Page 1 of 1

"በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 10:35
by Revelations
Please wait, video is loading...

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 10:47
by Revelations
If that's the case, why send his body to Addis for "further testing"?


Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 11:28
by Revelations
May be not! Clearly they're still working on a plausible story line,


Please wait, video is loading...

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 11:59
by Revelations

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 12:10
by Revelations
Seyoum Teshome spilling some secrets...he is in the know of the plans...


Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 12:33
by Wedi
ከሰሞኑ አንድ የኮሚሽነር #አበረ_አዳሙ ቤተሰብ የሆነ ሰው ደውሎልኝ አበረ በአጣየው ጭፍጨፋ ሰዓት ከትእዛዝ እንዲገለል ተደርጎ እንደነበርና ምንም አይነት ውሳኔ መስጠት እንዳይችል ተደርጓል ብሎ አጫወተኝ ።

ከዚያም አበረ የያዘው ብዙ መረጃ አለው ለ Ethio 360 Media -ኢትዮ 360 ሚዲያ ሚስጥሩን ለመስጠት አስበናል ግን በሂወቱ ላይ ችግር እንዳይፈጠር ፈርተናል በማለትም አጫወተኝ።

አቶ አበረም ይህንን ስለሚያውቅ ሚስጥሩን ብሞት እንኳን ህዝብ እንዲያውቀው. በማለት በድምፅ ቅጅና በሰነድ ወደውጭ መላካቸውን ሰምቸ ነበር ።

ይሁንና የዘመኑ ሙልጭልጭ ፓለቲካ የሰማሁትን ሁሉ እንዳላምን ቢያደርገኝም ዛሬ የአቶ አበረን ማረፍ ስሰማ የሰማሁት ሁሉ እውነት መሆኑን አረጋግጫለሁ።

ለማንኛውም የአቶ አበረ አዳሙን ሂወት ያስቀጠፈው ይህ ሚስጥር የተባለው ጉዳይ በይፋ እንዲወጣና የአማራ ህዝብ አልፎም ንፁህ ኢትዮጵያዊያ ይሰሙት ዘንድ ምኞቴ ነው ‼
Please wait, video is loading...

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 12:51
by Wedi
ኮሚሽነር አበረ ከሃላፊነት የተነሳሁ የስራ ግምገማ ሳይደረግ: ድክመቴና ጥፋቴን ሳላውቀው ነው:: ስሜም ያለአግባብ ጠፍቷል:: ስለዚህ የስራ ግመገማ ማድረግ አለብን::
ይህ ካልሆነ ግን

".....በአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ ጥቅሞች ላይ የሚቆምረውን ሃይል በመረጃና ማስረጃ ለሃገሬ ህዝብ ለማጋለጥ የምገደድ ይሆናል::"

አለ:: ይህ ቁማርተኛ ሃይል መሆን አለበት ምስጢር እንዳይወጣ የገደለው:: ይህ ቆማሪ ሃይል ዛሬ ገዳይ ቢሆንም ነገ ሟች መሆኑ አይቀርም:: Political Assassination አይደለም ኢትዮጵያ ይቅርና ጠንካራ ሚዲያና ጋዜጠኞች እንዲሁም ገለልተኛ ተቋማት ባላቸው ሃገራት ላይ እንኳ ምስጢሩን ለማግኘት ይከብዳል:: ይህ የሚሆን ደግሞ በዋናነት ገዳይ ቡድኑ ስልጣን ላይ ያለ ወይም ሪሶርስ ያለው ቡድን ስለሚሆን መረጃዎችን የማጥፋት አቅሙ ከፍተኛ ስለሆነ እና ሌላ alternative reality አሳማኝ በሚመስል መልኩ አዘጋጅቶ ህዝብ ለማሳሳት መልቀቅ ስለሚችል ነው::
በዚህ በማይረባ ሴራ ውስጥ ሰዎች ሲሞቱ: ቤተሰቦቻቸው ተበትነው ሲቀሩ ማየት በጣም ልብ ይሰብራል::



