Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

አቡነ ማቲያስ በፊት እጃቸዉ እየተንቀጠቀጠ በእንባ እየታጠቡ የአማራ ጅምላ ጭፍጨፋን ለምን አወገዙ በሚል ሰበብ ጥርስ ዉስጥ ገብተዋል። አሁን አቡኑ ወገንተኛ ለማስመሰል ብልፀግና እየሰራ ነው።

Post by sarcasm » 08 May 2021, 08:13

ተጻፈ በይድነቃቸው ከበደ

“ ልጄቼ እንባዬን እያፈሰስኩ ስለ እናንተ ስቃይ አምላካችንን በፀሎቴ እየጠየኩ ነው"

“ እዉነታዉን የሚያዉቅ ያዉቀዋል። ከዚህ በፊት ጅምላ ጭፍጨፋን ለምን አወገዙ በሚል ሰበብ ጥርስ ዉስጥ ገብተዉ ከርመዋል። ቂም ተይዞባቸዉ ለአፈና ተዳርገዋል። “ ግዮን ፈንታሁን

ኦርቶዶክሳዉያን ከብልፅግና ተከፋይ አክቲቪስቶች ተንኮል ራሳችሁን አርቁ። ብፁዕ አቡነ ማቲያስን አንዱ ነቃፊ ሌላኛዉ ደጋፊ ሆኖ እንዲከፋፈሉ እያራገቡ ነዉ። ሰከን ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል። ኦርቶዶክስ ዉስጥ ፖለቲካዉን ገፍቶ በማስገባት የመሰንጠቅ ስራ ከተጀመረ ቆይቷል ።

አቡነ ማቲያስን ወገንተኛ በማስመሰል በምዕመኑ መካከል ልዩነት ለመዝራት የታቀደ ነባር ፕሮጀክት አለ። አቡነ ማተያስ ለትግራይ ብቻ ድምፅ እየሆኑ ነዉ የሚለዉ ማደናገሪያ ከብልፀግና የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ማዕከል የተላለፈ ነዉ። አቡነ ማቲያስ ከዚህ በፊት እጃቸዉ እየተንቀጠቀጠ በእንባ እየታጠቡ አባታዊ መልዕክት ማስተላለፋቸዉን መርሳት አይገባም። ቤተክርስቲያኗም ለተጎጅዎች ድጋፍ እንድታደርግ አድርገዋል። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ጠባቂዎቻቸዉ ያለእሳቸዉ ትዕዛዝ እንዲቀየሩ ተደርገዋል። የፕሮቶኮል ሀላፊያቸዉ ያለብፁዕ አቡነ ማቲያስ እዉቅና እንዲታሰሩ ተደርጓል። ከከፍተኛ ባለስልጣናት ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያና ዛቻ ደርሷቸዋል። በትልልቅ ሀገራዊ መድረኮችም እንዳይገኙ ተገፍተዋል ።

አሁን ለሌላዉ የተቆረቆሩ በመምሰል "አቡነ ማቲያስ መርጦ አልቃሽ ናቸዉ" እያሉ የሚያቀሳስሩ ተከፋይ አክቲቪስቶች በእምነቱ ተጋሪዎች አንድነት ላይ መጠራጠር ለመፍጠር የተሰጣቸዉ ስምሪት እንደሆነ ማመን ይገባል። ትግራይ ላይ እየደረሰ ያለዉን ሰብዓዊ ቀዉስ እንደ አባት ማዉገዛቸዉ ስህተት አይደለም። ነገር ግን አቀሳሳሪዎቹ ትግራይ ላይ ብቻ አወገዙ በሚል አቡነ ማቲያስ ላይ እንዲዘመትባቸዉ እየሰሩ ነዉ። እዉነታዉን የሚያዉቅ ያዉቀዋል። ከዚህ በፊት ጅምላ ጭፍጨፋን ለምን አወገዙ በሚል ሰበብ ጥርስ ዉስጥ ገብተዉ ከርመዋል። ቂም ተይዞባቸዉ ለአፈና ተዳርገዋል።

