Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የመስቀል አደባባይ አጠቃቀም በተመለከተ የሆረስ መፍትሄ

Post by Horus » 08 May 2021, 02:26

ለመስቀል አደባባይ አጠቃቀም ላይ የማየው መፍትሄ ይህ ነው።

(1) መስቀል አደባባይ ስሙ በፍጹም ሊለወጥ አይችልም። ደደቡ ደርግ አብዮት አደባባይ ያለ ሃይማኖት ስላልነበረው በክርስትናም በእስልምናም የማያምን አረመኔ መንግስት ስለነበር ነው ።

(2) መስቀል አደባባይ እንዳለ ሆኖ ግን ቦታው የሕዝብ አደባባይ ነው ። የፓፕሊክ እስኩየር ነው። ያ ማለት በቦታው የደመራ በአል፣ የዘፈን ኮንሰርት፣ የወታደር ሰልፍ፣ የፖለቲካ ት ዕይንተ ሕዝብ፣ ኢሪቻ ወዘተ ይደረግበታል ። ልክ የጃንሆይ ሜዳ ስሙን ይዞ ጥምቀት ይደረግበታል፣ ፈረስ ጉግስ፣ ኳስ ወዘተ እንደ ሚደረግበት ማለት ነው።

(3) ስለዚህ ሙስልሞች አፍጥር ሊያደርጉ ይችላሉ ፣ ልክ ጴንጤዎች የነሱን ኮንቬንሽን እንደ ሚያደርጉት ።

ስለዚህ የከተማው አስተዳደር ይህን የሕዝብ አደባባይ አጥቃቀም ላይ ሁሉንም የሚያስማማ ደምብ ማቅረብ አለበት ። እስከዚያ ግን የኦሮሞ አክራሪ እስላም ንቅናቄ ጉዳዩን እንዳይጠልፈው የሁለቱም እምነት መሪዎች አስቸኳይ ምክር አድረገው የሰላም መፍትሄ ማቅረብ አለባቸው እነሱ ራሳቸው መንግስት ሳይሆን ።

እኔ ብሆን ይህን ያደባባይ አስተዳደር ደንብ እስኪዘጋጅ ይህን አመት ሙስሊሙ እስታዲዮም ያድርጉ እላለሁ ። ወደፊት ግን ሁለቱ የሚከባበሩ ታላላቅ የኢትዮጵያ እምነቶች በራሳቸው ግዜ መስቀል አደባባይን ሊጠቀሙ ይገባል ። ኢሪቻ እዚያ ተደርጎ ሙስሊሙ እዚያ ማፍጠሩ ምን ልዩነት አለው።

ድሮ መስቀል አደባባይ መስገድ ፈልገው ይከልከሉ አይከልከሉ አላቅም። መስቀል አደባባይ እያለ ለምን እስታዲዮም እንደ መረጡ አላቅም። ዛሬ ለምን መስቀል አደባባይን እንደ ፈለጉ አላቅም ። ፖለቲካ ከሆነ ወዲያ ማለት ነው።

ይህም ሆነ ያ የሙስሊሙ ሙፍቲና ጳጳሱ መስማማት አለባቸው ከፖሊስና ማዘጋጃ ቤት ቀድሞ !!

ኬር ለኢትዮጵያ !

ETHIOPIA INVICTUS !!

temari
Member
Posts: 3743
Joined: 28 Dec 2014, 21:18

Re: የመስቀል አደባባይ አጠቃቀም በተመለከተ የሆረስ መፍትሄ

Post by temari » 08 May 2021, 03:33

I agree 100%. The name can’t be changed. We can’t go back to ugly derg name. But as you said it’s a public place and anybody should be able to hold an event including our muslim brothers.

Having said that the current push for holding any muslim event at mesqal square for the first time now looks to me a political move from PP. PP hopes to get muslim vote by dividing Addis Ababan residents. So don’t be surprised if you hear more frictions between the two communities until the election date.
Horus wrote:
08 May 2021, 02:26
ለመስቀል አደባባይ አጠቃቀም ላይ የማየው መፍትሄ ይህ ነው።

(1) መስቀል አደባባይ ስሙ በፍጹም ሊለወጥ አይችልም። ደደቡ ደርግ አብዮት አደባባይ ያለ ሃይማኖት ስላልነበረው በክርስትናም በእስልምናም የማያምን አረመኔ መንግስት ስለነበር ነው ።

(2) መስቀል አደባባይ እንዳለ ሆኖ ግን ቦታው የሕዝብ አደባባይ ነው ። የፓፕሊክ እስኩየር ነው። ያ ማለት በቦታው የደመራ በአል፣ የዘፈን ኮንሰርት፣ የወታደር ሰልፍ፣ የፖለቲካ ት ዕይንተ ሕዝብ፣ ኢሪቻ ወዘተ ይደረግበታል ። ልክ የጃንሆይ ሜዳ ስሙን ይዞ ጥምቀት ይደረግበታል፣ ፈረስ ጉግስ፣ ኳስ ወዘተ እንደ ሚደረግበት ማለት ነው።

(3) ስለዚህ ሙስልሞች አፍጥር ሊያደርጉ ይችላሉ ፣ ልክ ጴንጤዎች የነሱን ኮንቬንሽን እንደ ሚያደርጉት ።

ስለዚህ የከተማው አስተዳደር ይህን የሕዝብ አደባባይ አጥቃቀም ላይ ሁሉንም የሚያስማማ ደምብ ማቅረብ አለበት ። እስከዚያ ግን የኦሮሞ አክራሪ እስላም ንቅናቄ ጉዳዩን እንዳይጠልፈው የሁለቱም እምነት መሪዎች አስቸኳይ ምክር አድረገው የሰላም መፍትሄ ማቅረብ አለባቸው እነሱ ራሳቸው መንግስት ሳይሆን ።

