Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ብሔራዊ ቋንቋዎች እና የስራ ቋንቋዎች

Post by Naga Tuma » 14 Apr 2021, 21:18

ዛሬ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መልካም ዉይይት ጨረፍታ ኣይቼ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራሴን እንደገና ጠየኩኝ።

በያንዳንዱ ቋንቋ በየዕለቱ ብያንስ ሁለት ሰዎች ስራ እየሰሩበት ኣይኖሩም? ይህ ከሆነ ሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የስራ ቋንቋዎች ኣይዴሉም?

እያንዳንዱ የሃገር ቋንቋ ብሔራዊ ሃብት ኣይዴለም? ይህ ከሆነ ሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ብሔራዊ ቋንቋዎች ኣይዴሉም?

የትኛዉም ሃገር ኣቀፍ ፓርቲ የትኛዉንም የሃገር ቋንቋ ለስራ ኣስፈላጊ በኖነበት ሁሉ እንጠቀማለን ማለት ምን ስሕተት ኣለዉ? መጠቃም ማለት ኣንድ ቀን ስብሰባ ላይ መልዕክት ማስተላልፍ ሊሆን ይችላል። ያ ብቻ ቋንቋዉን የስራ ቋንቋ ኣያስብለዉም? የቋንቋዉ ተናጋሪ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ ኣባል ከሌላ የፓርቲ አመራር ጋር በሌላ ቋንቋ መግባባት ከቻለ እና መልዕክትን ማስተላልፍ ከቻለ ስራ ኣልሰራም? ስራ ኣልተፈጸመም?

ይህ ማለት ሁሉንም ቋንቋዎች በኣንድ ጊዜ ሁሉም ቦታ እንጠቀማለን ማለት ኣይዴለም። ብዙሃን ቦታዎች በኣንድ ጊዜ ለስራ ከኣንድ ቋንቋ በላይ የምያስፈልግ ኣይመስለኝም። የኣንዱን አከባቢ የስራ ቋንቋ ከሌላው አከባቢ የስራ ቋንቋ ጋር ለማግባብት በሁለቱ አከባቢዎች ከምያገለግሉ የስራ ቋንቋዎች በላይ ያስፈልጋል? የምያዋጣዉን የስራ ቋንቋ እና የየትኛዉን አከባቢ ቋንቋ በደባልነት መማር እንደሚፈልግ እያንዳንዱ አከባቢ በራሱ መወሰን ኣይችልም? በተጨማሪ ቋንቋን የማበልጸግ ኣላማ ካሆነ ለማህበራዊ ወይም ሲቪክ ድርጅቶች መተዉ ኣይቻልም?

እንደሚመስለኝ በእንግሊዘኛ ኦፍሻል እና ዎርኪንግ የሚባሉ ቃሎች ትርጉሞች ብዙ ሰዎችን ኣላስፈላጊ ክርክሮች ዉስጥ እያስገቡ ነዉ።
Last edited by Naga Tuma on 14 Apr 2021, 23:21, edited 1 time in total.

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: ብሔራዊ ቋንቋዎች እና የስራ ቋንቋዎች

Post by EPRDF » 14 Apr 2021, 22:20

Naga Tuma wrote:
14 Apr 2021, 21:18
ዛሬ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መልካም ዉይይት ጨረፍታ ኣይቼ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራሴን እንደገና ጠየኩኝ።

እያንዳንዱ የሃገር ቋንቋ ብሔራዊ ቋንቋ ኣይዴለም? ይህ ከሆነ ሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ብሔራዊ ቋንቋዎች ኣይዴሉም?

እንደሚመስለኝ በእንግሊዘኛ ኦፍሻል እና ዎርኪንግ የሚባሉ ቃሎች ትርጉሞች ብዙ ሰዎችን ኣላስፈላጊ ክርክሮች ዉስጥ እያስገቡ ነዉ።
ኦቦ ናጋ ቱማ፣

ለነገሩ ይህን ክርክር ያየሁት ትናንት ነበር፣ የሆነ ነገር ሰምቼም ሳይዋጥልኝ አሳለፍኩት። ሆኖም፣ ጨወታን ጨወታ ያመጣዋልና አሁን አንተ ጉዳዩን ስታነሳ ስለነሸጠኝ፣ እስቲ እኔም ያ ያልተዋጠልኝን ነገር ልተንፍሰው።

