Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ትግራዋይ እርስ በእርሱ እየተጫረሰ ነው!

Post by Ejersa » 12 May 2021, 09:46

ከአክሱም ትንሽ ወጣ ብላ የምትገኝ ውቕሮ ማራይ የምትባል ከተማ ጁንታው ከፈረጠጠ ቦሃላ ህዝብ አገልግሎት እንዲያገኝ በውቕሮ ማራይ የተሾሙት ሁለት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር ሹመኞች በአሸባሪ የህወሓት ቡድን ተገደሉ። እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ የጊዚያዊ አስተዳድር ሃላፊዎች በአሸባሪው ህወሓት ቡድን ተገድለዋል ታፍነዋል።

ትግራዋይ ለትግራዋይ ወንድሙ መግደሉ ቀጥሏል ፤ ትግራዋይ እርስ በእርሱ እየተጫረሰ ነው። ህዝብ ስላስተዳደሩ መግደል ጁንታው የትግራይ ህዝብ ያለ መሪ ለማስቀረት እና የትግራይ ህዝብ እንዲበተን ካለው ጥላቻ የሚነሳ ነው። ጁንታው ሁሌም በተጋሩ ላይ ይጨክናል የራሱ ወገን በመግደል በማሰቃየት ከበርሃ ጀምሮ ይዞት የመጣ መጥፎ ጭካኔ ነው።

በዚህ ባረጀ ስልት እና ሴራ የሚሸማቀቅ ሰው የለም ነገር ግን የትግራይ ህዝብ ራሱ በራሱ እንዲበላላ የሚያደርግ ቀይ ሽብር እንዲወለድ የሚያፋፍም ፀያፍ ተግባር ነው።

ጁንታው ህዝብ የሚያስተዳድሩ፣ በሃሳብ የተለየ ሰው በመግደል ትግራዋይ እርስ በእርስ እያተጋደለ ይገኛል።

እኔ ከሌለሁ ማንም ትግራይ አይመራትም የሚል የአህያ አስተሳሰብ በፍፁም አይሳካም ነገር ግን ዋጋ ያስከፍላል።