Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ውርደት

Post by sarcasm » 02 May 2021, 12:24

ሚያዝያ 21 ቀን 2013
ይቅርታ መጠየቅ

ዛሬ ጠዋት "የመከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል ጋር ተወያዩ" በሚል መዘገባችን ይታወቃል ።
"አምባሳደር አሊስተር ከውይይቱ በኋላ እንደተናገሩት ፣ አገራቸው ከጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን ቀመር ከ2020 ጀምሮ ከአፍሪካ አገራት ጋር እንደ አዲስ ግንኙነቷን አንደምታጠናክር..." ብለን የጠቀስነው አመተ ምህረት ከ2018 ጀምሮ በሚል አመተ ምህረቱ እንዲስተካከልልን እንጠይቃለን ።

በተጨማሪም "በቅርቡ የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ለሀገሪቱ የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ሒደትና ለቀጣናው ዙሪያ መለስ ሰላምና ደህንነት አስተዋጽኦ ያበረከተ መሆኑን..." ብለን የዘገብነው " በትግራይ ፣ በሀገሪቱ ፣ በቀጣናው እና በሌሎች ጉዳዮች መነጋገራቸውንም አስታውቀዋል '' በሚል ተስተካክሎ እንዲነበብልን ተከታዮቻችንን ከይቅርታ ጋር እንጠይቃለን ።

Please wait, video is loading...




FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
29 April at 06:51
ሚያዝያ 21 ቀን 2013

ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል ከኢፌዴሪ ጋር ተወያዩ፡፡

የእንግሊዝ አምባሳደር እና ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ያደረጉት ውይይት በአፍሪካ ቀንድ እና በቀጣናው የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች እንዲሁም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል ከውይይቱ በኋላ እንደተናገሩት ፣ አገራቸው ከጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን ቀመር 2020 ጀምሮ ከአፍሪካ አገራት ጋር እንደ አዲስ በመቃኘት የጀመረቸውን የግንኙነት ምዕራፍ በመርህ ላይ በተመሰረተ አኳዃን ለማስኬድ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት ግልህ ሚና ይጫወታል ፡፡

ከአገራችን ጋር ያላቸውን ስትራቴጂክ አጋርነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገርም በወታደራዊና የሰላም እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ በትግራይ የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ለአገሪቱ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሂደትና ለቀጣናው ዙሪያ-መለስ ሰላምና ደህንነት አስተዋፅዎ ያበረከተ መሆኑን የተናገሩት አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል ፣ በቀጣይ ከሚካሄዱ አገራዊ ሁነቶችና ሌሎች ጉዳዮች አንፃር የእንግሊዝ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄ/ል ብርሀኑ ጁላ በበኩላቸው ፣ አገራችን ካለችበት አሁናዊ ሁናቴ አንጻር ከቀጣናው አገራት ጋር ያሉትን የእርስ በርስ ግንኙነቶች በማጤን ለዘላቂ ሰላማችን በትኩረት በመሰራት ላይ መሆኑን ገልፀው ፣ በአህጉራዊ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና ሰራዊታችንም የአገሪቱን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በአስተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠውላቸዋል፡፡
Please wait, video is loading...