ነገሩ ይህ ነው፣ ያ የኢዜማው ብርሃኑ ነጋ አማርኛ የስራም የብሔራዊ ቋንቋም መሆን አለበት ሲል ሰማሁት። ፕሮፌሰሩ ብሄራዊ ቋንቋ የሚለውን ሐረግ በሚገባ የተረዳው አይመስለኝም፣ ያንን ማለቱም የተወሰነውን ማህበረሰብ ክፍለ ለማስደሰት፣ ድጋፍና አድናቆት ከዛው የማህበርሰብ ክፍል ለማግኘት ሲል ነው ካሜራ በተደቀነበት አደባባይ የተዘረጠጠው።

አንድ ቋንቋ ለአንድ ሐገር ብሔራዊ ቋንቋ ለመሆን የሚያበቃው አንድኛውና ብቸኛው መስፈርት፣ ያ ቋንቋ ሌላ ቋንቋ በአካባቢው ሳይፎካከረው፣ ብቸኛ የዛ መሬት ህዝቦች ቋንቋና ከመሬቱም ጋር ታሪካዊ ቁርኝትና ትሥሥር ሲኖረው ብቻ ነው።

ከሰማንያ ብላይ ቋንቋ ባሉባት ኢትዮጵያ ማንኛውም ቋንቋ የብሔራዊ ቋንቋ የሚል ታይትል ሊሰጠው የሚያስችል ሕግ አይኖርም።

አማርኛ እንኳንስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ሊሆን፣ የአማራ ክልል የብሔራዊ ቋንቋ ለመሆንም አይበቃም ምክንያቱም በዛ የአማራ ክልል በሚባል መሬት ላይ፣ የነ አገው፣አርጎባና ቂማንት ለመሬቱ ኢንዲጂነስ የሆኑ ሕዝቦች ቋንቋ በሕይወት ስላለ።
ስለዚህ አማርኛም ይሁን ኦሮምኛ የስራ ቋንቋ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ብሔራዊ ቋንቋ የሚለውን ካባ ግን በገለፅኩት ምክንያት መደረብ አይችሉም።

ፕሮፌሶሬ ብርሃኑ ነጋም ይሁን የእርሱ ዓይነት ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸው ግለሰቦች ሕዝብ የሚያየው ካሜራ ፊት እየወጡ ከመቀደድ በፊት፣ በእንደዚ ዓይነት ስሜታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ግንዛቤና ዕውቀት በደንብ ቢፈትሹ መልካም ነው።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ብሔራዊ ቋንቋዎች እና የስራ ቋንቋዎች

Post by Naga Tuma » 15 Apr 2021, 00:00

EPRDF,

ይህ ለጫወታ የምነሽጥህ ከሆነ እሺ ይነሽጥህ ልበል?

መልካም ዉይይት ብዬ ሀሳብ የሰጠሁት ለወቀሳ ስይሆን ለግንባታ የሚረዳ ከሆነ ብዬ ነዉ።

እኛ ሁለታችን እያንዳንዱ ሃገር ያበቀለዉ ቋንቋ የሃገር ሃብት ስለሆነ ብሔራዊ ቋንቋ ነዉ ብለን ከተስማማን እስቲ በዚህ ሀሳብ የማይስማማ ካለ ከነምክንያቱ ይሰማ። ከሌለ ማንም የማይስማማበት በጣም ቃላል ሀሳብ ነዉ ማለት ነዉ።

እንዲሁም እያንዳንዱ ቋንቋ በየ አከባቢዉ በየቀኑ ስራ የሚሰራበት ስለሆነ የስራ ቋንቋ ነዉ ማለት ይቻላል በሚለዉም መስማማት የማንችልበት ምክንያት ያለ ኣይመስለኝም። ይህ እኮ እኛ ብንስማማም ባንስማማም በየቀኑ እየተፈፀመ ያለ ነዉ። እስቲ በዚህ ሀሳብም የማይስማማ ካለ ከነምክንያቱ ይሰማ። ከሌለ ይህም በጣም ቀላል ሀሳብ ነዉ ማለት ነዉ።

