Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5626
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

በአየር ላይ የሚንሳፈፉት የአብይና የደጋፊዎቹ የውሸት ንግግሮች ሀገሪቱን ከዳጡ ወደ ማጡ

Post by TGAA » 01 May 2021, 02:30

በአሁኑ ሰአት ትልቁ የኢትዮጵያ ችግር በግንባር ቀደትምትነት የህዝብ ደህንነት ነው ፤ የአብይ መንግስት ዋና የዘንጋውና የሚያጣጥለው ደግሞ የህዝብ ደህንነትን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ የህዝብ ደህንነትን ከአሜሪካ ህዝብ ጋር እያወዳደረ የኛ ጋር የሚሞተው ህዝብ ትንሽ ነው ስለዚህ ስለሚገደለው ሰው አታጋኑ የሚል መንግስትም ለመጀመሪያ ግዜ ነው፤ ህዝብ ከመንግስት ቁጥጥር በሆን መንገድ ሊሞት ይችላል ነገሩ ግን በየቀኑ የሚደረጉ ወገል ለይቶ የመግደል ዘመቻን እንለማመደው የሚል መንግስ ተሰምቶም አያውቅም ፡፡
የኢትዮጵያ የህዝብ ግድያን ለማለማመድ የሚደረጉ ዲስኩሮች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ የኦሮሙማ ይቅደም ቱሪናፋዎችና የአማራ ብልጽግና ሲደመጡ
1/ አማራ ብቻ አይደለም እየሞተ ያለው እንደውም አብዛኛ የሚሞተው ኦሮሞ ነው(ኦሮሞ ኦርቶዶክሶች ተገድለዋል ለምንguilt by association ) የዚህ አቀንቃኞች በዋነኝነት ጠ/ሚ አብይ ታየ ደንደአ የኦሮምያ ብልጽግና በስምምነት የሚያስተላልፈት መልክ (ማስረጃው የራሳቸው አፍ ነው )
2/ አማራን እየገደለ ያለው አማራ ነው ፤ ቤንሻንጉል ያለውን ወርቅ ለመውሰድ አማራ እየገደሉ በግሬደር እየቀብሩ ፎቶ እያነሱ ይለጥፋሉ ( የአብይ ውታፍ ነቃይ የታየ ደንደአ ጓደኛ ስዩም ተሾመ) ማስረጃው ከደህንነት ያገኘው ማስረጃ _ ጥቅስ ጥቅስ ታየ ደንደአ)
3/አማሮች እራሳቸው ላይ ሞት የሚጠሩት ተገደልን እያሉ እየለፈለፉ እየጋበዙ ነው ስለሚገደሉ ሪፖርት የሚያደርጉትም ያንኑ እያረጉ ነው አማራን የሚያስጨርሱት ፤ ዝም ቢሉ ኖሮ አይገደሉም ነበር ( የኦሮሞ ተንታኝ ፤ አስመሳይ የአማራ አዛኝ ነኝ ባይ በውስጡ ደስተኛ ኦሮሙማ ትቅደም ፕሮፓጋንዲስት )
4/ ስለአማራ መገደል በአማራ ክልል እያነሱ የሚጮሁ ፤ የሚናገሩ ፤ የሚከራከሩ ሁሉ ከአማራ ክልል ውጭ ያሉ አማሮችን ሊያስጨርሱ ነው ፤ እንደነሩስ ያሉት ናቸው የበለጠ አማሮች እንዲገደሉ የሚያደርጉት ( ከኢትዮጵያ ውጭ ስላለሰው የሚናገሩ ነው የሚመስሉት) የአማራ ብልጽግን የየቀን መዝሙር ፤ ሲገድሉ ዝም ብሎ ነው መገደል እንጂ መናገር ስለሞት የበለጠ ያስገድላል ፤ ከዚህ የበለጠ ደደብነት ሊኖር ይችል ይሆን ፤
5/ የአማሮች ችግር የዚህ ሁሉ ሶቆቃ ምክንያት መብታችን ይጠበቅ ማለታቸው ነው እንደሁለተኛ ዜጋ በሌላው ልገሳ ብቻ ነው መኖር ያለበችው እኩልነት መጠየቅ የሌላውን መበት ለመውሰድ የሚደረግ ሙከራ ነው ፤ ኦሮሙማ ይቅደም ጥርቅም
6/ የኦነግን ማን ነው ከመከላከያ የበለጠ እንዲታጠቅ ፤ እንዲሰለጥን ፤ በትልልቅ መኪና እየጫነ እየተመላለሰ የአማራን ህዝብ እንዲጨርስ የሚያደርገው ፤ በመጀመርያ ወያኔ ነው ገንዘብ መሳሪያ እየላከ ጸረ ሰላም ሀይሎች ጭፍጨፋ እንዲያደርጉ የሚያደርገው ፤ ከዚያ ኦነግ ሸኔ አንዳንድ ከውስጥ ሆነው ከሚሰሩ የኦሮሞ ብልጽግና አባላት ጋር በማበር ነው ሰላማችን የሚነሱን (10፣000 የኦነግ ደጋፊዎች ከብልጽግና ከተባረሩ በኋላና በአብይ ትእዛስ የአማራው ልዩ ሀይል ከወያኔጋር ሲፋለም የኦሮሞ ልዩ ሀይል ደግሞ የመካከለኝውናን የደቡቡን አካባቢ ለማጽዳት ባደረገው ዘመቻ 10፣000 ኦነግ ሸኔ ደምሧል እንዲሁም ከሁለት ሺህ በላይ ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን ማርኳል (ማስረጃ “እመኑን “) አሁን ደግሞ ወያኔም ወድቆ እየተፍራግጠ ባለበት ስራው ወደ ግብጽና ሱዳን ተሸጋግሯል ። ሱዳን _ ግብጽ አይተኙም ግን በሩን ከፍቶ የሰጠው ቢሆን እንኳን አብይ ነው)

ይህንን አይነት አይነት መርዝ ቅስቀሳ መላው ኢትዮጵያ በሚተላለፍ የፓርላማ ስብሰባ ላይ _ ይህ ጥያቄ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለማቅረብ በጽሁፍ ከሶስት ቀን በፊት ቀርቦ ተቀባይነት ካገኝ ብቻ ነው የፓርላማው አባል ጥያቄውን ማቅረብ የሚችለው ፤ ይህ ጸረ አማራ የሆነ የውሸት ቅስቀሳ በአንድ ሰው ሳይሆን በተመሳሳይ ሁኔታ በሌላ ሴትም በፓርላማ ውስት፣ እንዲደገም ተደርጓል ፤ አማሮች ግን በአከታታይ እየተጨፈጨፉ ማስረጃ እያላቸው ፓርላመቱ ጠቅላይ ሚንስትሩ ባለበት ተነስቶ አያውቅም ። ፓርላመቱም ቀርበው ወለጋ ላይ ስለተደረገው ጭፍጭፋ እንዲገልጹ ቢጠይቃቸው መልስ ሳይስጥበት አብይ አልፎታል ፤

በመንግስት በሚደገፈው የኦሮም ሚድያ ላይ የተወሰደው

ከወር በኋላ አጣዬና ህዝቧ ምን ይመስላሉ ከፓርላማው የአክራሪዎች ፕሮፓጋንዳ በኋላ፤ ገዳዮቹስ ተራ ገበሬዎች ናቸውን ፤ ከወንጀሉ ሰለባ ከሆኑት ደግሞ እንስማ