Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
temari
Member
Posts: 3743
Joined: 28 Dec 2014, 21:18

Live Iftar from Meskel Square

Post by temari » 11 May 2021, 11:52


kerenite
Member
Posts: 4441
Joined: 16 Nov 2013, 13:15

Re: Live Iftar from Meskel Square

Post by kerenite » 11 May 2021, 13:06

Haha..

Yesterday or was it day before yesterday yeislamochu chihot or slogan in mesqel or abiyot adebabay or whatever you call it was: abiy leba naw..juntaw yishalal. Perhaps as a consequence we are noticing today a U-turn, the abi and his regime are doing all the best they can in order to satisfy them and hence assure them that they are better than the junta.

Hey! Does it have something to do with the forthcoming so-called miricha? Lol

ZEMEN
Member
Posts: 2482
Joined: 27 Jun 2011, 14:37

Re: Live Iftar from Meskel Square

Post by ZEMEN » 11 May 2021, 13:22

temari wrote:
11 May 2021, 11:52
I hate copy cat BS. I don't know why they need to get out on this massive way during this Covid danger. Because Egypt did it, it does not mean it had to be done in Ethiopia, why?

Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Live Iftar from Meskel Square

Post by Horus » 11 May 2021, 13:26

ተማሪ
እኔ ሲጀመርም ያልኩት ይህን ነበር። ዘመናዊነት። ሴኩላር የፖለቲካ ማህበረ ሰብ ማለት ይህ ነው። ያም ማለት የተለያዩ እምነት እና ሃስተሳሰብ ያላቸው ቡድኖች ማህበሮች የራሳቸውን ጉዳይ እየኖሩ ያንድ አገር፣ ያንድ መንግስት፣ ያንድ ስልጣኔ ህዝብ መሆን ማለት ነው።

ሙስሊሞች መስቀል አደባባይ ምግብ በሉና ምንድን ነው የግጭት ምንችነቱ? ሙስሊምና ክርስቲያን የሚበላው በግ አንድ በግ ነው። ክርስቲያን በስመ አብ (በእግዚአብሄር ስም) ብሎ ያርደዋል፣ ሙስሊሙ ቢስሚላህ (በአላህ ስም) ብሎ ይርደዋል ። በጉ ግን አንድ በግ ነው ። በሬው አንድ በሬ ነው። ልብ ብለ መላ ቅርብ ምስራቅ ክርስቲያን ገበሬ ያሰባውን ሰንጋ ነው የሚበላው።

የመስቀል አደባባይ አፈርም እንዲሁ ነው። ቄሱ በስመ አብ ብሎ ደመራ ያነድበታል፣ ሙስሊሙ በስመ አላህ ብሎ ያፈጥርበታል ። ቴዲ አፍሮ በስመ አርት፣ በስመ ፍቅር ብሎ ይዘፍንበታል፣ ፖለቲከኛው በስመ መብት ወበስመ መንግስት ብሎ ይሰለፍበታል።

አበሻ ግን አንጎሉ በችግር የተዋቀረ አስቸጋሪ ሰው ስለሆነ ብቻ ነው ይህ ሁሉ ድራማ በ21ኛ ዘመን !!!

ነገር ግን በመንግስት ወጪ መደረጉ ፍጹም ስህተት ነው ። አሁን መንግስት ፖለቲካና ሃይማኖት አንድ አደረገ ማለት ነው ።

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: Live Iftar from Meskel Square

Post by Guest1 » 11 May 2021, 14:44

የነበረው አሁንም ያለው ችግር አልተነገረም። የችግሩ መነሻ ከመከፋፈል የመጣ ነው። እንደ ፕሮተስታንትና ኦርቶዶክስ። ኢድ አደባባይ የተባለው ለፓለቲካ ነው። አንድነትን ሳይሆን ልዩነትን ለመገፋፋት።

ኢፍጣር ማብላት የሚባል ባህል አልነበረም። ለምን? ምግብ ይሁን ገንዘብ አንድ ሃብታም በጾም ወር ለድሃው መስጠት (alms) ግዴታው ስለሆነ። ኢድ ቀን ሁሉም እንደ አቅሙ ቤቱ ደሃ ያበላል። በመስኪድም ሆነ አካባቢው ምግብ ማብላት የሚባል አልነበረም ምክንያቱም ወሩን ሙሉ ገንዘብና ምግብ ስለሚታደል። መንገድ ላይ ምግብ ደርድሮ ማብላት አይታውቅም (አሳዛኝ ገጽታም አለው)። የአሁኑ እንደ አቤቱታም እንደ ማስታወቂያም ሳይሆን አይቀርም። በዝህ ክቀጠለ ክርስቲያኑም መንገድ እየዘጋ ጾም እንፈታለን ማለቱ የማይቀር ይሆናል። ያኔ መንግስት መክልከል አይችልም።

አደባባዩን እንደዛሬ ማክበር የሚከለክል አልነበረም። ለወደፊቱም አይኖርም። ስም ቀይሩ የሚለው ግን ተገቢ አይደለም። ሌላ ኢድ አደባባይ ቢሰራ የተሻለ ነው። በዝሁ ከቀጠለም ኢድ አደባባይ ይበሉት ክርስቲያኑም መስቀል አደባባይ ማለቱን አያቆምም። አያጣላም።

ትክክል በሃይማኖት መንግስት ጣልቃ መግባት አልነበረበትም። የለበትም።

Post Reply