ከነዚህ ሁለት ፓርቲዎች ምልክቱና ማንነቱን በትክክል ያጣጣመ የቱ ፓርቲ ነው?
ኢዜማን እንውሰድ ። የዚህ ፓርቲ ምልክት የፍልስፍናው ቁልፍና እምብርት የሆነው ጽንሰ ሃሳብና ፍሬ ነገር ፍትህ ነው፤ እኩለት ነው ፤ እውቀት ነው ። እውቀት ነጻነት ነው። የኢዜማ ምክልክት በብዕር (እውቀት) ላይ የቆመ ሚዛን ነው፣ በነጻነት ላይ የቆመ ፍትሃ ነው። ባንድ ቃል የፖለቲካና የሶሻል ፍልስፍናውን በምልክቱ ሙሉ በሙሉ የገለጸ የኢዜማ ፓርቲ ነው ።
ብልጽግናን እንውሰድ። ብልጽግና ማለት ማደግ፣ መጨመር፣ መተለቅ፣ በላይ በላይ መደመር ማለት ነው ። በመሰረቱ የኢኮኖሚ ጽንሰ ሃስብ ነው ። ባለጸጋ መሆን፣ ሃብታም መሆን ከአምፖል ጋር ምን ያገናኘዋል?
አምፖል (አምፕ) ማለት የኤሌክትሪክ መቁጠሪያ ነው ፤ እሱም በአንድ ሰኮንድ አንድ ኮሎምብ የኤሌክትሪክ ከረንት ማለት ሲሆን የህን የፈለሰፈው አንድሬ መሪ አምፔር የተባለው ፈረንሳይዊ ነው ። ስለዚህ አምቦል ማለት የአንድ ፈረርሳያዊ ሰው ስም ነው።
ስለዚህ የብልጽግና አላማ የኤሌክትሪክ ፓርቲ ወይም ያባይ ፓርቲ ወይም የግድብ ፓርቲ ለማለት ተፈልጎ ቢሆን ኖሮ ምልክቱ ትክክል ይሆን ነበር ። ኤሌክትሪክ ሃብት ነው፤ ብልጽግና ሃብት ነው።
ነገር ግን የብልጽግና አምፖል በርቷል፣ ሊባል የተሞከረው ብርሃን ነው! ብርሃን የሚመጣው ከአምፖሉ ፣ እንደ ፊኛ ከተነፋው የመስተዋት ቅል ሳይሆን በአምፖሉ ውስጥ ካሉት ሽቦዎች መሞቅ ነው ። ይህ የመጀመሪያው ግዙፍ የብልጽግና ስህተት ነው!
ብልጽግና የሚያወራ ስለብርሃን ነው ወይስ ስለኤሌክትሪክ?
ስለ ኤሌክትሪክ ቢሆን፣ ስለ ግድብ ቢሆን ምናልባት ትርጉም ይኖረው ነበር። ግን ስለ ብርሃን ከሆነ ደሞ ትልቁ፣ ገናናው የኢትዮጵያ ጽንሰ ሃስብና ጽንሰ ነገር ጧፍ አለ! ሻማ አለ! ኩራዝ አለ! ችቦ አለ! ሌላም ሌላም !!
ብርሃን ደሞ ከብልጽግና ጋር እጅግ የራቀ ሜታፎር ስለሆነ ኮሚኒኬሽን የማያውቅ ሰው የቀረጸው ሃሳብ ነው ።
የብርሃን ሜታፎር ትርጉም እውቀት ነው ። እውቀት (ትምህርት) ደሞ የብልጽግና ህሳቤ ፍሬ ነገር ወይም ኤሰንስ አይደለም ። ስለዚህ አምፖል በጥሬ ትርጉሙ ሆነ በምሳሌነት ሜታፎሩ ከብልጽግና የማይገናኝ ምልክት ስለሆነ ነው አሁን የፓርቲ ካድሪውዎች ስለሻማ የሚያወሩት ።
የብርሃን ሜታፎር ይበልጥ አግባብ ያለው ከኢዜማ አላማና የፓርቲ ምልክት ጋር ነው ። በኢዜማ የፓርቲ አርማ ውስጥ ያለው ብዕር የሚያመለክተው እውቀትን ነው ። እውቀት ብርሃን ነው! ብርሃን እውቀት ነው። ይህ ነው ትልቁ የዚህ ምርጫ አንዱ አስገራሚ የሂሳቤ መዘባረቅ !!
Language Matters !!