Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

መልካም ዜና ለአዲስ አበባ ወጣት!! የአሮሚያ ከልል መንግስት ስራ አጥ የሆነውን የአዲስ አበባ ወጣትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ዘመናው የጫት መሸጫ ሱቆች ሊገነባለት ነው!!

Post by Wedi » 08 Jun 2021, 07:13

የአሮሚያ ከልል መንግስት ስራ አጥ የሆነውን የአዲስ አበባ ወጣትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ዘመናው የጫት መሸጫ ሱቆች ሊገነባለት ነው!! :P :P

“ ኦሮምያ ክልል አዲስ አበባን ጨምሮ በ4 ከተሞች ዘመናዊ የጫት የገበያ ማእከል እያስገነባ ነው።”
***********************
ያረጁ የቡና ዛፎችን በአዲስ የመተካት እና እንዲሁም የቡና ልማትን በአዳዲስ የክልሉ አካባቢዎች እያሰፋ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ።

የክልሉ ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ነገሩኝ ሲል ካፒታል ጋዜጣ እንደዘገበው በክልሉ ቡና የሚመረትባቸው ዛፎች እስከ 40 አመት የቆዩና ምርታማነታቸው በእርጅና እየቀነሰ በመሆኑ ምርቱን በስፋት አሳድጎ ገበሬውን ተጠቃሚ ለማድረግ እና የውጭ ምንዛሬ ግኝቱን ለማስፋት ከፍተኛ የቡና ችግኝ ተከላ ከሁለት አመት ወዲህ በክልሉ እየተደረገ ነው ብለዋል። ለአብነትም በ2011 እና 2012 የክረምት ወቅቶች በቅደም ተከተላቸው 800 እና 900 ሚሊየን የቡና ዛፍ ተከላ ተከናውኗል ብለዋል።

በመጪው የክረምት ወቅትም 1.1 ቢሊየን የቡና ዛፍ ተከላ ለማድረግ ተዘጋጅተናል በማለት አክለዋል።

ሌላው የውጭ ምንዛሬ ምንጭ የሆነውን ጫት ምርት ለማሳደግ እና ዘርፉን ከህገወጥ ደላሎች ጣልቃ ገብነት በማፅዳት አርሶ አደሩ ተጠቃሚ የሚሆንበት አሰራር እየተዘረጋ ነው ያሉት አቶ ሽመልስ በዚህም ዘመናዊ የጫት ምርት ማሸጊያ እና ማቆያ ያካተቱ የገበያ ማእከላት በአወዳይ፣ በዴሳ እና አዲስ አበባ እየተገነቡ መሆኑን ጠቅሰው ተጨማሪ መሰል ማእከል በድሬዳዋ ወደ ስራ ይገባል ብለዋል።

ምንጭ፡-#Capital /ካፒታል ጋዜጣ/


Please wait, video is loading...