እነዚህ ሁለት ቀላል ሀሳቦች ከክልል ወደ ኣስተዳደርም የምያሻግሩን ይመስለኛል።

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ብሔራዊ ቋንቋዎች እና የስራ ቋንቋዎች

Post by Horus » 15 Apr 2021, 00:20

እኔ እስከ ሚገባኝ ድረስ ይህ በመሰረቱ ደደብ ጥያቄ ነው ።

ኦፊሴል ቋንቋ ማለት የመንግስት ቋንቋ ማለት ነው ። የመንግስት ቋንቋ መንግስት የመንግስት አገልግሎት የሚሰጥበት ቋንቋ ማለት ነው። አገልግሎት ሚሰጣቸው ዜጋዎች ናቸው ። ያ ህዝብ በሚገባው፣ በሚግባባበት ቋንቋ አገልግሎት ይሰጣል። እኔ በምኖርበት የአሜሪካ ከተማ ያሜርካ መንግስት (ፌዴአል፣ እስቴት፣ ካዉንቲ፣ ሲቲ) ባማሪኛ፣ ሱማሌ፣ ትግርኛ፣ ኦሮሞኛ አገልግሎት ይሰጣል ። ማለትም የተጠቃሚው ሰው ቁጥር ይወስነዋል ማለት ነው ። አላማውም የብሄር ጥያቄ ሳይሆን ያገልግሎት አቅርቦት መብት ነው ።

ይህ በቀጥታ የኢትዮጵያ ፌዴራል መፍትሄ ነው ። በኢትዮጵያ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የዞን፣ የክልል ፌዴራል መንግስታት አሉ። ስራቸው በውስጣቸው ላሉ ሰዎች አገልግሎት መስጠት ነው ። ለምሳሌ የሻሸመኔ ከተማ ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎች፣ ኦሮሞኛ ማያውቁ ሰዎች እዚያ ከተማ ሄደው እንዲኖሩ፣ እንዲሰሩ ፣ ታክስ እንዲከፍሉ የሚፈልግ የሚያበረታታ ከሆነ ለነዚያ ሰዎች በቋንቋቸው አገልግሎት መስጠት አለበት ። ሌላው ቢቀር አሰርጓሚ በመቅጠር ።

ይህ የመንግስት ቋንቋ የብሄራዊ ቋንቋ ሰብሴት (አንድ ክፍል ነው) ። ብሄራዊ ቋንቋ የዚያ ብሄር ህዝብ ቋንቋ ነው ። በኢትዮጵያ ብሄር ወስጥ 80 ጎሳዎች እና 80 ቋንቋዎች አሉ ። እነዚህ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋዎች ናቸው። የሚኖረው ጥያቄ አንድ የጎሳ ቋንቋ ሙሉ ነው ወይስ ዲአሌክት የሚል ነው ። ማለትም የተቀራራቢ፣ ተግባቢ፣ ዲያሌክቶች ስብስብ ነው ወይስ ብቻውን የቆመ ያደገ ለማለት ነው።

ስለሆነም አንድ ህዝብ ኢኮኖሚው፣ ባህሉ፣ አካባዊው፣ ገበያው ወዘተ አንድ ሆኖ ቁንቋው በብዙ ዴያሌክቶች የተለያየ ከሆነ ከዚያ ወጭ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ ይጠቀማል ። እንደ አማርራኛ ቋንቋ ያለው የሌሎች የጋራ ቋንቋ የሆነው በዚህ አይነት ነው።

መንግስት አንድ ቋንቋ በግድ ሊያስተምር አይችልም ፣ ቢሞክርም ገንዘብ ያባክናል እንጂ አይሰራም ። በአንድ ገበያ ውስጥ የሸማቾችን ቋንቋ መማር ያለበት ሻጩ፣ ነጋዴው ነው ። ስለዚህ ዶርዜ ለኦሮሞ ጥበብ መሸጥ ከፈለገ ኦሮምኛ ማወቅ አለበት ። ኦሮሞ ለዶርዜ ስንዴ መሸጠ ከፈለገ ዶርዜኛ ማወቅ አለበት ። ህዝብ ቋንቋ የሚማረውና የሚመርጠው በዚህ መንገድ እንጂ ኦነግ ሸኔ ኦሮሞኛ በሌሎች ላይ ለመጫን ብረት ስላነሳ አይደለም።

ወደፊት የተፈለልገውን ያህል ቋንቋዎች ብሄራዊ የሚል ቅጽል ሊለጠፍላቸው ይችላል። ያ ሁሉ ወረቀት ላይ ይቀመጣል ። ህዝቡ ራሱ በፈቃዱ የሚማራቸው የገበያ፣ የትምህርት፣ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የፍልስፍና፣ የአርት ወዘተ መሳሪያ፣ መስሪያ የሆኑት የመላ ኢትዮያዊያን የጋራ ቋንቋ ሆኖ ይወጣል ፣ ልክ እንደ ዛሬ አማርኛ ማለት ነው። ማለም 80 ጎሳዎቹን ሁሉ የሚያግባባ ማለት ነው።

