Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Y3n3g3s3w
Member
Posts: 125
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

ኢትዮጵያን ለማድከም የብሔር/የጎሳ ፖለትካን ማለምለም !

Post by Y3n3g3s3w » 07 Jun 2021, 11:29

ኢትዮጵያ እየተደነቃቀፈችም ቢሆን ወደ ትልቅ መዳረሻ እየተጓዘች ነዉ:: ስኬቷ ግን የሚወሰነዉ በሀገር ዉስጥም ሆነ ከሀገር ዉጭ በምንኖር ኢትዮጵያዊያን ነን በምንል ህዝቦቿ ሁለገብ ድጋፍና ፅናት ይሆናል:: በተለይ በዚህ በምርጫ ትኩሳት ሰሞን እያንዳዳችን የማንኛዉ ብሔር; ፖለቲካ ፓርቲ አባል; ደጋፊና አመራር አካል ብንሆንም ሀገሪቱ ለጀመረችዉ ጉዞ ስኬታማነት ወሳኙ ሁሉም ከብሄሩ; ፖለቲካ ፓርቲዉ; ከግል ጥቅምና ፍላጎት በፊት የሀገሪቱን ሕልዉና ማስቀደም ሲችል ብቻ ነዉ::
ከብሄር በፊት ሁላችንም የሰዉ ልጅ ፍጡር መሆናችንን ካላስቀደምንና በብሄር ተቧድነን እርስ በርስ መላተማችንን ካላቆምን ሁሌም ዉድቀታችንን ለሚሹ መሳሪያ ከመሆን ያለፍ በየፊናችን አንድ ስንዝር መራመድ ከቶ አይቻለንም::
ባሁኑ ሰዓት ሀገሪቱ ላይ ፊትለፊት የተጋረጠባት ትልቁ ወቅታዊ ፈተናና ሁሉም በሚባል ደረጃ የዉጭም የዉስጥም ሀገሪቱ ስኬታማ አንዳትሆነ የሚሹ ኃይሎች ሁሉ በፅኑ እየሰሩበት ያለ ነገር ቢኖር ሀገሪቱ የተረጋጋ መንግስት እንዳይኖራት ማረግ ነዉ::
ለዚህ ደሞ የመጀመሪያዉ ትኩረታቸው ምርጫ ማስተጉአጎል ሲሆን ሁለተኛውና በጣም አደገኛዉ ደሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በማንኛዉ መንገድ ማስወገድ ይህ ደሞ በመፈንቅለ መንግስት ወይም በኃይል ካልተቻለ በግድያም ጭምር ሊሆን ይችላል::
በርግጥ ይሄን መንግስት በተለይ የደህንነቱ መዋቅር አደጋዉን በበቂ ሁኔታ ተገንዝቦ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያረጋል ብዬ አምናለሁ ነገር ግን ህዝቡም ይሄን ተገንዝቦ በማንኛዉም ጎራ ብትሰለፉም; ፓስፖርታቹ ላይ የማንኛውም ሀገር ስም ቢፃፍበትም; በልባቹ ኢትዮጵያዊ ነን ብላቹ የምታምኑ ሁሉ ለመንግስት አይንና ጆሮ ሆነን ሀገራችንንና መንግስታችንን ለማፍረስ እየተንደረደሩ ካሉ ሁሉ መጠበቅ ይኖርብናል:: ይሄን የምናረገዉ ለኢትዮጵያ ብለን እንጂ ለአብይ ወይም ለብልፅግና ፓርቲ እያሽቃበጥን እንዳልሆነ በቅጡ ልንገነዘብ ይገባል::
በግሌ ምርጫዉን በተመለከተ ማንኛዉ ሀገሪቱ የጀመረችዉን ተስፋ ሰጪ ግስጋሴ ለማስቀጠል ብቁ ዝግጅት ያለዉ ኃይል ቢያሸንፍ እመርጣለሁ:: በአሁኑ ሰዓት ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠዉ ጉዳይ ግን የምርጫ ዉጤት ሳይሆን የጠቅላይ ሚኒስትሩና ሌሎቹም የለዉጥ አመራሮች ደህንነት ነዉ:: ለምን? ለሚለዉ መልስ ለማግኘት በጣም ቀላል ነዉ: 360 ድግሪ በጠቅላይ ሚኒስትሩና ዙሪያቸዉ ላይ የሚወርደውን የተቃዉሞ ዉርጅብኝ ማጤን ከበቂ በላይ ነዉ::
ይሄ በድጋሜ እለዋለሁ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም ለብልፅግና ፓርቲ ማሽቃበጥ ነዉ የሚል ሰዉ ካለ እዉነት እዉነት እላችሁዓለሁ እሱ አስመሳይና ሌባ ሰዉ መሆን አለበት::


BE WARE OF THE DEVIL!!

ኢትዮጵያን ወደስኬት ለማድረስ;
የብሔርና የጎሰኛነት ፖለቲካን ቀስ በቀስ መደርመስ::


TheManWhoSawTomorrow

Y3n3g3s3w
Member
Posts: 125
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

Re: ኢትዮጵያን ለማድከም የብሔር/የጎሳ ፖለትካን ማለምለም !

Post by Y3n3g3s3w » 09 Jun 2021, 14:44

ኢትዮጵያ እየተደነቃቀፈችም ቢሆን ወደ ትልቅ መዳረሻ እየተጓዘች ነዉ የምለዉ ለዚህ ነው

እንቅፋቶች/የጎጥ ፖለቲከኞች እባካቹ ለዶር አብይ መንግስት እድል ስጡት ከ 5-10 ዓመት; ተጨማሪ እንቅፋት ሆናቹ የበለጥ አታደናቅፉት


Post Reply