Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በጄኖሳይድ እና በ ethnic cleansing እየተከሰሰ ያለው የአማራ ሚልሻ ከትግራይ ክልል ይውጣ ማለት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት አይደለም

Post by sarcasm » 18 May 2021, 08:30

በጄኖሳይድ እና በ ethnic cleansing እየተከሰሰ ያለው የአማራ ሚልሻ ከትግራይ ክልል ይውጣ ማለት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት አይደለም።

አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ አብሮ ለመኖር እያለ፣ ለነገ ብሎ፣ በይሉኝታ የሚያልፈው ነገር ይበዛል።
ወደሮኞቻችን ይህ ባይገባቸውም ወይም እያወቁ ባይቀበሉትም፣ እኛ ሁላችን በዚህ የህዝባችን የቻይነት ስነልቦና ተገድበን፣ ከምንናገረው፣ የማንናገረው ይበልጣል።ከምን ፅፈው፣ የማን ፅፈው ይበልጣል።

በተቃራኒው ግን፣ ዓይናቸውን በጨው ታጥበው፣ ቅንድባቸውን ተላጭተው፣ ሁሉን የሰብዓዊነት ሞራል ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሄርን የቻይነት ድንበር ጥሰው፣ የኢትዮጵያን ህዝብ እያመሱ ያለት የአማራ ዘረኛ ቡድኖች ግን፣ ይሉኝታ ብሎ ነገር፣ የሰው የሰብዓዊነት ሞራል ልክ ብሎ ማሰብ፣ ወይም እግዚአብሄር ምን ይለናል የሚል ነገር በጭራሽ ያልፈጠረባቸው ጉዶች ናቸው።

ዛሬ፣ ዛሬ ደግሞ፣ የአገር ውስጡ ሸፍጥ አልበቃቸው ብሎ፣ ድንበር ዘለው ፈረንጆችንም አይናችውን ጨፍኑ እናሞኛችሁ እያሏቸው ይገኛሉ።
ይህ ሸፍጠኛ እና ዘረኛ ቡድን በአለም አቀፍ ደረጃ የሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ስም ሳያጠፉ፣ ይህን ሞራለ ቢስ ኃይል አደብ ማስገዛት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ፣የአማራ ህዝብ ጭምር፣ ግዴታ ነው።

ለምሳሌ የኢትዮጵያ (የአማራ ክልል ማለት ይቻላል) ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የአማራ ሚልሻን ከትግራይ ክልል አውጡ መባላችን በኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባት ነው ብሎ የሚያዜማት የውሸት ነጠላ ትርክትንበ እንይ። ትናንትም በሰጡት የፕሬስ መግለጫ ደግመውታልና።
ከዋናው መሰረታዊ ጥያቄ እንነሳ።

የአማራ ሚልሻ ማን ነው?

የአማራ ሚልሻ ማለት፣
1) በአማራ ዘረኝነት እና የበላይነትን በኢትዮጵያ ለማስፈን የተቋቋመ፣

2ኛ) ይህን ዓላማ ለማሳካት ደግሞ ከ500 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጠላቴ ነው የሚለውን የኦሮሞ ህዝብን ማሸነፍ ግዴታው እንደሆነ ተነግሮት የተመሰረተ እና የሰለጠነ፣

3ኛ/ የአማራን እርስት ከምዕራብ እና ከደቡብ ትግራይ ማስመለስ የዚህ ዘረኛ ሚልሻ ግልፅ ዓላማ መሆኑ ተነግሮት ወደ ትግራይ የዘመተ፣

4ኛ/ የምንልክ ብርጌድ ወዘተ እያለ በኦሮሞ እና በጉሙዝ ህዝብ ላይ በፌዴራል እና በአማራ ክልል መንግስት ተልዕኮ ተሰጥቶት ህዝብ እየፈጀ ያለ፣
በኢትዮጵያ ምድር የተቋቋመ ብቸኛ ዘረኛ እና ፋሽስት ሚልሻ ነው።

ይህ እውነታ ደግሞ በጄኔራል አሳምነው ፅጌ እና በአቶ አበረ አዳሙ ከሺህ ጊዜ በላይ የተነገሩን፣ ንግግራቸውንም በመንግስት እና በማህበራዊ ሚዲያ ሁላችንም የሰማነው፣ ማንም የማይክደው፣ እውነት እና ሃቅ ነው።

