Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 2688
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

የአቡዳቢ መሪ ቢን ዛይድ የህዳሴ ግድቡን ቀውስ ለመፍታት ለአል ሲሲ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥተዋል ! 2.5 ቢሊዮን ዶላር እንደማይሰጣቸው ተነግሯቸዋል።

Post by Za-Ilmaknun » 03 May 2021, 17:05

በቅርቡ ካይሮን የጎበኙት የአቡዳቢ መሪ ቢን ዛይድ የህዳሴ ግድቡን ቀውስ ለመፍታት ባቀረቡ አዲስ የመፍትሔ ማዕቀፍ ውስጥ ለአል ሲሲ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥተዋል ተብሏል። ወደ ግጭት እንዳይገባ አማራጭ የሰጡት ቢን ዛይድ ለግብፅ የሚያቀርቡትን ገንዘብ ለማዘግየት ወስነዋል። አል ሲሲ ከአቡ ዳቢ እየጠበቁት የነበረው የሚያዝያ፣ ግንቦትና ሰኔ ወር 2.5 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ገንዘብ ትዕዛዙን ተፈፃሚ እስሚያደርጉ ድረስ እንደማሰጣቸው ተነግሯቸዋል። :|

አብደላህ ሐምዶክ "ዋስትና የምናገኘው ከካይሮ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ነው” ብለዋል። ሳዲቅ አል-ማህዲ ከካይሮ ያላትን ትስስርም ከልክለዋል።አል-አረቢያ የግብፅ ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ሰፊ ዘገባ አስነብቧል። ምንጮቹ እንዳሉት ግብፅ የሱዳንን አቋም “አደገኛ” ሲሉ ገልፀውታል።
በሱዳንና ግብፅ መካከል የተፈጠረው የአቋም ልዩነት የሱዳን ውጭ ጉዳይ ምኒስትሯ ማርያም አል-ማህዲ ከግብፁ አቻ ሳሚህ ሹክሪ በካይሮ ሊያካሂዱት የታቀደው ስብሰባ እንዲሰረዝ ምክንያት ሆኗል፡፡

ከግብፁ ውጭ ጉዳይ ሳሜህ ሹኩሪ ጋር ለመምከር የሱዳኗ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ማሪያም ሳዲቅ አል-ማህዲ ወደ ካይሮ ለመጓዝ ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩ ስብሰባው በሐምዶክና እሳቸው ባደራጁት የባለ ስልጣናት ጥምረት መሰረዙ ነው ምንጮቹ ለአል-አረቢ የጠቀሱት፡፡ የሱዳን መስኖ ሚኒስትር ያሲር አባስና ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ መካከል በህዳሴ ግድቡ ውጥረት ዙሪያ የማያግባቡ አካሄዶች እንደነበሯቸውም አል-አረቢ ጠቁሟል። ሐምዶክ የግድቡን አለመግባባት የኃይል ካርድ መፍትሄ አይደለም የሚል አቋም ነው ያላቸው ብሏል ዘገባው

አል-አረቢ ዋቢዎች ጠቅሶ ባስነበበው ሌላ መረጃም ቢን ዛይድ የፖለቲካ አማካሪያቸው ባለፈው ሳምንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጋር እንዲወያዩ በድብቅ ልከዋቸዋል። የኤሚሬት ጥረት አንድም ግብፅ የምታራምደው አካሄድ ወደ ግጭት አምርቶ በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንቨስትመንቷ እክል እንዳይገጥመው ያለመ ነው(የተባበሩት አረብ ኤምሬት በሦስቱም አገሮች ሰፋፊ ኢንበስትመንት እንዳላት ዘገባው አስታውሷል)። አል-አረቢ ከምንጮቹ ያገኘውን ተጨማሪ መረጃ ጠቅሶ “የቢን-ዛይድ አማካሪን የአዲስ አበባ ጉብኝት በተመለከተ ኤሚሬትስ ምንም ነገር ሳታሳውቃት እንደነበር የተረዳችው ካይሮ ሁሉም ካለፈ በኋላ መሆኑ ያስደነገጣት ሆኗል” ብሏል።

የግድቡ ሁለተኛ ዙር ሙሊት ሁለት ወራት በቀሩት በዚህ ጊዜ አብደላህ ሐምዶክ ከሽግግር ባለ ስልጣናቱ ጫና የተላቀቀ ጠንካራ አመራር በመስጠት ላይ ነው የሚገኙት።

https://mereja.com/amharic/v2/500900

Post Reply