Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Lakeshore
Member
Posts: 2627
Joined: 24 Jul 2018, 09:32

ምን ያደርጋል ሀገር…..?

Post by Lakeshore » 11 May 2021, 11:23

ምን ያደርጋል ሀገር…..?
ሶረኔ - መስከረም - 2011)


ምን ያደርጋል ሀገር፣ …. ምን ሊበጅ ዜግነት፣
ወልደው ካልሳሙበት፣…. ዘርተው ካልቃሙበት፣
ህጻናት በመስኩ፣…. አዛውንት በሸንጎ፣…. ደምቀው ካልታዩበት፣
እምቦሳን በጓሮ፣…. ጥገትቱን ከጨፌው፣… ታስረው ካልዋሉበት፣
ጋማ ከብቱ በመስክ፣… አውሬም በውርማ፣… ሞልተው ካልታዩበት፣
ፏፏቴው በዳገት፣… ጅረት በሸለቆ፣… ሲፎክር ካልሰሙት፣
ተራራውም በደን፣… ክምሩ ባውድማ፣…. ገኖ ካልታየበት።

ምንያደርጋል ሀገር……?

ከሰው ተወዳጅተው፣… ከሰው ተዋውለው፣…. ህይወት ካልመሩበት፣
ቅጠሉን በጥሰው፣… አፈሩንም ልሰው፣…. ቆመው ካልሄዱበት፣
አርሰው፣ አሳርሰው፣…. ነግደው፣ አትርፈው… ሐብት ካልደረጀበት፣
ከእውቀትም ጨልፈው፣… በሳይንስ ተራቀው፣… ለድገት ካልሰሩበት፣
እናቶች፣ ህጻናት፣… መበለት፣ አዛውንት፣… ካልተከበሩበት፣
ታመው ካልዳኑበት፣… አርጅተው አፍጅተው፣… ካልተቀበሩበት።
ወጥተው ካልገቡበት፣…. ሰርተው ካልኖሩበት፣
ከሸንጎው ዳኝነት፣…. ከወንበሩ ፍትህ፣…. ነጥፈው ከጠፉበት፣
መብት ሚዛን አጥቶ፣…. ስርዓት ባገር ጠፍቶ፣… እብሪት ከገዛበት፣
ዜግነት ከሀገር፣…. ማንነት ከአንድነት፣…. ሰላም ከመቻቻል፣… ከተለያዩበት፣
ባሳብ ተደራጅተው፣… ደግፈው ተቃውመው፣… ውለው ካልገቡበት፣
በልዩነት ደምቀው፣… በባህል፣ በእምነት፣… ካልተከበሩበት።

ምን ያደርጋል ሀገር……?

መውጣትና መግባት፣…. መኖርና መስራት፣… ከሚያስጨንቁበት፣
ያገር መውደድ ፍቅር፣…. ነጻነት፣ አርነት፣… ወንጀል ከሆነበት፣
ቃዬል በመንበሩ፣… ይሁዳ ከልፍኙ፣… ከሰለጠኑበት.
ዜጋው ጠላት ሆኖ፣… ዘራፊና ባእድ፣…. ተከብረው ካሉበት፣
ስደትና ረሀብ፣…. እስራትና ሞት፣…. ዳረጎት ከሆኑት፣
በስልጣን መባለግ፣…. በሀብት መንደላቀቅ፣… ገነው ከታዩበት።
የሰው ነፍስ ረክሶ፣… በየጉራንጉሩ፣…. ጭዳ ከሆነበት፣
ውንብድና ባገር፣… ሸንጎ ተቀምጦ፣… ህግ ካረቀቀበት፣
ከሐዲ በዙፋን፣… ገንጣይ ባማካሪ፣… ነግሰው ከኖሩበት፣
ጦቢያ ማለት ቀርቶ፣…. ቋንቋ፣ የዘር ሐረግ፣… ሀገር ከመሩበት.
የእብሪት ማራገፊያ፣… ያአምባገነን ቅርሻት፣… መትፊያ ከሆኑበት.

ምንስ ሀገር አለን……!