***************************************************
ለክቡር አቶ ደመቀ መኮነን
ለክቡር አቶ ብናልፍ አንዷለም
ለክቡር አቶ አብርሃም አለኸኝ

ጉዳዩ፡- የሥራ ግምገማ እንዲደረግ ስለመጠየቅ:-

እኔ ኮሚሽነር #አበረ አዳሙ በ1987 ዓ.ም ጀምሮ የፖሊስ ሠራዊት አባል በመሆን በተለያዩ ኃላፊነቶች ሀገሬን ሳገለግል አማራ ጠሏ ህወሓት በአማራ ህዝብና በሀገር ላይ የምትፈፅመውን በደልና አድሏዊ አሠራር በቅርበት የማየት ዕድል በማግኘቴ ሥርዓቱን አምርሬ መታገል ጀመርኩ፡፡ ለፍትሐዊነትና ለእኩልነት የማደርገው ትግል በህወሓት ዘንድ በመታወቁ ለእስር ላለመዳረግና ትግሉንም አስፍቶ ለመታገል የፖሊስነት ሥራዬን በመልቀቅ ከሀገር ውጭ በስደት ህወሓት መራሹን መንግሥት አቅሜ በፈቀደ መጠን ስታገል ቆይቻለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብና በኢህአዴግ ውስጥ በነበሩ ለውጥ ፈላጊ አመራሮች ቆራጥ ትግልም ለውጥ መጥቶ ህወሓት በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ታሪክ ሆናለች፡፡

ለዘመናት ስታገልለትና ስመኘው የነበረው ለውጥ በሀገሬ ኢትዮጵያ በመምጣቱ እጅግ በጣም ተደስቼ ባሁበት ሰዓት የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ወደ ክልሉ መጥቼ አብሬያቸው እንደሰራና ህዝቤን ባለኝ የፖሊስነት ሙያ እንዳገለግል በተደጋጋሚ ጠየቁኝ፡፡ እኔም ህዝቤንና ሀገሬን ለማገልገል ካለኝ ፍላጎትና ሳልወድ ተገድጄ ጥያት የሄድኋትን ሀገሬን በሙያዬ ለማገልገል የአብረን እንሥራ ጥያቄውን በሙሉ ፍላጎት ተቀብዬ ከየካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የክልሉ መንግሥት በሰጠኝ ምደባ መሠረት አቅሜ በፈቀደ መጠን በቅንነትና በታማኝነት ህዝቤንና የክልሉን መንገሥት ሳገለግል ቆይቻለሁ፡፡ በዚህ የአገልግሎቴና የኃላፊነቴ ወቅትም ከላይ በሥም የጠቀስኳችሁ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች ከጎኔ ሆነው ሲያበረታቱኝና ሲደገፉኝ ስለነበር፤ለተደረገልኝ ድጋፍ እጅግ የከበረ ምስጋና አለኝ፡፡

ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሰላም መደፍረሶች ሲከሰቱ በአግባቡ እየተገመገመና የጋራ የመፍትሄ አቅጣጫ እየተቀመጠ በተቀናጀ መንገድ የሚመራ አካል የለም፡፡ ይህ ባለመሆኑም በኃላፊነት እስከአለን ድረስ ለችግሮች መፍትሄ ብለን የምናቀርባቸውን ሀሳቦች በመተው በተቃራኒው በመተግበር ችግሮችን ማወሳሰብና ማባባስ እየጨመረ በመምጣቱ ይህ ነገር ለምን ይሆናል በሚል ጉዳዩን በተደጋጋሚ በማንሳት ለመፍትሄ ተግቻለሁ፡፡ ችግሮችም ከዛሬ ነገ ይፈታሉ ብዬ በግሌ ባምንም በተገቢው ፍጥነት ባለመፈታታቸው ምክንያት በችግሩና በመከራው ጊዜ ለህዝባችን እንደ ተቋም ማድረግ ያለብንን ሁሉ እንዳናደርግ ሆነን ቆይተናል፡፡ ይባስ ብሎም የክልሉ ወቅታዊም ሆነ የቆዩ የፀጥታና የሰላም ግንባታ ሂደቶችና ነባራዊ ሁኔታ በከፍተኛ አመራሩ ሳይገመገምና ችግሮች ተለይተው #የጋራ የመፍትሄ አቅጣጫ ሳይሰጥ በቀን 01/07/2013 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ስልጣንን አለአግባብ በመጠቀም የኮሚሽኑ #ሥልጣንና ኃላፊነት የሆነውን “የፖሊስ ምክትል ዘርፍ ኃላፊ” መመደብን በመሻር በሁሉም አቅጣጫ የተወጠረውን የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ተገቢውን የሰው ኃይል መድበን እንዳንመራ ታግደን ቆይተናል፡፡ ይህ እግድ ከአሠራር ሥርዓት ውጭና ወቅቱን ያለጠበቀ መሆኑን በተደጋጋሚ እንዲሁ ለሚመለከተው አካል ባሳውቅም መፍትሄ የሚሰጥ አመራር አልነበረም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከ15/08/2013 ዓ.ም ጀምሮ ከኃላፊነት ተነስተሃል የሚል ደብዳቤ እንደተጻፈ ሰምቻለሁ፡፡ ከኃላፊነት በመነሳቴ ተቃውሞ ባይኖረኝም አንድ ኃላፊ ከኃላፊነቱ ሲነሳ የነበረው ድክመትና ጥንካሬ በመደበኛ ሁኔታ ተገምግሞ መሆን እንዳበት አምናለሁ፡፡ ለዚህም በተደጋጋሚ ግምገማ እንዲካሄድ ሳነሳ ቆይቻለሁ፡፡ የፀጥታ ሥራው በጥልቀት እንዲገመገም ሳነሳ የቆየሁበት ምክንያት ለግሌ በማሰብ ሳይሆን እያንዳንዱ ተቋም ኃላፊ ስላለውና ኃላፊውም በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት ልክ የተግባር ሥራው መገምገም እንዳለበት በመርህ ደረጃ ስለማምን ነው፡፡ በተጨማሪም አመራሮችና ኃላፊዎች ከተላላኪነትና ከአድርባይነት ወጥተው ራሳቸውን ለሕግና ለሥርዓት ብቻ ተገዥ አድርገው ሕግና ሥርዓት በሚፈቅድላቸው መሠረት ህዝባቸውንና ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ብዬም አምናለሁ፡፡

አሁን ላይ ያለው የአሠራር ሥርዓት አንድም ቀን ግምገማ ሳይደረግ እንዳንሰራ ደግሞ ስልጣንን አለአግባብ ተጠቅሞ በደብዳቤ ታግደን እያለ በሂደት ደግሞ ከኃላፊነት ተነስተሃል ማለትና ከኃላፊነት የተነሳበት ምክንያቶች ተብሎ #ስብዕናዬን የማይመጥንና የሥም ማጥፋት ሥራ #በማህበራዊ ሜድያ እየተሠራ ነው፡፡ ሥም የማጥፋት ሥራው ለተከፋይ የማህበራዊ ሜድያ ፀሀፊዎች #የሀሰት መረጃ በመስጠት ክብሬን ለማዋረድ ተሞክሯል፡፡ እኔ አንዳንድ መሪዎች በሄዱበት የጥፋት መንገድ መሄድን አልመረጥሁም እንጅ ለሜድያ ሩቅ ሆኜ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ለህዝቤ ክብር ስል ላለፉት ዓመታት ከምወዳቸው ቤተሰቦቼ ተለይቼ በርካታ ሥራዎችን ሰርቻለሁ ብዬ ስለማምን ሥራዬ ሳይገመገምና ከጥፋቴ ሳልማር በግምገማ ከኃላፊነቴ አንደተነሳሁ ተደርጎ የሚናፈሰው ሥም ማጥፋት ትክክል ባለመሆኑ ይህን የሥራ ግምገማ ማመልከቻ እንድጽፍ ተገድጃለሁ፡፡ ስለሆነም እናንተ የሚመለከታችሁ ከፍተኛ አመራሮች የግምገማ መድረክ ፈጥራችሁ በኃላፊነት የነበርኩባቸው ዓመታት ሥራዎች በአግባቡ እንዲገመገሙና እኔም ሆንኩ ተተኪው አመራር ከግምገማ ውጤቱ ትምህርት ወስደን ጥንካሬያችንን ይበልጥ እንድናጎለብት ደካማ ጎናችንን ደግሞ እንድናርም በአጭር ጊዜ እድል እንዲፈጠር በአንክሮ እጠይቃለሁ፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ሥም አጥፊውን አካልና በአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ ጥቅሞች ላይ የሚቆምረውን ኃይል በመረጃና በማስረጃ ለሀገሬ ህዝብ ለማጋለጥ የምገደድ ይሆናል፡፡

ከሰላምታ ጋር!
አበረ አዳሙ

Please wait, video is loading...