አንድ ቋንቋ የሁሉም የጋራ መግብቢያ የሚሆነው ሁሉም ጎሳዎች በዚያ ቋንቋ ሁልም ወይም አብዛኛውን ነገር ሊሰሩበት ሲያስቻልቸው ነው። አንድ ቋንቋ የሁሉም የጋራ የሚሆነው ራሱ ያደገ፣ በቀላሉ መናገርና መጻፍ የሚቻል፣ ሁሉም አይነት የሰው ህይወት እና ስራዎችን መግለጽ የሚችል ሆኖ ሲያድግ ነው እንጂ ማጆሪቲ ስለተናገረው አይደልም። አማራኛ ብዙ አማራ ይናገረዋል፣ በአፋር ህይወት ወስጥ ምንም ሚና ከሌለው አፋር ባማግርኛ ላይ ግዜ አያጠፋም ። ግ ን አፋር አማራኛ በማወቁ እቃውን ለመሸጥ፣ እውቀት ለማካበት፣ አማራ ሄኦ እውቀቱን ለመሸጥ ከጠቀመው አፋር አማራ ባይሊንጓል ይሆናል ማለት ነው ።

ስለዚህ ባዶ የፖለቲካ መዶናቆር ዋጋ የለውም ። ቴክኖሎጂ ወጥ እስታንዳርድ ቋንቋ አለው ። ካልቸርም እንዲሁ ገበያ አለው። ዛሬ 80 ጎሳዎች ሁሉም በራሳቸውን የራሳቸውን ካልቸር ያመርታሉ። በዚህ የቴክኖሎጂና የካልቸር ገበያ ለመክበር የሚጣደፉት ፈጣሪዎች፣ አርቲስቶች፣ ኢንዱስትሪያሊስቶች ምርታቸውን ለገበያ የሚያቀርቡት በነሱ ጎሳ ቋንቋ ሳይሆን አብዛኛው ሸማች በሚገባው ቃል ነው ።

ይህ የቋንቋ እድገት ሳይንስ ነው ፣ ፖለቲከኞች ያሻቸውን ወረቀት ጽፈው በየቢሮው መደርደር ይችላሉ ።

ስለዚህ ዝም ብላችሁ ኢትዮጵያን አስተውሉ ፣ 90% ያገሪቱ ብሄራዊ ስራ ሚሰራው ባማርኛ እና እንግሊዝኛ ነው ። ይህን ነው ብርሃኑ ነጋ ያለው ። 90% የጎሳዎች ስራ ሚሰራው በጎሳዎች ቋንቋ ነው ። ይህን ማስተዋል ሮኬት ሳይንስ አይደለም ።
Last edited by Horus on 15 Apr 2021, 15:48, edited 1 time in total.

Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ብሔራዊ ቋንቋዎች እና የስራ ቋንቋዎች

Post by Naga Tuma » 15 Apr 2021, 10:55

Horus wrote:
15 Apr 2021, 00:20
እኔ እስከ ሚገባኝ ድረስ ይህ በመሰረቱ ደደብ ጥያቄ ነው ።

ኦፊሴል ቋንቋ ማለት የመንግስት ቋንቋ ማለት ነው ። የመንግስት ቋንቋ መንግስት የመንግስት አገልግሎት የሚሰጥበት ቋንቋ ማለት ነው። አገልግሎት ሚሰጣቸው ዜጋዎች ናቸው ። ያ ህዝብ በሚገባው፣ በሚግባባበት ቋንቋ አገልግሎት ይሰጣል። እኔ በምኖርበት የአሜሪካ ከተማ ያሜርካ መንግስት (ፌዴአል፣ እስቴት፣ ካዉንቲ፣ ሲቲ) ባማሪኛ፣ ሱማሌ፣ ትግርኛ፣ ኦሮሞኛ አገልግሎት ይሰጣል ። ማለትም የተጠቃሚው ሰው ቁጥር ይወስነዋል ማለት ነው ። አላማውም የብሄር ጥያቄ ሳይሆን ያገልግሎት አቅርቦት መብት ነው ።

ይህ በቀጥታ የኢትዮጵያ ፌዴራል መፍትሄ ነው ። በኢትዮጵያ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የዞን፣ የክልል ፌዴራል መንግስታት አሉ። ስራቸው በውስጣቸው ላሉ ሰዎች አገልግሎት መስጠት ነው ። ለምሳሌ የሻሸመኔ ከተማ ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎች፣ ኦሮሞኛ ማያውቁ ሰዎች እዚያ ከተማ ሄደው እንዲኖሩ፣ እንዲሰሩ ፣ ታክስ እንዲከፍሉ የሚፈልግ የሚያበረታታ ከሆነ ለነዚያ ሰዎች በቋንቋቸው አገልግሎት መስጠት አለበት ። ሌላው ቢቀር አሰርጓሚ በመቅጠር ።

