Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ሰበር ዜና፣ አሸባሪው ህወሓት ክሱዳን መሬት ጥቃት ለመሰንዘር ሞክሮ ተድምስሷል!!!!

Post by Ejersa » 12 May 2021, 09:19

ከሱዳን በሁመራ በኩል የገቡት አሸባሪዎች ብዛት 300 የሚጠጉ ነበሩ።በተለለያየ አቅጣጫ ነበር ለመግባት የሞከሩት 150 የታጠቁና 150 ጀሌዎች ናቸው፣ እስከ ትናንትና ድረስ 93 ሲደመሰሱ 95 ተማርከዋል።በጠቅላላው 188!! አሁን ቀሪዎቹ ደጋጉም በተባለው አካባቢ በከበባ ውስጥ ሲሆኑ እጃቸውን እንዲሰጡ ተጠይቀዋል። ከተደመሰሱትና ከተማረኩት ውስጥ አብዛኞቹ በሱዳን የስደተኛ ካምፖች ውስጥ ተጠልለው የነበሩ ታዳጊ ወጣቶች ናቸው።

በነገራችን ላይ እነዚህ በከበባ ውስጥ የገቡት ታጣቂዎች አሁን ላይ አዛዥ/አመራር የላቸውም። አመራሮቻቸው ገቢ ተደርገዋል።ገቢ ያልተደረጉት ደግሞ አንገት አልባ ሆነዋል!! አንገታቸው ተቆርጦ የተገኙ አስከሬኖች ቁጥር 4 ደርሷል። ኮሎኔል ባህረ፣ ሻለቃ ባየው ሺበሺና ሻምበል ተክለወይኒ ደግሞ ከነ አንገታቸው ተማርከዋል።

Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

Re: ሰበር ዜና፣ አሸባሪው ህወሓት ክሱዳን መሬት ጥቃት ለመሰንዘር ሞክሮ ተድምስሷል!!!!

Post by Hameddibewoyane » 12 May 2021, 09:37

:lol: :lol: :lol: :lol:
Ejersa wrote:
12 May 2021, 09:19
ከሱዳን በሁመራ በኩል የገቡት አሸባሪዎች ብዛት 300 የሚጠጉ ነበሩ።በተለለያየ አቅጣጫ ነበር ለመግባት የሞከሩት 150 የታጠቁና 150 ጀሌዎች ናቸው፣ እስከ ትናንትና ድረስ 93 ሲደመሰሱ 95 ተማርከዋል።በጠቅላላው 188!! አሁን ቀሪዎቹ ደጋጉም በተባለው አካባቢ በከበባ ውስጥ ሲሆኑ እጃቸውን እንዲሰጡ ተጠይቀዋል። ከተደመሰሱትና ከተማረኩት ውስጥ አብዛኞቹ በሱዳን የስደተኛ ካምፖች ውስጥ ተጠልለው የነበሩ ታዳጊ ወጣቶች ናቸው።

በነገራችን ላይ እነዚህ በከበባ ውስጥ የገቡት ታጣቂዎች አሁን ላይ አዛዥ/አመራር የላቸውም። አመራሮቻቸው ገቢ ተደርገዋል።ገቢ ያልተደረጉት ደግሞ አንገት አልባ ሆነዋል!! አንገታቸው ተቆርጦ የተገኙ አስከሬኖች ቁጥር 4 ደርሷል። ኮሎኔል ባህረ፣ ሻለቃ ባየው ሺበሺና ሻምበል ተክለወይኒ ደግሞ ከነ አንገታቸው ተማርከዋል።

Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: ሰበር ዜና፣ አሸባሪው ህወሓት ክሱዳን መሬት ጥቃት ለመሰንዘር ሞክሮ ተድምስሷል!!!!

Post by Ejersa » 12 May 2021, 13:38

ትህነግ ተአምር ይሰራልኛል ብሎ ሲጠብቀው የነበረው ኃይል ወልቃይት ላይ ቀርቷል!

ትህነግ ተስፋ ሲያደርግበት የቆየው ሱዳን ውስጥ ስልጠና ሲወስድ የነበረውን ኃይል ነው። ይህ ኃይል ሰሞኑን በወልቃይት በኩል ወደ ትግራይ ሊያልፍ ሲል ድል ሆኖ መንገድ ላይ ቀርቷል። የወልቃይት ጠገዴ ገበሬ፣ ከአማራ ልዩ ኃይልና ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር ሆኖ መንገድ ላይ አስቀርቶታል።

በኮ/ል ባሕረ መሪነት፣ በሻምበል ተክላይ ምክትል አዛዥነት፣ ኢንስፔክተር ባየሁ ስለሽና ሌሎችም አስተባባሪነት ከሱዳን ወልቃይትን አቋርጦ ትግራይ ለመግባት ያቀደው ኃይል በዓከር ላይ በተደረገ ጦርነት አብዛኛው ተገድሏል። ከተረፉት መካከል አብዛኛዎቹ እጃቸውን ሲሰጡ፣ የተወሰኑት ከበባ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

ከ304 በላይ የሰው ኃይል የነበረው ይህ ቡድን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ ለብሶ ወደትግራይ ሊሻገር ሲል ነው የተመታው። ከሱዳን መድሃኒት፣ ስንቅና መሳርያዎችን ይዞ ወደ ትግራይ ሊሻገር አስቦ እንደነበር ነው የተገለፀው። ቡድኑ ከ230 በላይ ዘመናዊ የመገናኛ መሳርያዎችን ይዞ መገኘቱም ተገልፆአል።

የሚገርመው ይህ ኃይል መመታቱን ቀድመው የሰሙት የትህነግ አክቲቪስቶች፣ ትህነግ ሰራዊቱ ላይ ድል እንደተቀዳጀ አድርገው ዜና ሲሰሩ ሰንብተዋል።

ትህነግ የመገናኛ መሳርያ እጥረት ገጥሞታል። የመድሃኒት እጥረት ገጥሞታል። ይህ ኃይል ትግራይ ቢደርስ ተአምር ይሰራልኛል ብሎ እየጠበቀ ነበር። ወልቃይት ላይ ቀርቷል።

Post Reply