ኢሳት Ethio360 ወይስ ቪኦኤ፡ "የኢትዮጵያ ህዝብ ዓይንና ጆሮ"፡ ከፓትርያርክ ማቲያስ ሮሮ አኳያ!
Posted: 10 May 2021, 05:08
ኢሳቶች ምነውሳ እኒህን የሃይማኖት አባትና፡ የሚሊዮኖች የነፍስ እረኛን፡ ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስን፡ ስለሁኔታቸው ራሳቸውን ቃለመጠየቅ ከማድረግ አፈገፈጋቹሳ፡ ኧረ ባባጃሌው! የጦቢያ ህዝብ ዓይንና ጆሮ ነን ትሉ አልነበረምን?
ምርጡ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ይሰማል ወይ? ነጻ ጋዜጠኞችና የጦቢያ ህዝብ ዓይንና ጆሮ ነን እያላችሁ፡ ትልቁ የኃይማኖት አባት መሃል አዲስ አበባ ውስጥ ሆነው፡ ችግር ውስጥ አለሁ ብለው ‘አቤት’ ሲሉ አለማየታችሁ አለመስማታችሁም፡ ኧረ ጀሮዳባ ልበስ ማለታችሁ ጭምር አያስተዛዝብምን? እንዲህ ተሆነማ ሚዛናዊነታችሁ በየትኛው ሚዛን ነው የተመዘነው? ለዜጎች መብት ነው የምንታገለው አላላችሁምን? ታዲያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶው አባት የሚሊዮኖች እረኛ ፓትርያርክ ማቲያስ ኢትዮጵያዊ ዜግነት የላቸውምን? የሃይማኖት አባቱን በመስቀለኛ ጥያቄ ወጣጥራችሁ፡ የሳቸውን የማይናወጥ ነጻ እይታ ለህዝብ ለማጋራት ባለመትጋታችሁ ያፍሪካ ቀንድ ህዝብ እየታዘባችሁ ነው።
አይፈቀድላቸውም እንጂ ቆቆቹ Ethio360 እንዲሁም ቪኦኤዎች እኒህን የሃይማኖት አባት ከመጠየቅ ወደኋላ አይሉም ነበር ቢለን እናስባለን!
ጎበዝ! ጦቢያውያን ቦለቲከኞችና ጋዜጠኞች እንዲህ አይነት ስንኩልና ወገናዊ የተዛባ አመለካከት ይዛችሁ ነው ከኤርትራ ህዝብ ጋር በኮንፌዴሬሽን ለመዋሃድ የምትቋምጡት! ድንቄም ኮንፌዴሬሽን! ዛሬ የሃይማኖት አባቶች ድምጥ ሲደፈጠጥ ዝም ካላችሁ’ማ ነገ ራሱ ሃይማኖቱን መደፍጠጣችሁ ይቀራልን?
ያዝ እንግዲህ አንዱ ለነፍሱ ሲል የጣፈውን https://mereja.com/amharic/v2/503890
እግረመንገዳችንን እኛም ለኢሳት አንድ እንቀኝላታ
"የኢትዮጵያ ህዝብ ዓይንና ጆሮ፣
'ኢሳት' ነው" ይባል ነበር ድሮ፣
እናማ ምን ሆኖ ነው ዘንድሮ፣
የፓትርያርክ ማቲያስን ሮሮ፣
ጀሮዳባ ልበስ ያለው ተንቀባሮ!!!!!