"ልጆቼ እኔ የሃይማኖት አባት ነኝ። እኔ የእናንተ ጠባቂ ነኝ። ይሁንና ከመታረድ ልታደጋችሁ አልቻልኩም። ከሞት ላድናችሁ አልቻልኩም። እኔ የጦር መሪ አይደለሁም። ገዳዮቻችሁን ለፍርድ ለማቅረብ አቅሙ ዬለኝም። በእጄ ሽጉጥ ሳይሆን መስቀል ነው የምይዘው። ልጄቼ እንባዬን እያፈሰስኩ ስለ እናንተ ስቃይ አምላካችንን በፀሎቴ እየጠየኩ ነው።" ይሄንን አባታዊ ተማፅኖ እጃቸዉ እየተንቀጠቀጠ እንባቸዉ እየፈሰሰ የተናገሩት በኦሮሚያ፣ በቤንሻንጉልና በተለያዩ አካባቢዎች እንደበግ እየተጎተቱ ለታረዱ ልጆቻቸዉ መድረስ አልቻልሁም ብለዉ ነዉ።

ያኔ አቡነ ማቲያስን ሳይቃወሙ ዛሬ ለተቃዉሞ እየተንደረደሩ ያሉ ተኩላዎችን አትመኗቸዉ። ብልፅግና ኦርቶዶክስን የማተራመስ ፕሮጀክት ነድፎ መንቀሳቀስ ከጀመረ ቆይቷል። የብልፅግናን ሀልዮታዊ የፖለቲካ እሳቤና አሰላለፍ በደንብ ለመረመረ ኦርቶዶክስ ፀረ ለዉጥ ናት ብሎ የሚያምን ድርጅት መሆኑን ይደርስበታል።

ለዚህ ፁፍ ባይሆንም ብልፅግና ርዕዮተ አለማዊ ሽፋን ይዞ ከፍ ባለ ደረጃ በኦርቶዶክስና በእስልምና ተቋማዊ አደረጃጀት ሰርጎ በመግባት በየእምነቶቹ ስር ዉጥረት በመፍጠር ለመሰንጠቅ እየሄዱበት ያለዉን መንገድ ባናቱም ግጭት እየቀሰቀሱ የሚሽነሪ ፖለቲክስን አጀንዳ ስትራቴጅካሊ በምን መልኩ እንደሚያስፈፅሙ አንድ ቀን ሰፋ አድርገን እናየዋለን። እየሰሩ ያሉት ስራ የዘፈቀደ ሳይሆን በእቅድ የሚመራ ነዉ። በሙስሊሙ በኩል መጅሊሱን በተመለከተ ነበረዉን ሰሞነኛ ጉርምርምታና ኦርቲዶክሱን የማመስ ስራ ምንጩ አንድ ነዉ።

ከፍ ሲል አማራ ክልል መስጊድ በማቃጠል፣ ኦሮሚያ ክልል ደግሞ ቤተ ክርስቲያን በማዉደም በሁለቱ እምነት ተከታዮች ስነልቦና ላይ የግጭት ፖለቲካ በማንበር ላይ የተመሰረተ ስራ በመስራት ስደትና መፈናቀል ሲገጥም ለሚሽነሪ ፖለቲክሱ መጋቢ የሆነ ታክቲካል ድጋፍ በማድረግ ምን እየተፈፀመ እንዳለም ማስታወስ ያስፈልጋል።

ይልቅ የብልፅግናን ሴራ አሜን ብሎ በመቀበል ኦርቶዶክሳዊዉ መከፋፈል ከጀመረ አቡነ ማቲያስን "ህወኃት" ናቸዉ በማለት ከፓትሪያሪክነታቸዉ አንስቶ ፓትሪያሪክ ራሴ ካላስቀመጥኩላችሁ ማለቱ አይቀርም። በጊዜ መንቃቱ ጠቃሚ ነዉ።

ተጻፈ በይድነቃቸው ከበደ
https://www.facebook.com/yidenkachew.ke ... 5004966818