳ ክፍፍል በሚሊታሪውም ውስጥ ይነሳና የሲቪሉ አመጽ ብቻውን መንግስት ማቆም ሲያቅተው ልክ እንደ ኢትዮጵያ 1966 ግዜ ሕዝብ ደጋፊ ሚመስል መፈንቅል ይደረጋል ።

በዛሬ ሱዳን በቁጥር 2፣ 3፣ 4 ያሉት ሁኔታዎች አሉ ። ለምሳሌ የጃንጀዊቱ ጄኔራል የራሱና ጥቅም ለመጠበቅ የፈጥኖ ደራሽ ህልውናን ይጠብቃል። አል ቡህራን በቁጥር 2 ና 3 መሰረት መሪ መሆን ይፈልጋል። ግብጽም አሜርካም ይደግፉታል ።

አራተኛ መፈንቅል በሲቪሉ መንግስት ዙሪያ ያለ ነው። ሃምዶግ ጸረ ህዝብ ሆኖ ከቀጠለ ወይ የበታች ኦፊሰሮች ከህዝብ አብረው ጄኒራሎቹንና ሃሞድኝ ያስወግዳሉ ወይም ሃምዶግ ከወታደሩ ጋር ሆኖ የህዝቡን አመጽ ይመታል ።

ዞሮ ዞሮ ሱዳን ወ ወደ ሬቮሉሽን ወይ ወደ ወታደራዊ አገዛዝ ነው የምትሄደው ።

Post Reply