Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3976
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

የሶስት ትውልድ ደም የጠጣ ጁንታው ህወሓት!

Post by Ejersa » 15 Apr 2021, 03:58

ጁንታው ህፃናት እሳት ላይ ማግዶ ለራሱ ግን እግሬ አውጭኝ ብሎ በየበርሃው እየተደበቀ ይገኛል። ጁንታ ህወሓት በ40 አመት ሶስት ትውልድ የበላ የደም መፍሰስ ፍቅር ያለው ሴጣናዊ ስብስብ ነው።

ለስልጣን ሲል የራሱ ህዝብ እንኳ ሳይራራ ይዞ ለመጥፋት ሞክሯል። ስርአቶች ይፈጠራሉ ይጠፋሉ ህዝብ ግን ሁሌም አለ። የትግራይ ህዝብ የ3000 አመት ታሪክ ያለው መንግስትነት የሚያቅ ህዝብ ነው ህወሓት ግን ይሄን ታሪክ ቀምቶ የትግራይ ህዝብ ታሪክ የ40 አመት ታሪክ እንደሆነ አድርጎ ራሱ ሲያገዝፍ ቆይቷል።

ጁንታው እኔ ከሌለሁ ትጠፋላቹህ ብሎም ያለ ህፍረት ይናገር ነበር። ጁንታው በእብሪት ተወጥሮ የማይነካ ቀይ መስመር አልፎ የሃገር መከላከያ ጨፍጭፎ በጀመረው ጦርነት ይሄን የጁንታ ክህደት እና ጭካኔ ለኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣ ቀስቅሶ ጁንታው እድሜው ሊያጥር ችሏል።