በሌሎች ክልሎችስ የተቋቋሙ የክልል ሚልሻዎችን ከዚህ ምን ለያቸው የሚል አይጠፋም።
የአንድም የክልል ሚልሻ ከአማራ ክልል ሚልሻ ጋር የሚመሳሰል፣ ድንበር ዘለል፣ የአንድን ብሄር የበላይነት ለማረጋገጥ የሚል ዓላማ እና ግብ ኖሮት የተቋቋመ የክልል ልዩ ሚልሻ የለም።

ይኸውም፣ በሌሎች አከባቢ የተቋቋሙት ልዩ ሚልሻዎች የየክልሉ ገዥ የፖለቲካ ድርጅቶች በህግ እና ሰላም ማስከበር ስም የህዝብ ማፈኛ እና መጨቆኛ መሳሪያዎች አድርገው የሚጠቀሙባቸው እንጂ እንደ አማራ ልዩ ሚልሻ በብሄር የበላይነት እና ዘረኝነት ላይ የተቋቋሙ ፋሽስት ሚልሻዎች አይደሉም።

የትግራይ ጦርነት ደግሞ ምንም "የህግ ማስከበር ጦርነት" ተብሎ የዳቦ ስም ቢወጣለትም፣ መጀመሪያም እንደገመትነው፣ በትግራይ ህዝብ ማንነት እና ከኢትዮጵያ ምድር የማንነት ፖለቲካን(ከአማራ ማንነት በስተቀር) ማጥፋት በሚል ግልፅ ዓላማ ላይ ተመስርቶ የተከፈተ ጦርነት ነው።

ይህ ደግሞ እኛ ያልነው ነገር ሳይሆን ሁሉም የአማራ ዘረኛ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ሙሁራን አንድም ሳይቀሩ፣ የተናገሩት እና ንግግራቸው በግልፅ በየ መህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጩ የአደባባይ ምስጥሮች ናቸው።

ጦርነቱ ደግሞ ብሄር ተኮር መሆኑን ጥሩ ማሳያው ደግሞ "ትግሬ፣ ትግሬን አይወጋም"፣ በሚል ግልፅ የኢትዮጵያ መከላከያ ፖሊሲ፣ "በኢትዮጵያዊነት ስነ ልቦና" ላይ ተገነባ በሚባለው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያሉት ትግሬዎች፣ በበብሄር ተለይተው፣ በጦርነቱ እንዳይሳተፉ መከልከል ብቻ ሳይሆን ተለይተው መታሰራቸው ግልፅ ምስክር ነው።

ይህ ዓይነት ብሄርን መሰረት ያደረገ ጦርነት እና የመንግስት አቋም ደግሞ 30 ዓመታት በፈጀው የሻቢያ ጦርነትም ሆነ 17 አመታት በፈጀው የትግራይ ጦርነት ወቅት በቀደሙት የኢትዮጵያ መንግስታት በስራ ላይ የዋለ አዲስ ፖሊሲ ነው።

በዚህ በቀደሙት የኢትዮጵያ መንግስታት ጦርነቶቹ አገራዊ ናቸው የሚል እምነት ስለነበራቸው፣ ትግሬዎች እና ኤርትራዊያን የኢትዮጵያ መንግስት መከላከያ ኃይል አካል ሆነው ህወሃት እና ሻቢያ ላይ ይደረጉ በነበሩት ጦርነቶች ላይ ተሳትፈዋል።

የአሁኑ ግን በይዘቱም ሆነ በትርክቱ አገራዊ ጦርነት ሳይሆን የአማራ የበላይነት መንግስት ለመመስረት እየተደረገ ያለ ብሄር ተኮር ጦርነት ነው።
ደጋግሜ ሳስበው የሚያሳዝነኝ አብይ አህመድ ስልጣን ላይ እቆያለው በሚል ተስፋ፣ የአገሩን ፖለቲካ ባለማወቅ በገባበት ቁማር ተደልለው፣ የኦሮሞ እና የሰፊው ደቡብ ወታደሮች እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በዚህ ጦርነት መሳተፋቸው ነው።

እዚህ ጋ በኢትዮጵያ መከላከያ ውስጥ እያገለገሉ ያሉት የአማራ ወታደሮች ከትግራይ ይውጡ የማንለው በዚያ "ኢትዮጵያ" በሚለው ውሸት መታለል ፈልገን እንጂ በአማራ ዘረኞች በሁሉም ደረጃ የሚካሄደው ፖለቲካ ውሉ ጠፍቶን እንዳልሆነም መታወቅ አለበት።

ወደ አማራው ሚልሻ እንመለስ።

በግልፅ ዓላማ እና ግብ የተደራጀው የአማራ ሚልሻ ትግራይ የዘመተው አራት የፖለቲካ ዓላማዎችን አንግቦ ነው።

አንደኛ፣ ህወሃትን በማጥፋት እና የትግሬን ስነ ልቦና በመስበር፣ ከአማራ ብሄር የማንነት ፖለቲካ በስተቀር የብሄር ማንነት ፖለቲካን ከትግራይ እና ከመላው ኢትዮጵያ ለማጥፋት።