ይህ የመንግስት ቋንቋ የብሄራዊ ቋንቋ ሰብሴት (አንድ ክፍል ነው) ። ብሄራዊ ቋንቋ የዚያ ብሄር ህዝብ ቋንቋ ነው ። በኢትዮጵያ ብሄር ወስጥ 80 ጎሳዎች እና 80 ቋንቋዎች አሉ ። እነዚህ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋዎች ናቸው። የሚኖረው ጥያቄ አንድ የጎሳ ቋንቋ ሙሉ ነው ወይስ ዲአሌክት የሚል ነው ። ማለትም የተቀራራቢ፣ ተግባቢ፣ ዲያሌክቶች ስብስብ ነው ወይስ ብቻውን የቆመ ያደገ ለማለት ነው።

ስለሆነም አንድ ህዝብ ኢኮኖሚው፣ ባህሉ፣ አካባዊው፣ ገበያው ወዘተ አንድ ሆኖ ቁንቋው በብዙ ዴያሌክቶች የተለያየ ከሆነ ከዚያ ወጭ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ ይጠቀማል ። እንደ አማርራኛ ቋንቋ ያለው የሌሎች የጋራ ቋንቋ የሆነው በዚህ አይነት ነው።

መንግስት አንድ ቋንቋ በግድ ሊያስተምር አይችልም ፣ ቢሞክርም ገንዘብ ያባክናል እንጂ አይሰራም ። በአንድ ገበያ ውስጥ የሸማቾችን ቋንቋ መማር ያለበት ሻጩ፣ ነጋዴው ነው ። ስለዚህ ዶርዜ ለኦሮሞ ጥበብ መሸጥ ከፈለገ ኦሮምኛ ማወቅ አለበት ። ኦሮሞ ለዶርዜ ስንዴ መሸጠ ከፈለገ ዶርዜኛ ማወቅ አለበት ። ህዝብ ቋንቋ የሚማረውና የሚመርጠው በዚህ መንገድ እንጂ ኦነግ ሸኔ ኦሮሞኛ በሌሎች ላይ ለመጫን ብረት ስላነሳ አይደለም።

ወደፊት የተፈለልገውን ያህል ቋንቋዎች ብሄራዊ የሚል ቅጽል ሊለጠፍላቸው ይችላል። ያ ሁሉ ወረቀት ላይ ይቀመጣል ። ህዝቡ ራሱ በፈቃዱ የሚማራቸው የገበያ፣ የትምህርት፣ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የፍልስፍና፣ የአርት ወዘተ መሳሪያ፣ መስሪያ የሆኑት የመላ ኢትዮያዊያን የጋራ ቋንቋ ሆኖ ይወጣል ፣ ልክ እንደ ዛሬ አማርኛ ማለት ነው። ማለም 80 ጎሳዎቹን ሁሉ የሚያግባባ ማለት ነው።

አንድ ቋንቋ የሁሉም የጋራ መግብቢያ የሚሆነው ሁሉም ጎሳዎች በዚያ ቋንቋ ሁልም ወይም አብዛኛውን ነገር ሊሰሩበት ሲያስቻልቸው ነው። አንድ ቋንቋ የሁሉም የጋራ የሚሆነው ራሱ ያደገ፣ በቀላሉ መናገርና መጻፍ የሚቻል፣ ሁሉም አይነት የሰው ህይወት እና ስራዎችን መግለጽ የሚችል ሆኖ ሲያድግ ነው እንጂ ማጆሪቲ ስለተናገረው አይደልም። አማራኛ ብዙ አማራ ይናገረዋል፣ በአፋር ህይወት ወስጥ ምንም ሚና ከሌለው አፋር ባማግርኛ ላይ ግዜ አያጠፋም ። ግ ን አፋር አማራኛ በማወቁ እቃውን ለመሸጥ፣ እውቀት ለማካበት፣ አማራ ሄኦ እውቀቱን ለመሸጥ ከጠቀመው አፋር አምራ ባይሊንጓል ይሆናል ማለት ነው ።