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 13:21
by Revelations
Please wait, video is loading...

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 13:37
by Revelations

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 14:02
by Revelations

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 16:30
by Revelations

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 17:04
by Wedi
Dr Bezabeh Asmamaw

የአበረ አዳሙ የፎርንሲክ ምርመራ በውጭ ሀገር ሊሰራ የሚያስገድዱ አራት ምክንያቶች።

1. ትክክለኛው ሰውየው የሞተበትን ምክንያት በአስተማማኝ ማወቅ ግድ ስለሚል። የኮሚሽነሩ መሞት ከተሰማበት ሰዓት ጀምሮ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የፎርንሲክ ሙያ ከሚጠይቀው እውቀትና ሳይንስ በተላተመ ሁኔታ የሞቱ ምክንያት በሚል ዘገባ ይዞ ወጥቷል። የጤና ባለሙያዎች የሰው ልጅ ልቡ እየመታ ይሞት ይመስል ለሰውየው ሞት ምክንያቱ የልብ ድካም ነው የሚል ከሙያ ስነ ምግባር ውጭ የሆነ ማብራሪያ ለፕሬስ ድርጅቱ ሰጥተዋል። የዚሁ ተመሳሳይ የዜና ዘገባ ለቁጥር የሚታክቱ አክቲቪስቶች እየተቀባበሉ ሞት ይሁን ግድያ ያልገባንን ሰዎች ግድያ የሚመስል ጥርጣሬ ውስጥ እንድንገባ አድርገዋል። ከእነዚህ በተቃራኒ ኢትዮ360 ግድያ ነው የሚል ዘገባ ሰርቷል። በሰውዬው ሞት የመገናኛ ብዙኃን ተጨባጭ ያልሆነ ወሬና የጤና ባለሙያዎች ከሙያው ስነ ምግባር ውጭ የሆነ ማብራሪያ ሰጥተው እንደታዘብነው የአበረ አዳሙ የፎርንሲክ ምርመራ የግድ በገለልተኛና በሦስተኛ ወገን መሰራት ግድ ይለዋል የሚል መደምደሚያ እንድንደርስ ያስገድዳል።

2. ቤተሰቦቹ የሰውዮውን ሞት ምክንያት ያለ ተፅንኦና በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ማወቅ ስለሚኖርባቸውና መብታቸው በመሆኑ። ይሄ ደግሞ የፌደራል መንግስቱ የሞት ምክንያት በሚል ያቀረበው ሪፖርትና በኢንጅነር ስመኘው የተፈፀመው ለቤተሰብም ለህዝብም ሆነ ለማንም አሳማኝ ያልሆነ የኢንጅነሩ የሞት ምክንያት አንፃር አሁንም ድረስ በቤተሰቦቹ ተቀባይ የሌለው መሆኑን ስለምናውቅና ሁለተኛ ስህተት መፈፀም ስለሌለበት።

3. የአማራ ህዝብ በገለልተኛ አካል እውነታውን የማወቅ መብትና ግዴታ ስላለበት። ሎሌውና ሽንፍላው ብአዴን ምንም እንኳን ሲኖር አማራ ባይሆንም፣ ሲኖር የአማራ ህዝብን በጠላቶቹ የሚያስፈጅ ቢሆንም ብአዴን ገዱ በአንድ ወቅት ስለ ወልቃይት በተናገረው አውድ ስናየው የብአዴን ጉዳይ ብንሸሸው ብንሸሸው ከአማራ ህዝብ አጀንዳነት የማይወጣ በመሆኑ። የአማራ ህዝብ ደግሞ ከመቼውም በላይ የተቃጣበትን የህልውና ተግዳሮት አንድ ሁኖ እንጂ ተለያይቶ መታገል የማይችል በመሆኑ ከገለልተኛ ወገን ያለምንም ጥርጣሬ እውነታውን ማወቅ ግድ ይለዋል። መብቱና ግዴታውም ነው። ብአዴን ሲኖር አማራ ባይሆንም ሲሞት አማራ እየተደረገ የአማራ መጣያ መሆን ስለሌለበት።

