Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የድምጽ መስጫ ቀን "አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል" ይችላል - ብርቱካን ሚደቅሳ [Why ወደ ኋላ? It's fishy]

Post by sarcasm » 11 May 2021, 08:05

ብርቱካን ሚደቅሳ የምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ላይ ለውጥ ሊኖር ይችላል አሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ በርቱካን ሚደቅሳ የ2013 አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ድምጽ መስጫ ቀን ላይ ለውጥ ሊደርግ እንደሚችል ተናገሩ።
የቦርዱ ሰብሳቢዋ የስድሰተኛው ሃገራዊ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን "አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል" ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።
ሰብሳቢዋ ቦርዱ በጉዳዩ ላይ እስካሁን የወሰነው ምንም ዓይነት የቀን ለውጥ አለመኖሩን አረጋግጠው፤ በመራጮች ምዝገባ እና በድምጽ መስጫ ቀናት መካከል መከናወን ያለባቸው ተግባራት መኖራቸውን አስረድተዋል።
ባሳለፍነው ቅደሜ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት፤ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚደቅሳ የሎጂስቲክ እና የደህንነት ጉዳዮችን እንደምክንያት በመጥቀስ፤ የድምጽ መስጫው ቀን "አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል ይችላል ብዬ እገምታለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።
ቦርዱ እስካሁን ድረስ ከ31 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
የምርጫ ቁሳቁሶችን ማከፋፈል፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ እና ስልጣና እንዲሁም የፓርቲዎች ግብዓት ማግኘት የሚሉት ተግባራት የመራጮች ምዝገባ ተጠናቆ እስከ ድምጽ መስጫ እለት የሚተገበሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።
"እነዚህን አይተን በሁለቱ መካከል ለማስገባት እንሠራለን። የሚያስፈልገው ነገር የሚወስደው ጊዜ ከታወቀ በኋላ አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል ይችላል ብዬ እገምታለሁ" ብለዋል።
በአዲስ አበባ እና በሌሎች ህዝብ በብዛት የሰፈረባቸው ቦታዎች የምርጫ ጣቢያ አለመኖሩን ያረጋገጡት የቦርዱ ሰብሳቡቢ "ይህ የአሰራር ክፍተት ነው። ችግር በመሆኑ ኃላፊነትም የወሰድንበትም ጉዳይ ነው" ብለዋል።
የሕዝብ ቆጠራ አለመደረጉ እና ያለው መረጃ የቆየ መሆኑ የመራጮች ምዝገባ ግምት አስቸጋሪ ማድረጉን በምክንያትነት አስቀምጠዋል።
ችግሩን ለመቅረፍ እየተሠራ መሆኑን በመጠቆም "አዲስ አበባ ላይ ብዙ ቦታዎች ላይ በተለይም ኮንዶሚኒየም አካባቢዎች ላይ ከህዝብ ቁጥር አንጻር ያለመመጣጠን ነበር። በቀረው ጊዜ ብዙ ሰው እንመዘገባል ብለን እንገምታለን። የተሻለ ምዝገባ እንጠብቃልን" ብለዋል።(BBC)

https://www.facebook.com/diretube/posts ... 1301479587
Last edited by sarcasm on 11 May 2021, 18:24, edited 1 time in total.

Selam/
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የድምጽ መስጫ ቀን "አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል" ይችላል - ብርቱካን ሚደቅሳ [Why ወደፊት? It's fishy]

Post by Selam/ » 11 May 2021, 08:21

Kichamo Komalo - That’s how she plans to handshred woyane leeches to pieces: one move forward, another backward just like sawcutting hard wood. KIFU!
sarcasm wrote:
11 May 2021, 08:05

Post Reply