ስለዚህ ባዶ የፖለቲካ መዶናቆር ዋጋ የለውም ። ቴክኖሎጂ ወጥ እስታንዳርድ ቋንቋ አለው ። ካልቸርም እንዲሁ ገበያ አለው። ዛሬ 80 ጎሳዎች ሁሉም በራሳቸውን የራሳቸውን ካልቸር ያመርታሉ። በዚህ የቴክኖሎጂና የካልቸር ገበያ ለመክበር የሚጣደፉት ፈጣሪዎች፣ አርቲስቶች፣ ኢንዱስትሪያሊስቶች ምርታቸውን ለገበያ የሚያቀርቡት በነሱ ጎሳ ቋንቋ ሳይሆን አብዛኛው ሸማች በሚገባው ቃል ነው ።

ይህ የቋንቋ እድገት ሳይንስ ፣ ፖለቲከኞች ያሻቸውን ወረቀት ጽፈው በየቢሮው መደርደር ይችላሉ ።

ስለዚህ ዝም ብላችሁ ኢትዮጵያን አስተውሉ ፣ 90% ያገሪቱ ብሄራዊ ስራ ሚሰራው ባማርኛ እና እንግሊዝኛ ነው ። ይህን ነው ብርሃኑ ነጋ ያለው ። 90% የጎሳዎች ስራ ሚሰራው በጎሳዎች ቋንቋ ነው ። ይህን ማስተዋል ሮኬት ሳይንስ አይደለም ።
እስቲ እኔ ባጭሩ በጠየኩት እና ኣንተ በሰፊዉ በዘረዘርከዉ መካከል ምን ያህል መሠረታዊ ልዩነት ኣለ? ኣሜሪካ ዉስጥ ኣንተ ያስተዋልከዉን ሳላስተዉል እና ሳላስብ ነዉ ኣንተ ደደብ ጥያቄ ለማለት የሚቃጣህን የጠየኩኝ? ወይስ ፈትፍተዉ ካላጎረሱህ ኣኝከህ መዋጥ ኣትችልም? ወይስ የተማሪ ኣብዮት ያደነቆረዉ ሆነህ ቀርተህ ከኣብዮቱ በፊት ጀምሮ እስከዛሬ ህዝባችን ከጫፍ እስከጫፍ ዕለታዊ ኑሮዉን እንዴት እንደሚመራ ኣይኖችህን ገልጠህ ማየት ኣቃተህ?

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ብሔራዊ ቋንቋዎች እና የስራ ቋንቋዎች

Post by Horus » 15 Apr 2021, 12:50

ናጋ ቱማ፤ እኔ ሃሳብ የሰጠሁት አንተ ባልከው ላይ አይደለም፣ የብርሃኑ ነጋን አባል በተሳደበው ሰው ላይ ነው ። በመሰረቱ ካልከው ጋር ብዙ ልዩነት የለኝም ። ብርሃኑ አማርኛ የስራም ብሄርዊም ቋንቋ ነው ያለውን ነው ለማሳየት የሞከርኩት ። ኬር!

Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ብሔራዊ ቋንቋዎች እና የስራ ቋንቋዎች

Post by Naga Tuma » 15 Apr 2021, 14:12

ሆረስ፣

መልስህን ካነበብኩ በኃላ ተመልሼ የእኔንም፣ የኢፕአርዲኤፍንም ሀሳቦች እንደገና ኣነበብኩኝ።

የኔ ጽሁፍ ዉስጥ ኣስራ ኣንድ ጥይቄዎችን ከነጥያቄ ምልክቶች ጋር ቆጠርክኝ። ሌልው ጽሁፍ ዉስጥ ኣንድም ጥያቄ ወይም ጥያቄ ምልክት ኣላየሁም።

ያንተ ጽሁፍ የመጀመርያ አረፍተነገር ውስጥ “በመሰረቱ ደደብ ጥያቄ ነው” የሚል ሀረግ ኣለ።

ስለዚህ ያንተ ጽሁፍ ለእኔ ጥያቄዎች መልስ እንደሆነ ነዉ ያነበብኩኝ።

መልስህ ኣንድ ጊዜ ስለ ኮሚንዩኬሽን ኣስቸጋሪነት የወሰድኩትን ኣጭር ስልጠና ኣስታወሰኝ። ስልጠናዉ ዉስጥ ሁለት ሰዎች ሲነጋጋገሩ ስድስት ሰዎች እንደሚነጋገሩ ቁጠሩ የሚል ሀሳብ ኣለ። ኣንድ ተናጋሪ ለመናገር ያሰበው፣ የተናገረዉ፣ እና ከተናገረ በኃላ የተናገርኩት ይሄ ነዉ ብሎ የምያስበዉ ሲዘረዘሩ እንደሶስት ሰዎች ማየት ይቻላል ይላል። በሰሚዉም በኩል እንደዛዉ። ይህ ማለት እማጂኔሽን እና ቨርባላዜሽን መሃል ክፍተት ሊኖር ይችላል ማለት ነዉ።

