ሁለተኛ በትክክል ስዩም እንዳለው ብልጽግናን ተቀባይ ፓርቲ የሚያደርገው አቢይ ብቻ ነው ። ብልጽግና ማለት አቢይ ማለት ነው። አለ አቢይ የብልጽግና ፓርቲ የሚባል ነገር አይኖርም። አለ አቢይ ብልጽግና ማለት ኢህአዴግ የሚባል የጎሳ ጥርቃሞ በትህነግ የተፈጠረ ስብስብ ነው።
ሶስተኛ፣ የጎሳ ፖለቲካ እኔ ዴሞክርሲ ሳይሆን ኤትኖክራሲ ነው የምለው። ስለሆነም የጎሳ ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም ። ይህ እጅግ መሰረታዊው ያቢይ ችግር ነው ። አቢይ አህመድ በኢሃዴግ ላይ ቆሞ ዴሞክርሲ ሊያመጣ በፍጹም አይችልም ። ይህ እጅግ መሰረታዊ ሃቅ ገና በመጀመሪያው ክርክር ግልጽ እየሆነ ነው።
አቢይ በግል አቋሙ የኢዜማ አባል ቢሆን የሚቀለው ሰው ነው ።
አራተኛ፣ ይህ ክርክር በጣም የሚፈለግና የሚደገፍ ነው ። ምክንያቱም ይህ ክርክር ያገራችን ፖለቲካ እውነተኛ ገጽታና ይዘት ማለትም ዜጋዊና ጎሳዊ መንገዶች መካከል ያለው ልዩነትና ትግል ነው። በዚህም ምክኛት ነው አሁን ባለበት ከቀጠለ ብልጽግ ና አምባገነን ፓርቲ እንደ ሚሆን ስይታለም የተፈታ ነው ።
አምስተኛ፣ ስዩም በትክክል እንዳለው አቢይ አሁን በያዘው አቋሙ ከጸና ወደ ፊት በቅንጅት የኢትዮጵያዊነት ፖለቲካ የሚያራምደው ከኢዜማ ጋር እንጂ ከኢሃድጋዊ ጎሳዊ ጥርቃሞች ጋር በመጨማለቅ አይደለም ።
ኤትኖክራሲ ማለት የጎሳ አገዛዝ ማለት ነው ። ዴሞክራሲ ማለት ሕዝባዊ አገዛዝ ማለት ነው ። ይህ ነው አንዱና ብቸኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅራኔ እምብርት !
ስዩም ተሾመ፣ ድንቅ ትንተና !!