-
- Senior Member
- Posts: 12454
- Joined: 27 Sep 2009, 19:43
- Location: Zemunda
-
- Member
- Posts: 3057
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Re: ትግሬ መጮህያ
ትንሽ ወግ ስለ ትግሬ መጮሂያ
ትግሬ መጮሂያ የተባለው ቦታ፡ በጎንደር ከተማ ውስጥ ገነት (ጎሃ) ተራራ ወገብ ላይ የሚገኝ ዋሻ ቢጤ ስፍራ ነው። ያኔ በጎንደር ነገሥታት ዘመን፡ ስሞታ ያለው ደጅ ሊጠና ያሰበና ልዩ ጉዳዪ ያለው ማንኛውም ዜጋ ከሰሜኑ የአቢሲኒያ ክፍል ጭምር ንጉሱ ወደሚገኝበት ጎንደር በአካል ሄዶ ጉዳዩን ማቅረብ የተለመደ አሰራር ነበር። ታድያ በዚያ ዘመን ትግሬ የተባለ ቤተመንግሥት አካባቢ ዝር እንዲል ኣይፈለግም ነበርና፥ ማንኛውም ትግሬ እዛው ጎንደር ከተማ ዳርቻ ላይ ሆኖ እየጮከ ከተጣራ በኋላ ነበር ጉዳዩ ትኩረት አግኝቶ የሚታይለት ይባላል።
ታድያ በዘመነ መሳፍትን ግዜ ጎንደርንና ነገሥታቱን እንዳሻቸው ያደርጉ የነበሩት፡ ጎንደር ውስጥም ምን የመሰለውን ግንብ በስማቸው “ራስ ግንብን” ያስገነቡት፡ አስቀድመው በኤርትራ በእረኝነት ሙያ ከዚያም ብላታ ተብለው አድዋን ለማስተዳደር የተላኩት፡ የኋላኋላ ራስ የሆኑት ሚካኤል ስሑል፡ ካንዱ ጎንደሬ ባለሟላቸው ጋር ወግ ያዙ።
ራስ ሚካኤል፡- ኣንተዬ፡ ለምንድን ነው ያን ማዶ “ትግሬ መጮሂያ” ያላችሁት? ኧረ ለመሆኑ ትግሬ ቤተመንግሥት አካባቢ ዝር እንዳይል የወሰናችሁት ለምንድን ነው? ምንድን ነው ምሥጢሩ’ሳ?
ጐንደሬው ባለሟል፡- ጌታየ፡ ልክ እንደስዎ (ልክ እንደ ኣሁኑ) ራስ እንዳይሆን ነዋ!
በነገራችን ላይ ከትግሬ መጮሂያ ዋሻ፡ ውስጥ ለውስጥ እስከ አክሱምና አስመራ ድረስ የሚያደርስ መንገድ አለ የሚል አፈታሪክም ኣለ። ስለዚህ ቅዱስ ያሬድን ካፈለቀችው ትግራይ የበቀለችው ዱቄት የሆነችው ሕወሓት በዚ ዋሻ ተሽሎክሉካ እዚም እዚያም እንዳትበጠብጥ የዲጅታሉን ድር ብቻ ሳይሆን የውስጥ ለውስጡን ድርም በጥንቃቄ መፈተሹ ኣይከፋም ቢለናል!
ክብር ለሓበሻው ሊቀ ሊቃውንት ለትግሬው ለቅዱስ ያሬድ!
ኢትዮጵያ በተለይም ትግራይ፡ ቅዱስ ያሬድን የሚያክል ትልቅ ሰው ስላበረከትሽልን እናመሰግንሻለን። ትዕቢተኞቹንና ልካቸውን የማያውቁትን ሌቦቹን ሕወሓቶችን ግን ባትወልጃቸው ይሻልሽ ነበር።