ለማብራርይህ ኣመሰግናለሁ። ኬር።

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ብሔራዊ ቋንቋዎች እና የስራ ቋንቋዎች

Post by Horus » 15 Apr 2021, 14:51

ናጋ፣
በትክክል፣ አንተ ሙሉውን ሃሳብህ መልስ አዘል (መልስ ኢምፕላይ በሚያደርጉ) ጥያቄዎች ነው ያቀረብከው፤ ስለገባኝ እዚያ አልሄድኩም ። ጥያቄ ያልኩት በአጠቃላይ የቋንቋ ጥያቄ የሚባለውን ነው፤ ልክ የብሄር ጥያቄ እንደ ሚባለው። ልክ ነህ፣ በጥቂት ቃላት ሰፊና ውስብስብ ጉዳዮችን ኮሚዪኒኬት ማድረግ አስቸጋሪና ሪስኪ ነው። በቢሄቪየር ገለጻ (ዲስክሪፕሽን) ቲኦሪ ያለው ይህ ነው ። አንድ ተግባር ምን እንደ ሆነ ለመግለጽ የአድራጊው (አክተር) አመለካከት አለ፤ የተመልካች (ኦብዘርቨር) አመለካከት አለ ። እሱ አድራጊውን የሚገልጽበት ማለት ነው ። ሶስተኛው የተቺ (ክሪቲክ) አመለካከት አለ ። ተቺ የሚተቸው ተመልካቹን እንጂ አድራጊውን አይደለም ። በተግባሩ ፈጻሚ ላይ ሃሳብ የምንሰጥ ከሆነ እኛ ኦብዘርቨር እንጂ ክሪቲክ አይደለንም ። ለምሳሌ ከላይ ባለው የቋንቋ ክርክር ላይ ብርሃኑ የንግግሩ አድራጊ ነው ። ኢፒሪአራኤፍ የብርሃኑ ተመልካች (ኦብዘርቨር) ነው ። እኔ የኢፒዲአራኤፍ ተቺ (ክሪቲክ ነኝ) ። ግን እንዳልከው ሰዎች እነዚህን ሶስት ሚናዎች በግልጽ ስለማይለዩ የኮሚዩኒኬሽን መዘባረቅ ይፈጥራል። ሰላም!

Abere
Senior Member
Posts: 10890
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ብሔራዊ ቋንቋዎች እና የስራ ቋንቋዎች

Post by Abere » 15 Apr 2021, 17:47

በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ለማለት አልፈልግም ግን የዝሆን ያህል ገዝፎ ያለውን ሃቅ በፓለቲካ ስሜት ለመደባበቅ የሚፈልገውን ወድ EPRDF አንድ ነገር ለማለት ነው፥፤
አማርኛ ቋንቋ በመላው ኢትዮዽያ ቢያንስ 95 በመቶ ህዝብ ይግባባበታል፥፥ አሁን በዚህ ጉዳይ ነጋቱማ :ሆሩስ እና አንተ EPRDF እንኳን ሃሳባችሁን የተጋራችሁት በአማርኛ ነው ቢያንስ እስከ አሁን 350 በላይ አንባብያን ተረድተውታል - ይህን ውይይት። አማርኛ ከኢትዮዽያ አልፎ በአህጉራት ብዙዎች የሚናገሩት የበለፀገ ቋንቋ ነው። ይህ ቋንቋ በእራሱ ተፈጥሮአዊ ባህይ በብልጫ እራሱን ያስመረጠ እንጅ በፖለቲካ አንቀልባ ታዝዬ የግድ ፈልጉኝ ያለ አይደለም። መሳርያ ከመሳርያ ብልጫ እንዳለው የአማርኛቋንቋም ተመራጫ የመግባብያ ብሄራዊ ቋንቋ ነው። ታዲያ በምን ልትግባባ ነው ከድፍን ኢትዮዽያ? ጋር ወይስ ቋንቋ ፀንሰን ወልደን ኣሳድገን ብሄራዊ መግባብያ ልናደርግ ነው ? ሰው በአፉ የሚያወራበት ቋንቋ አይደለም የተቸገረው በአፉ የሚጎርሰው ዳቦ ነው ያጣው። እንደዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ከከንቱ ኦሮሙማ የመጣ የህዝብ እና የአገር ሃብት፣ ጊዜ የማያቃጥለ ነው።