በስሟ እምንጠራት፣….ምን ወዳጅ ተጘኝቶ፣… ወገኔ የሚሉት።
ሲታመም ካላዩት፣… ሲወድቅ ካላነሱት፣… ሲሞት ካልቀበሩት፣
ሲቸገር ካልረዱት፣…. ሲራብ ካልጎበኙት፣…. ሲዳር ካላኮሩት፣
ሲበደል ሲጨቆን፣ ድምጽ ካልሆኑለት፣ እጅ ካልዘረጉለት
በሸንጎ ተሟግተው፣… መብቱን አስመልሰው፣.. ካላስከበሩለት፣
ዘምተው ግዳይ ጥለው፣… ወድቀው ተሰውተው፣…ታሪክ ካልሰሩለት፣
ውርደቱን በክብር፣….. ጥቃቱንም በድል፣… ታግለው ካልቀየሩት፣
ቢፎከር፣ ቢቅራሩ፣… ሀገር! ሀገር! ቢሉት፣… ዲስኩር ቢያበዙለት፣
ህንፃው ቢደረደር፣…አስፋልቱ ቢነጠፍ፣… ግድብ ቢሰሩለት፣
ምን ያደርጋል ታዲያ፣… ምን ያደርጋል ሃገር፣…. ያለሰው ቢወዱት።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!

Lakeshore
Member
Posts: 2627
Joined: 24 Jul 2018, 09:32

Re: ምን ያደርጋል ሀገር…..?

Post by Lakeshore » 11 May 2021, 16:04

መውጣትና መግባት፣…. መኖርና መስራት፣… ከሚያስጨንቁበት፣
ያገር መውደድ ፍቅር፣…. ነጻነት፣ አርነት፣… ወንጀል ከሆነበት፣
ቃዬል በመንበሩ፣… ይሁዳ ከልፍኙ፣… ከሰለጠኑበት.
ዜጋው ጠላት ሆኖ፣… ዘራፊና ባእድ፣…. ተከብረው ካሉበት፣
ስደትና ረሀብ፣…. እስራትና ሞት፣…. ዳረጎት ከሆኑት፣
በስልጣን መባለግ፣…. በሀብት መንደላቀቅ፣… ገነው ከታዩበት።
የሰው ነፍስ ረክሶ፣… በየጉራንጉሩ፣…. ጭዳ ከሆነበት፣
ውንብድና ባገር፣… ሸንጎ ተቀምጦ፣… ህግ ካረቀቀበት፣
ከሐዲ በዙፋን፣… ገንጣይ ባማካሪ፣… ነግሰው ከኖሩበት፣
ጦቢያ ማለት ቀርቶ፣…. ቋንቋ፣ የዘር ሐረግ፣… ሀገር ከመሩበት.
የእብሪት ማራገፊያ፣… ያአምባገነን ቅርሻት፣… መትፊያ ከሆኑበት.

ምንስ ሀገር አለን……!

በስሟ እምንጠራት፣….ምን ወዳጅ ተጘኝቶ፣… ወገኔ የሚሉት።
ሲታመም ካላዩት፣… ሲወድቅ ካላነሱት፣… ሲሞት ካልቀበሩት፣
ሲቸገር ካልረዱት፣…. ሲራብ ካልጎበኙት፣…. ሲዳር ካላኮሩት፣
ሲበደል ሲጨቆን፣ ድምጽ ካልሆኑለት፣ እጅ ካልዘረጉለት
በሸንጎ ተሟግተው፣… መብቱን አስመልሰው፣.. ካላስከበሩለት፣
ዘምተው ግዳይ ጥለው፣… ወድቀው ተሰውተው፣…ታሪክ ካልሰሩለት፣
ውርደቱን በክብር፣….. ጥቃቱንም በድል፣… ታግለው ካልቀየሩት፣
ቢፎከር፣ ቢቅራሩ፣… ሀገር! ሀገር! ቢሉት፣… ዲስኩር ቢያበዙለት፣
ህንፃው ቢደረደር፣…አስፋልቱ ቢነጠፍ፣… ግድብ ቢሰሩለት፣
ምን ያደርጋል ታዲያ፣… ምን ያደርጋል ሃገር፣…. ያለሰው ቢወዱት።

Lakeshore
Member
Posts: 2627
Joined: 24 Jul 2018, 09:32

Re: ምን ያደርጋል ሀገር…..?

Post by Lakeshore » 12 May 2021, 18:52

ስለ አላማ የሌለው ኣንኮላ ተላላኪ ኦሮሞ

"ኦሮሞ " እስካል ወያኔ ኦሮሞን መላክ እይሰለቸውም:: ወያኔ አሁንም ተመራምሮ ከጋላ የተሰራ ቦንብ ሊያመርት ይችላል

Ilmme Hateraw Galla
[/size]

Post Reply