Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

የሕወሐት ውድቀት ምክንያት በሁለት እግሩ ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት መሞከሩ፣ ጠርዝ የነካ ብሔርተኝነትን መስበኩ፣ ሰፊ መሬት፣ ኢኮኖሚውን መቆጣጠሩ፤ በመጨረሻ የትግራይ ሕዝብን ለመከራ ዳርጏታል።

Post by Dawi » 15 Apr 2021, 03:15

"የሕወሐት ውድቀት ምክንያት በሁለት እግሩ ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት መሞከሩ፣ ጠርዝ የነካ ብሔርተኝነትን መስበኩ፣ ሰፊ መሬት፣ ኢኮኖሚውን መቆጣጠሩ፤ በመጨረሻ የትግራይ ሕዝብን ለመከራ ዳርጏታል" ። BINGO!

ቴዲ እና ኤርምያስ በጣም ጥሩ ውይይት አካሂደዋል፣ የዚህ ዓይነት ውይይት መልካም ነው።

እንደኔ ከሆነ ዶ/ር ዐብይ መሬት ላይ የሚሠራውን በማየት ከቤተ መንግሥቱ እድሳት ጀምሮ ኤትዮጵያን በጠነከረ መንገድ የሚያስቀጥል ሁኔታ ላይ ነን እላለሁ።

Check the following clip!

Last edited by Dawi on 16 Apr 2021, 14:47, edited 1 time in total.

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የሕወሐት ውድቀት ምክንያት በሁለት እግሩ ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት መሞከሩ፣ ጠርዝ የነካ ብሔርተኝነትን መስበኩ፣ ሰፊ መሬት፣ ኢኮኖሚውን መቆጣጠሩ፤ በመጨረሻ የትግራይ ሕዝብን ለመከራ ዳር

Post by Meleket » 15 Apr 2021, 05:04

ኤርምያስ ለገሠ በብዕሩ ወያኔን ገመና በተጨባጭ ማስረጃ ያጋለጠ፡ የወያኔን የሸፍጥ አካሄድ በማለዳ አጢኖ፡ ሳይመሽም የኢትዮጵያ ህዝብን አንቅቶና ኣቅንቶ፡ ወያኔን ከሥልጣን ኮረቻ በመገፍተሩ ሂደት ጉልህ ሚና ያበረከተ፡ ምርጥ ዜጋ ነው። ያይን ቀለም ቦለቲካ ሰለባ ኤርትራዉያን የኤርምያስን ጉልህ ሚናና ሓቅን ገላጭነት ላፍታም በፍጡም አይዘነጉትም።

ኤርሚያስ የወዲያኛው ሳይሆን የወዲህኛው ትውልድ ኣብነትና አስኳል ነህና፡ ያመንክበትን ቦለቲካ እንደትናንቱ ዛሬም በነጻነትና በትጋት ህዝብን በማንቃት ጥረትህ ግፋበት እንልሃለን፡ በሃሳብ ልዕልናና በነጻነት ሃሳብን የመግለጽ ሂደትን የምናከብር ኤርትራውያን ጎረቤቶችህና ወንድሞችህ።
:lol:

የሕወሓት ውድቀት ዋንኛ ምክንያቱ፡ በምዕራባውያን እርጥባንና በኢትዮጵያ ሕዝብ ፈንጂ ረጋጭነት ተማምና፡ ካስታጠቃትና ከባለ ውለታዋ ከኤርትራ ህዝብ ጋር፡ በዕብሪተኝነት ተገፋፍታ ጦር መማዘዟ ነው። ይህም ብቻ ኣይደለም፡ በዓለም አደባባይ የፈረመችበት ይግባኝ የሌለው ፍርድን ሳታቅማማ ከመተግበር ይልቅ፡ አንካሳ ምክንያት በማቅረብ ሰላማዊ መፍትሄን ለማጨናገፍ እስከ ጣረሞቷና ኣየር ላይ የተበተነ ዱቄት እስክትሆን ድረስ ሳታሰልስ ለከንቱ በመፍጋቷ ነው።[አራት ሚሊየን ነጥቦች]
:mrgreen:
Dawi wrote:
15 Apr 2021, 03:15
"የሕወሐት ውድቀት ምክንያት በሁለት እግሩ ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት መሞከሩ፣ ጠርዝ የነካ ብሔርተኝነትን መስበኩ፣ ሰፊ መሬት፣ ኢኮኖሚውን መቆጣጠሩ፤ በመጨረሻ የትግራይ ሕዝብን ለመከራ ዳርጏታል" ። ...

Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

Re: የሕወሐት ውድቀት ምክንያት በሁለት እግሩ ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት መሞከሩ፣ ጠርዝ የነካ ብሔርተኝነትን መስበኩ፣ ሰፊ መሬት፣ ኢኮኖሚውን መቆጣጠሩ፤ በመጨረሻ የትግራይ ሕዝብን ለመከራ ዳር

Post by Dawi » 16 Apr 2021, 14:31

Fiyameta - ፊያሜታ ለምን ከአሥር ዓመት በፊት የተሰራ ቪድዮ ቀንጥባ፣ ኤርምያስ ስለደብረጺዮን ከሐይለማሪያም አወዳድሮ? ያለውን እንዳመጣች አልገባኝም፣ የሐሳብ "ድርቀት" እንደ "ጁንታ" ሳይሆን አይቀርም፤
ውታፍ ነቃይ! :P

Meleket - መለከት ግን ሐቁን በግሩም አቀራረብ ተናግረሃል፤

I couldn't agree more!

Cheers!

Meleket wrote:
15 Apr 2021, 05:04
ኤርምያስ ለገሠ በብዕሩ ወያኔን ገመና በተጨባጭ ማስረጃ ያጋለጠ፡ የወያኔን የሸፍጥ አካሄድ በማለዳ አጢኖ፡ ሳይመሽም የኢትዮጵያ ህዝብን አንቅቶና ኣቅንቶ፡ ወያኔን ከሥልጣን ኮረቻ በመገፍተሩ ሂደት ጉልህ ሚና ያበረከተ፡ ምርጥ ዜጋ ነው። ያይን ቀለም ቦለቲካ ሰለባ ኤርትራዉያን የኤርምያስን ጉልህ ሚናና ሓቅን ገላጭነት ላፍታም በፍጡም አይዘነጉትም።

ኤርሚያስ የወዲያኛው ሳይሆን የወዲህኛው ትውልድ ኣብነትና አስኳል ነህና፡ ያመንክበትን ቦለቲካ እንደትናንቱ ዛሬም በነጻነትና በትጋት ህዝብን በማንቃት ጥረትህ ግፋበት እንልሃለን፡ በሃሳብ ልዕልናና በነጻነት ሃሳብን የመግለጽ ሂደትን የምናከብር ኤርትራውያን ጎረቤቶችህና ወንድሞችህ።
:lol:

የሕወሓት ውድቀት ዋንኛ ምክንያቱ፡ በምዕራባውያን እርጥባንና በኢትዮጵያ ሕዝብ ፈንጂ ረጋጭነት ተማምና፡ ካስታጠቃትና ከባለ ውለታዋ ከኤርትራ ህዝብ ጋር፡ በዕብሪተኝነት ተገፋፍታ ጦር መማዘዟ ነው። ይህም ብቻ ኣይደለም፡ በዓለም አደባባይ የፈረመችበት ይግባኝ የሌለው ፍርድን ሳታቅማማ ከመተግበር ይልቅ፡ አንካሳ ምክንያት በማቅረብ ሰላማዊ መፍትሄን ለማጨናገፍ እስከ ጣረሞቷና ኣየር ላይ የተበተነ ዱቄት እስክትሆን ድረስ ሳታሰልስ ለከንቱ በመፍጋቷ ነው።[አራት ሚሊየን ነጥቦች]
:mrgreen:
Dawi wrote:
15 Apr 2021, 03:15
"የሕወሐት ውድቀት ምክንያት በሁለት እግሩ ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት መሞከሩ፣ ጠርዝ የነካ ብሔርተኝነትን መስበኩ፣ ሰፊ መሬት፣ ኢኮኖሚውን መቆጣጠሩ፤ በመጨረሻ የትግራይ ሕዝብን ለመከራ ዳርጏታል" ። ...

Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የሕወሐት ውድቀት ምክንያት በሁለት እግሩ ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት መሞከሩ፣ ጠርዝ የነካ ብሔርተኝነትን መስበኩ፣ ሰፊ መሬት፣ ኢኮኖሚውን መቆጣጠሩ፤ በመጨረሻ የትግራይ ሕዝብን ለመከራ ዳር

Post by Meleket » 17 Apr 2021, 05:54

ወዳጃችን Dawi፦ ስለ ኤርምያስ ለገሰ የጻፍነው ምስክርነታችን፡ አቀራረቡን ግሩም እንዲሆን ያደረገው ሓቅ በመሆኑ ብቻ ነው። ሓቅ በተፈጥሮዋ ውብ ነች፡ ምንም ዓይነት ማሳመሪያ ኣያስፈልጋትም። ወዳጃችን Dawi ለለገሱልን ሞራል ከልብ እናመሰግናለን።

Post Reply