Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ጎጃም ክ/ሃገር ውስጥ ኣምቦ ይካተት ነበር በብሄር ፌደራሊዝም ሲዋቀር ግን የኣንቦ ነዋሪ ኦሮሞ ስለነበረ ኦሮምያ ክልል ውስጥ ተካተተ እና ባንተ ኣባባል ኣንቦ ኣማራ ክልል ነው ልትለኝ ነው?

Post by sarcasm » 17 May 2021, 17:32

መንግስት ምን እየሰራ ነው? - ተጻፈ በሰሎሞን ወልደገሪማ ፡ የአብይና የብልጽግና ደጋፊ ትግራዋይ

ህግ ማስከበር ተብሎ መከላከያን ተከትሎ መሬት በሃይል የያዘው የኣማራ ክልል ከፌደራል መንግስት እውቅና ውጭ መሬት ለእንቨስትመት በሚል ሲቸበችብ ሃይ ካልተባለ ነገ ለዳግም ግጭት ማስገባት በር እንደ መክፈት ኣይሆንም ወይ ?

ይህ ኣካሄድ ፈፅሞ ወደ ለየለት የእርስበርስ ግጭት የሚያስገባ መረን የለቀቀ ህገወጥ ኣካሄድ ነውና #እውነት_ከኣማራ_ክልል የወጣ ደብዳቤ ከሆነ ሃይ ሊባል ይገባል። እደግመዋለሁኝ #እውነት_ከኣማራ_ክልል የወጣ ደብዳቤ ከሆነ ሃይ ሊባል ይገባል።

ኣሁንም እንደ ትላንቱ ደጋግሜ እንደምነገረውና እንደምፅፈው ጥያቄ ካለ ባለድርሻ ኣካላትና መንግስት ህጉን በሚፈቅደው መልኩ እንዲፈተሽ እንዲሰራ መድረኮች ብናዘጋጅ እንጂ በዚህ መልኩ ደም ከማፋስስ ውጭ የሚያመጣው ለውጥ ኣይኖርም።

በርግጥ እኔ ብዙ ህወሓት ከትግራይ መሬት ኣሳልፎ የሰጠው
በወሎ እስከ ኣልወሃ ምላሽ
በጎንደር በኩል እስከ ሊማሊሞ
በኣፋር በኩል እስከ በራሕለ ድረስ ጥያቄ ኣለኝ ግን በሃይል ሳይሆን ህጉን በሚፈቅደው መልኩ እንዲፈተሽ ነው ፍላጎቴ ከዛ ውጭ ግን ማንም በሃይል መሬት መውረር ስያስብ ምላሹ የግዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የከፋ ሊሆን እንደሚችል መገመት ኣይከብድምና ለህዝባችን ሰላም ስንል ሰከን ማለቱ ብቻ ነው የሚያዋጣው።
በጦርነት እና በሃይልማ ውጤቱ ለዘመናት እያየነው መጥተናል ፤ በዚህ ጉዳይ ነገሮች በሰለማዊ እንዲፈቱ የኣንበሳ ድርሻ መውሰድ ያለበት የኣማራ ሊሂቃን ፣ ፓለቲከኞች ፣ ኣክቲቪስቶች ናቸው የሚል የፀና እምነት ኣለኝ።
ስለዚህ ኣሁን ቆም ብላቹ ኣስቡ ለህዝቡ ሰላም ሲባል።

ይሄ መሬት መቼ ነው የኣማራ ክልል የነበረ? ኣማራ ክልልስ ከ1983 በፊት የት ነበር?
ኣንድ ምሳሌ ኣጭር ልንገርህ ለምሳሌ ጎጃም ክ/ሃገር ውስጥ ኣምቦ ይካተት ነበር በብሄር ፌደራሊዝም ሲዋቀር ግን የኣንቦ ነዋሪ ኦሮሞ ስለነበረ ኦሮምያ ክልል ውስጥ ተካተተ እና ባንተ ኣባባል ኣንቦ ኣማራ ክልል ነው ልትለኝ ነው?

Robel Mitiku
Solomon Weldegerima የተፈናቀለው ሕዝብ አይመለስ ማን አለ? መመለስ እንዳለባቸው ምንም ጥርጥር የለውም። ግን እኔ የምለው በ25 እና 30 ዓመት የህወሓት ሴራ ፖለቲካ ውጤት ዘንድሮም ታሪክ መገልበጥ የለበትም ነው።

Solomon Weldegerima
Robel Mitiku ውጡ እየተባሉ እየተገደዱ ነው የተፈናቀሉት BZW ይሄ መሬት መቼ ነው የኣማራ ክልል የነበረ ኣማራ ክልልስ ከ1983 በፊት የት ነበር
ኣንድ ምሳሌ ኣጭር ልንገርህ ለምሳሌ ጎጃም ክ/ሃገር ውስጥ ኣምቦ ይካተት ነበር በብሄር ፌደራሊዝም ሲዋቀር ግን የኣንቦ ነዋሪ ኦሮሞ ስለነበረ ኦሮምያ ክልል ውስጥ ተካተተ እና ባንተ ኣባባል ኣንቦ ኣማራ ክልል ነው ልትለኝ ነው?


Please wait, video is loading...