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: ብሔራዊ ቋንቋዎች እና የስራ ቋንቋዎች

Post by EPRDF » 16 Apr 2021, 22:02

ደግሜ ይህን ቪድዮ ሳየው ፣ብርሃኑ ነጋ ያለው፣ ኦሮሞኛም አማርኛም የፌደራል ቋንቋ መሆን ይችላሉ ነው፣ ትክክል ነው።
አማርኛ ብሔራዊ ቋንቋ መሆን አለበት ያሉት ሁለቱ የአማራ ፖለቲከኞች ናቸው፣ የሕብሩ ኢንጂኒየር ይልቃል ና የመኢአዱ ተወካይ። ትችቴ ወደ ብርሃኑ ነጋ ሳይሆን በቀጥታ ወደ ሁለቱ ተከራካርዎች ተወስዶ እንዲነበብልኝ እማፀናለሁ። ተሳስቼ ብርሃኑ ነጋን ወነጀልኩ ይቅርታም ከክቡራንና ክብርታት አንባቢያን እጠይቃለሁ።
Abere wrote:
15 Apr 2021, 17:47
በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ለማለት አልፈልግም ግን የዝሆን ያህል ገዝፎ ያለውን ሃቅ በፓለቲካ ስሜት ለመደባበቅ የሚፈልገውን ወድ EPRDF አንድ ነገር ለማለት ነው፥፤
አማርኛ ቋንቋ በመላው ኢትዮዽያ ቢያንስ 95 በመቶ ህዝብ ይግባባበታል፥፥ አሁን በዚህ ጉዳይ ነጋቱማ :ሆሩስ እና አንተ EPRDF እንኳን ሃሳባችሁን የተጋራችሁት በአማርኛ ነው ቢያንስ እስከ አሁን 350 በላይ አንባብያን ተረድተውታል - ይህን ውይይት። አማርኛ ከኢትዮዽያ አልፎ በአህጉራት ብዙዎች የሚናገሩት የበለፀገ ቋንቋ ነው። ይህ ቋንቋ በእራሱ ተፈጥሮአዊ ባህይ በብልጫ እራሱን ያስመረጠ እንጅ በፖለቲካ አንቀልባ ታዝዬ የግድ ፈልጉኝ ያለ አይደለም። መሳርያ ከመሳርያ ብልጫ እንዳለው የአማርኛቋንቋም ተመራጫ የመግባብያ ብሄራዊ ቋንቋ ነው። ታዲያ በምን ልትግባባ ነው ከድፍን ኢትዮዽያ? ጋር ወይስ ቋንቋ ፀንሰን ወልደን ኣሳድገን ብሄራዊ መግባብያ ልናደርግ ነው ? ሰው በአፉ የሚያወራበት ቋንቋ አይደለም የተቸገረው በአፉ የሚጎርሰው ዳቦ ነው ያጣው። እንደዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ከከንቱ ኦሮሙማ የመጣ የህዝብ እና የአገር ሃብት፣ ጊዜ የማያቃጥለ ነው።
አቶ አብሬ፣
አንድ ነገር ስለ አማራ ሲወሳ ሙሾ አትውረድ። አማርኛም ይሁን ኦሮምኛ ትግርኛ ወላይትኛ የብሔራዊ ቋንቋ መሆን ሕብረ ብሔር በሆነች ኢትዮጵያ መሆን አይችሉም፣ የፌደራል ይሁን የስራ ቋንቋ መሆን ግን በህግ አግባብ ታይቶ መሆን ይችላሉ። የአንድን ቋንቋ የሕዝብ ቁጥር በብዛት ተናጋሪነት መኖር፣ የብሔራዊ ቋንቋ ዕጩ ለመሆን አያበቃውም። መልዕክቴም ያ ነው አስምሬበታለሁኝም፣ ተመልሰህ ፅሑፌን አንበው ምናልባት ትርዳው ይሆናል።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ብሔራዊ ቋንቋዎች እና የስራ ቋንቋዎች

Post by Naga Tuma » 21 Apr 2021, 19:30

ይህ ርዕስ ስር ተጨማሪ ኣስተያየት ኣሁን ተማልሼ ማየቴ ነዉ።

በጣም ቀላል የመሰለኝን ኣስተያየት እነዚህ ሁለት የሆረስ ዐረፍተነገሮች የደመደሙት ይመስለኛል፥ "በኢትዮጵያ ብሄር ወስጥ ፹ ጎሳዎች እና ፹ ቋንቋዎች አሉ ። እነዚህ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋዎች ናቸው።"

ካልተስተዋል እንደገና ማንበብ ነዉ። ካስፈለገም መልሶ መላልሶ።

Post Reply