እኔ ብሆን ይህን ያደባባይ አስተዳደር ደንብ እስኪዘጋጅ ይህን አመት ሙስሊሙ እስታዲዮም ያድርጉ እላለሁ ። ወደፊት ግን ሁለቱ የሚከባበሩ ታላላቅ የኢትዮጵያ እምነቶች በራሳቸው ግዜ መስቀል አደባባይን ሊጠቀሙ ይገባል ። ኢሪቻ እዚያ ተደርጎ ሙስሊሙ እዚያ ማፍጠሩ ምን ልዩነት አለው።

ድሮ መስቀል አደባባይ መስገድ ፈልገው ይከልከሉ አይከልከሉ አላቅም። መስቀል አደባባይ እያለ ለምን እስታዲዮም እንደ መረጡ አላቅም። ዛሬ ለምን መስቀል አደባባይን እንደ ፈለጉ አላቅም ። ፖለቲካ ከሆነ ወዲያ ማለት ነው።

ይህም ሆነ ያ የሙስሊሙ ሙፍቲና ጳጳሱ መስማማት አለባቸው ከፖሊስና ማዘጋጃ ቤት ቀድሞ !!

ኬር ለኢትዮጵያ !

ETHIOPIA INVICTUS !!

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የመስቀል አደባባይ አጠቃቀም በተመለከተ የሆረስ መፍትሄ

Post by Horus » 09 May 2021, 14:44

ኢትዮጵያ ውስጥ መቼም ችግር የመፍታት ክህሎት ደክሞ ድክሞ ሁሉም የጉልበትና የቀውስ መንገድ ይዞ የራሱን ድራማ ማሳየት ነው አላማው ።የጎሳና የሃይማኖት ፖለቲካ ነጋዴዎች አዳዲስ ጥያቄና አዳዲስ ንቅናቄዎችን በመስፍጠር የቀውስና የቅራኔ ቲያትር ይመስላቸዋል የህልውናቸው ምስክርና መግለጫ። እኔ የማውቀው ፈጣሪን የሚያመልኩ ሙስሊም ሆነ ክርስቲያን በቤት አምልኮአቸው አካባቢና ውስጥ እምነታቸውን ይፈጽማሉ እንጂ የመንገድ ላይ ቅብጥርስ እያሉ የጠብ ምንጭ እየፈለሰፉ አገርና መንግስት ማወክ ምን ይሉታል። ለምን ይህ አሁን አስፈለገ? ዞሮ ዞር አንድ ሌላ ውጥረትና የቀውስ ድራማ እንጂ ምንም የሚመጣ አዲስ ነገር የለም ። ለ30 አመት ቃል ያልተናገረው የትግሬ ቄስ አሁን ፈረንጅ ኢትዮጵያን ካረብ ጋር ሆኖ ስለ ወጠረ ተነስቶ የኢትዮጵያን ሰራዊት አወገዘ ። አሁን ደም ሙስሊሙ ተነስቶ ሌላ የውጥረት አቧራ እያስነሳ ነው። ያሳዝናል !!

Jirta
Member
Posts: 1505
Joined: 30 Sep 2018, 07:07

Re: የመስቀል አደባባይ አጠቃቀም በተመለከተ የሆረስ መፍትሄ

Post by Jirta » 09 May 2021, 17:03

በጣ የበሰለ አስተያየት ነው አሁንም ቢሆን ክርስቲያን አይሆንም ብሎ የተቃወመ የለም:: ሲያስጮኻቸው የዋለው መስቀሉ ነው:: መቼም ወደፊት መካ መዲና ጥምቀት ይከበር በሚለው ....
ሌላው ነገር ስታዲዬም እኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለ:: ስታዲየሙ የሙስሊሙ ሀገር አይደለም እንዴ:: መስቀል አደባባይ የቤተክርስቲያን ይዞታ ነው:: ካርታ አላት አነ ታከለ አስፈቅደው ነው ያለሙት:: እስላሞች ነገጊዮርጊስ እንግባ ሲሉስ? የመስቀል አደባባይ ጥያቄ ግቡ ወረራ ነው:: በጀቱ ከግብፅ ከሳውዲ ነው:: አፍሪካን በሙሉለማስለም ኢትዮጵያእንቅፊት ስለሆነቺ በዚህ መልኩ ለማዳከም ነው::

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የመስቀል አደባባይ አጠቃቀም በተመለከተ የሆረስ መፍትሄ

Post by Horus » 10 May 2021, 14:57

በቃ ይህ ነው ህዝብን መስማት ማለት!!! ኢትዮጵያ የአንድ ፈጣሪ አገር እንጂ የ10 እግዚአብሄሮች አገር አይደለችም !! ይህ የኢትዮጵያ አንድ ፈጣሪ አንዱ አላህ ይለዋል፣ ሌላው ጎድ ይለዋል፣ ሌላው ያዌ ይለዋል፣ ሌላው እዝጌር ይለዋል፣ አንዱ እግዚአብሄር ይለዋል ። መስቀል አደባባይ ሁሉም አምላኪዎች የሚበቃ ቦታ ነው ! ኬር ዬሁን ይላል ጉራጌ !!!

Post Reply