ሁለተኛ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ትግራይን በመያዝ፣ የአማራን እርስት ለአማራው በማስመለስ የትግሬ ተወላጆችን ከዚህ አከባቢ ማጥፈት። (ይህ ለአማራ ሚልሻ የተሰጠ ግዴታ ነው በምዕራብ ትግራይ በአንድ ሚልዮን የትግራይ ተወላጅ ላይ ethnic cleansing እንዲፈፀም ያደረገው።)

ሶስተኛ፣ ከትግራይ ጦርነት መልስ፣ ትግሬን ካሸነፍን ሌላው ገብስ ነው ባሉት መሰረት በመላ ኢትዮጵያ የአማራ ዘረኛ ቡድኖች የሚመሩት፣ የአማራ የበላይነት ጦርነት በወሎ፣ በቤኒ ሻንጉል እና በኦሮሚያ ጦርነቶች ከፍቶ ሰላማዊ ሰዎችን እየፈጀ ያለ ኃይል ነው።

አራተኛ፣ አዲስ አበባን እና ሙሉ ሸዋን ይዞ የአማራ የበላይነት መንግስት በኢትዮጵያ ለማቋቋም ተልዕኮ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ያለ ኃይል ነው።

ታዲያ ይህን በወንጃል ተፀንሶ፣ በወንጀል ተወልዶ፣ ወንጀል እየሰራ ያለን ኃይል ነው የኢትዮጵያ መንግስት ከትግራይ አላወጣም እያለ ያለው።

ይህን ሁሉ ሴራ አብይ ሚዲያ ስለማይከታተል፣ ቢዚ ስለሆነ አያውቅም የሚል ልኖር ይችላል።


አብይ የሚያውቃቸውን እውነታዎች እንመልከት።

አንደኛ፣ አብይ፣ የአማራ ክልል ከትግራይ ክልል የግዛት ይገባኛል ጥያቄ እንዳለው እያወቀ፣ የአማራን ምልሻ ወደ ትግራይ በኢትዮጵያ መከላከያ ታዝሎ እንዲገባ መፍቀድ አልነበረበትም። ጉልበት የቀን ጉዳይ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ አይሆንም።

ሁለተኛ፣ አብይ፣ የአንድን ክልል ሚልሻ ወደ ሌላ ክልል የመላክ በህገ መንግስቱም ሆነ በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን እንዳሌለው ያውቃል። አብይ የፌዴራል ጦር ኃይሎች አዛዥ እንጂ የክልል ሚልሻዎች አዛዥ አይደለም።

ሶስተኛ፣ አብይ የአማራ ክልል አመራሮች እና የፖለቲካ ድርጅቶች ጦርነቱ ለአማራው የአማራ እርስት ለማስመለስ እና የብሄር ማንነት ፖለቲካ አጥፍቶ የአማራ የበላይነት መንግስት በኢትዮጵያ መመስረት እንጂ እርሱ እንደሚለው "ህግ ለማስከበር(አብይን ስልጣን ላይ ለማቆየት)” የገቡበት ጦርነት ያለ መሆኑን ያውቃል።

አራተኛ፣ አብይ የአማራ ሚልሻ በትግራይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሞ ምዕራብ ትግራይ እና ደቡብ ትግራይን ወሮ መያዙን ያውቃል።

ስለዚህ አብይ ሁሉንም ባያውቅ እና ከላይ ከተጠቀሱት አራት ነጥቦች አንዱን እንኳን ቢያውቅ የአማራ ሚልሻን ወደ ትግራይ መላክ አልነበረበትም። ከላከም ማስወጣት አለበት።


ሌላው መልስ የማይሻው ነጥብ የአሜርካ ፕሬዚደንት የስቴት national guards ያዝ የለም የምትል የሞኝ ወሬ ነች። ሁለቱን አገር የሚያመሳስል ምድራዊ ምሳሌ የለም።ሰው ይስቅባችኋል እና የማታውቁትን አታውሩ።
ስለዚህ የአማራ ክልል ምልሻ ከትግራይ ክልል መውጣት ብቻ ሳይሆን መፍረስ እና እስከ አሁን ለሰራው ወንጀል ለህግ መቅረብ ያለበት ኃይል መሆኑ ታውቆ ይህ ወሬ መቆም አለበት።

https://www.facebook.com/birhanemeskel. ... 7616085854