Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7984
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

በኦርምያ ክልል በአማራ እና በክርስቲያኖች ላይ ቀይ ሸብር ግድያ በይፋ ተጀመር!! የአማኑኤል ወንድሙ አገዳደል !!

Post by Wedi » 13 May 2021, 17:21

በኦርምያ ክልል በአማራ እና በክርስቲያኖች ላይ ቀይ ሸብር ግድያ በይፋ ተጀመር!! የአማኑኤል ወንድሙ አገዳደል!!

የአማኑኤል ወንድሙ አገዳደል !!

… እደግመዋለሁ ይህ ዕድሜው ገና 18 ዓመት እንደሆነ የተነገረለት ኦርቶዶክሳዊ ባለማዕተብ ወጣት አማኑኤል ወንድሙ ከበደ ይባላል። ለወንጀሉ ዋነኛው ምክንያት የዐማራ ስም ያለው የኦሮሞ ኦርቶዶክስ መሆኑ ነው። በምዕራብ ወለጋ በደምቢ ዶሎ ከተማ ነዋሪ የሆነ ታዳጊ ወጣትም ነው። በተጠና ነገር ግን በድንገተኛ በሚመስል መልኩ የኢትዮጵያ መንግሥት መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይሎችና የከተማዋ ፖሊሶች በጋራ ወደ መኖሪያ ቤቱ በመሄድ በወንጀል እንደሚጠረጠር ነግረው በሕግ ቁጥጥር ስር እንዳዋሉት ነገሩት። አዋሉት። ከዚያ ወቅጠው፣ ደብድበው የምነነግርህን እየተናገርክ ከተማዋን ዙር አሉት። እነሱ ወታደሮች እንዲህ በል፣ እንዲያ በል እያሉ ሽጉጥ አስይዘው ወደሚገድሉበት አደባባይ እየነዱት እንደምታዩት እያዋከቡ ወሰዱት። (ሊያመልጥ ሲል እግሩን በጥይት መተን ነው የያዝነው የሚሉት እንግዲህ ይሄንን ነው)

ከዚያ…

" ከዚያም ከተማዋን ሲያዞሩት ውለው አምጥተውት አደባባዩ ላይ በማሰር ህዝቡ የከተማው ህዝብ ሁሉ እንዲሰበሰብ እና እንዲመለከተው አደረጉ። ህጻናትም እስከመጨረሻው በዚያው ነበሩ። ወላጅ እናቱ፣ የትምህርት ቤት ጓደኞቹ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ጓደኞቹ ሁሉ በዚያው ቆመው እንዲያዩት ተደረገ። የመንግሥት ወታደሮች ስለሆኑ የሆነ የሚጠብቁት ትእዛዝ ያለ ይመስልም ነበር። ከአሁን አሁን ወደ ጣቢያ ይወስዱታል ተብሎ ቢጠበቅ፣ ቢጠበቅ፣ 3 ሰዓት ሙሉ ምንም የለም። ህዝቡ ግን አደባባዩን ሞልቶ ይጠብቅ ነበረ።

ከዚያ…

" ከዚያም ከ3 ሰዓታት በላይ በታሰረበት እንዲቀመጥ ተደርጎ ህዝቡ በደንብ ሲወጣ ከተቀመጠበት አንስተውት ቪዲዮ ቀርፀው ጨረሱ። በመሃል ግን ወታደሮቹና ፖሊሶቹ ይቁነጠነጡም ነበረ። ከዚያ…
" ከዚያም በመጨረሻ መሳሪያ ከታጠቁት ወታደሮቹ ውስጥ አንዱ ወደ አማኑኤል በመጠጋት ወደዛ ዙር ብሎ መሳሪያውን አቀባበሎ "እንዴት ተመተህ ብትሞት ይሻልሃል?" ብሎ አማኑኤልን ጠየቀው። አማኑኤልም ምንም ተስፋ፣ ምንም አማራጭ፣ የሚደርስለት አካል እንደሌለ ሲያውቅ። መሞቱ፣ መገደሉን ሲረዳ ለገዳዩ ወታደር በአደባባዩ ላይ ጎንበስ ብሎ ተኛለት። ከዚያም ሁሉም ህዝብ ቆሞ እያየ ወታደሩ የአማኑኤል ጭንቅላቱ ላይ ጥይት ቶኮሰ። ከአማኑኤል ጭንቅላትም ላይ የሆነ ነጭ ነገር ከጭንቅላቱ ውስጥ ወደ ላይ ተረጨ።… በአከባቢው የነበሩት ወታደሮችም ወዲያው ህዝቡን አባረሩ። የአማኑኤል እናትም እዚያው በቆሙበት ጭቃ ላይ ሲወድቁ ወታደሮቹም እናትየውን እዛው መሬቱ ላይ ከልጃቸው አስከሬን ፊት ቀጠቀጧቸው... ህዝቡም ተበተነ። አስከሬኑም እንዳይነሣ አደሩጉ… ።"

ከዚያ …

… ከዚያ የሽመልስ አብዲሳው የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ የደስታ መግለጫ በይፋ ይዞ ወጣ። ቀይ ሽብር በወጣቱ አማኑኤል ላይ መወሰዱንም በኩራት ተናገረ። ይሄን ድርጊት ከጥቂቶች በቀር ያወገዙ የሉም። የብልጽግና አክቲቪስቶች በሙሉ ባላየ፣ ባልሰማ ዝም ብለዋል። የኢሳት ገሌ ጋዜጠኞችም ይሄን ትተው ማኅበረ ቅዱሳን ላይ አፋቸውን ሲከፍቱ አምሽተዋል። 30 ሚሊዮኗ ሠራች ማለት ነው።
" ገሌው ኢሳት ይሄና ይሄን መሰሉ የኦሮሞ ብልጽግና ግፍ አይታየውም። ቅርሻታም ሁላ አለ አጎቴ ሌኒን…


Please wait, video is loading...

tekeba
Member
Posts: 1504
Joined: 17 Dec 2013, 03:03

Re: በኦርምያ ክልል በአማራ እና በክርስቲያኖች ላይ ቀይ ሸብር ግድያ በይፋ ተጀመር!! የአማኑኤል ወንድሙ አገዳደል !!

Post by tekeba » 13 May 2021, 18:01

Wedi terewae Axgame. You are desperate and fuxxced up big time living in an illusion. Have you noticed the media propaganda is declining about the small and destitute kilil. Ignorant the WEST is using you for their poletical game, they don't care about you, mother fuxcker, do you get it

Post Reply