Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

" አቡነ ዮሴፍ የቋሚ ሲኖዶስ መግለጫ አስመሰለው በግላቸው የሰጡት መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል "

Post by sarcasm » 11 May 2021, 08:20

አቡነ ዮሴፍ ያለ ቋሚ ሲኖዶስ ፈቃድ መግለጫ ሰጡ
" አቡነ ዮሴፍ የቋሚ ሲኖዶስ መግለጫ አስመሰለው በግላቸው የሰጡት መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል "
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ "ታፍኛለሁ!" ብለው ንግግር ካደረጉ በኃላ ንግግራቸው በኹለት አተያይ እየታየ የሰሞኑ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።
አቡነ ዮሴፍም ይሄን ውዝግብ ወደሚያካርር ጨዋታ ውስጥ በመግባት ቅዱስነታቸውን የሚነቅፍ ያልተጠየቁትን "የሲኖዶስ አቋም አይደለም" በማለት ሳይጠሩ ‹‹አቤት›› ብለው ለመንግሥት ሚዲያዎች መግለጫም መልከዋል። ዛሬ መግለጫውን የዘገቡት ሚዲያዎች ቅዱስነታቸው ‹‹ታፍኛለሁ›› ሲሉ ሄደው ለማናገር እንኳን ያልፈለጉ እሳቸውን ለማጥቃት ታስቦ በተዘጋጀ የቤተ ክርስቲያንን ክብር በሚያሳንስ መግለጫ ላይ ተሸቀዳድመው እየዘገቡ ይገኛል፡፡
የአቡነ ዮሴፍ መግለጫ ዋና ዓላማ በየስብሰባው የሚታዘዙለትን መንግሥት ከማስደሰት ባለፈ በንቁ ሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ የሚያመጣው አንዳችም ለውጥ የለም። የዛሬውን መግለጫ ሌሎች የቋሚ ሲኖዶስ አባላት የማያውቁት አቡነ ዮሴፍ የቋሚ ሲኖዶስ መግለጫ አስመሰለው በግላቸው የሰጡት መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
አቡነ ዮሴፍ እና ጥቂት ግብረ አበሮቻቸው ለግል አላማቸው ብለው መናገር የማይችሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን ከአቡነ ማትያስ በመነጠል ለጠ/ሚሩ የምስጋና ሽልማት ይስጡ ብለው ሽልማቱን አቡነ መርቆርዮስ ያዘጋጁት በማስመል ቤተ መንግሥት ድረስ እሳቸውንም ሽልማቱንም የወሰዱ እና በጊዜው በምዕመናኑ ዘንድ ውዝግብ የፈጠሩ ለቤተ ክርስቲያን ክብር ሲባል ንትርክ ላለመፍጠር ዝም የተባሉ መሆናቸው በዚህ አጋጣሚ ማሳወቅ እፈልጋለሁ፡፡
የቤተ ክርስቲያኗ ዋና አባት እና የመጀመሪያው ዋና መሪ የሆኑት አቡነ ማትያስ በግላቸው መግለጫ መስጠት አይችሉም ብለው እሳቸው በግላቸው መግለጫ መስጠታቸው ማንን ተማምነው እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
ከዚህ በታች ያለው ደብዳቤ በእሳቸው ተዘጋጅቶ ለመገናኛ ብዙኃን የተሰራጨ ነው፡፡
Vis Habtamu Menale
130 c
Please wait, video is loading...