4. የፌደራል መንግስት ገለልተኛ ባለመሆኑ በተለይም ደግሞ የፌደራል መንግስቱ ቅጥያ አክቲቪስቶችና ፀሀፍት ከሰውየው መገደል ቀናትና ሳምንታትን አስቀድመው ጥርጣሬ የሚያጭሩ ፅሁፎችንና ሰነዶችን ያሰራጩ የነበረ በመሆኑ።

በእነዚህና ሌሎችም ምክንያቶች የአበረ አዳሙ የፎርንሲክ ምርመራ የግድ በውጭ ሀገርና በገለልተኛ አካል መሰራት ይኖርበታል። ይሄን እውን ማድረግ ደግሞ ብቸኛና ቀጥተኛው ኃላፊነት የሚወድቀው ያው በሎሌ ብአዴን ላይ መሆኑ ይሰመርበታል።

ሎሌ ብአዴን ቢያንስ ስትኖር አማራ ባትሆንም ስትሞት ለአማራ ህዝብ መነታረኪያ የምትሆነውን ምዕራፍህን ዝጋ።


Please wait, video is loading...

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 17:17
by Revelations

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 17:55
by Wedi
ኢትዮ 360 ከውስጥ ባገኘው መረጃ ኮሚሸነር አበረ አዳሙ በመርሽ መገደላቸውን አረጋግጧል!!

ኮሚሸነር አበረ አዳሙን ያስገደለው ሴረኘው አብይ አህመድ ነው፡፡ አብይ አህመድ ኮሚሸነር አበረ አዳሙን ያስገደለበት ምክንያት ሰኔ 15 እና ዶር አንባቸው መኮነን እና እነ ጀንራል አሳምነው ፅጌን አብይ አንዳስገደላቸው ስለሚታወቅ ኮሚሸነር አበረ አዳሙን ምስጢር እንዳያወጣ በማለት ነው!! አብይ አህመድ የመጨረሻ አረመኔ የሆነ ሰው ነው!!



Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 20:47
by Revelations

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 21:33
by Abere
በጣም አሳዛኝ ድርጊት። የአማራ ክልል የኦነግ ብልጽግና ተላላኪዎች ቆሻሻ እጅ ያለብት ነው እንጅ በምንም ተዐምር ድንገተኛ ሞተ የሚለው ከምርጫ ውስጥ የሚገባ አይደለም። በጣም የሚያሳዝነኝ የሞተው ሳይሆን ገና ለሚሞተው የአማራ ህዝብ ነው። አማራ ጄግኖች እና ሃቀኛ ልጆቹን በዐድርባይ ውሻ ተላላኪዎች እየተነጠቀ እንደት ነፃ ይወጣል። በጣም የሚገርመኝ የሕክምናው ቅብጥርስየ ምክንያት። በእግሩ ሆስፒታል እየተራመድ (ከአንድም ሁለት ሆስፒታል) ልብ ትካት ገደለው ማለት ያስቃል። የፈጥኖ ደራሽ አምቡላንስ ጤና ረዳት ወይም ተራ ቀይ መስቀል ስራተኛ የመጀመሪያ እርዳታ አድርጎ ህይወት ሊታደግ የሚችለውን ህመም የማጭበርበሪያ ምክንያት የሃኪሞች ምስክርነት መፈለጋቸው። አማራ ከብአደን እስካልተላቀቀ ገና እልፍ አዕላፍ ይሞታል።

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 04 May 2021, 22:56
by Revelations
According to this official, Commisioner Abere Adamu, "diagnosed himself" on his way to the hospital. Are we surprised by this statement? Nope!

Please wait, video is loading...

Re: "በድንገተኛ በሽታ ሞቱ" የሚለው "በሕክምና ሲረዱ ቆይተው" በሚል ተቀይሯል

Posted: 05 May 2021, 06:22
by Revelations
Please wait, video is loading...