Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ዛሬ በዓድዋና አካባቢዋ ዜጎች ተገደሉ። ታዲያ እስከመቼ ነው እንዲህ የሚቀጥለው?? ምን ያህሉን ህዝባችንን ካጣን በኋላ??? የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊ ትግራወይቲ ፍረወይኒ ገ/ፃዲቅ

Post by sarcasm » 12 Apr 2021, 20:18

ትግራይ ላይ ከ5 ወር በፊት ተከስቶ በነበረው ውጊያ በርካታ ጉዳቶች ( ጥፋቶች) መከሰታቸው እና አሁንም የተረጋጋ ሰላም ካለመኖሩ በተጨማሪ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ዜጎቻችን ከቤት ንብረታቸው ገሚሱ በዝርፊያ ገሚሱም አሁንም ድረስ ሰላም እና ምግብ በማጣት ሳቢያ በመቐለና ሌሎች የክልሉ ከተሞች ተጠልለው ይገኛሉ።

በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል ትግራይ እንደ ክልል አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ወድቃለች ። የጦርነት አስከፊ ገፅታ ከሚባለው በላይ ያውም በኛ የትውልድ ዘመን እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ህዝብ አላስፈላጊ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል።

በሚሊየን የሚቆጠር ህዝብ ያለበት የአገሪቱ አንዱ ክፍል ጥቂቶች በፈጠሩት የህግ ጥሰት ሰላም መረጋጋት ምግብ መድሐኒት መጠለያ እና አልባሳት አጥተው የሰሚ ያለህ እያለ ይገኛሉ።

ክልሉ ላይ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተገን በማድረግ የኤርትራ ወታደሮች ዝርፊያ የጅምላ ግድያና የሴት እናት እህቶቻችንንም ደፍሯል ።

በወልቃይትና ራያ ይኖሩ የነበሩ ተጋሩ ቤት ንብረታቸው ወድሟል ተሰደውም ከራያ የተፈናቀሉት በመቐለ ከወልቃይት የተሰደዱት ደግሞ በሽሬ ት/ ቤቶች ውስጥ ተጠልለዋል።


በየቀኑ ከትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች እና ገጠሮች ምግብ ፍለጋ መቐለ ሽሬ እና ዓዲግራት እየመጡ ቁጥራቸውም ከፍተኛ እየሆነ ነው ለዚህም ነው "ሚሊየኖች ችግር ውስጥ ናቸው" የምንለው። በዚህ ሰዓት የመሰረተ ልማት ውድመትን እና የመንግስት ተቋማትን ጨምሮ ፋብሪካዎች እንዲሁም የግዙፍ ፕሮጀክቶችን ዘረፈና ውድመት መዘርዘር ለእኔ ቅንጦት ነው።

የሆነው ሆኖ አሁንም በክልሉ ያልተጠናቀቁ ውጊያዎች በመኖራቸው በተለያዩ ስሜታዊ በሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ብዙ ወጣቶች እና እድሚያቸው ጥይት ለመሸከም ያልደረሱ ህፃናት ፈልገውም ይሁን በሁኔታዎች አስገዳጅነት የክልሉን ልዩ ሀይል ለመቀላቀል ወደ ጫካ እየወረዱ ይገኛሉ።

በዚህ ሁሉ ውስጥ በግዚያዊነት ክልሉን ለማረጋጋትና ወደ ነበረ ሁኔታው ለመመለስ ተብሎ በፌደራል መንግስት አማካኝነት የተቋቋመው ግዚያዊ መስተዳድር አባላት ወይም ግዚያዊ አስተዳደሮች ቁጥር በጣም ውሱን መሆናቸው ይታወቃል።

በኮማንድ ፖስት እየተመራች ያለችው ትግራይ አሁን ህዝቡና ክልሉ ያለበትን ችግር ተረድቶ ቅድሚያ በመስጠት የገጠመውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ብቃት ያለው ምሁር ባለሞያ ወይም ወጣት ፖለቲከኛ ጠፍቶ ነው???

"በውጊያ አሊያም በጦርነት የሚመጣ ለውጥ አለ" ብሎ በማመን በየጫካው ነፍጥ ያነገቡ በቅርበት የምናውቃቸው ምሁራን እና ፖለቲከኞችን ሳይቀር እያየን እየሰማን ነው። ይሁን ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ ዛሬን ጨምሮ በዓድዋና አካባቢዋ ዜጎች እየተገደሉ መሆኑን የፌስ ቡክ ጓደኞቼ ሲፅፉ ተመልክቻለው ይህም እጅግ በጣም ያማል።

ታዲያ እስከመቼ ነው እንዲህ የሚቀጥለው?? ምን ያህሉን ህዝባችንን ካጣን በኋላ???

በርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በየአቅጣጫው ችግሮች አሉ ዜጎች ይገደላሉ ይሰደዳሉ ቤት ንብረታቸው ይወድማል ግን ቢያንስ ቁመና ያለው የክልል መሪ አሏቸውና በመከላከያና በፀጥታ ክፍል አማካኝነት ውድመት እንዲቀንስ ይደረጋል።

የየክልላቸውን ችግር ለመፍታት እና ለማረጋጋት ወጣቶቻቸው ይመክራሉም ተሳታፊ ሆነውም ይንቀሳቀሳሉ። ይመካከራሉ ይግባባሉ ይወቃቀሳሉ። በልዩነትም ይሁን በአንድነት ቆመው ስለክልላቸው ህዝብና መሪ ይነጋገራሉ። ይህ አይነቱ ተግባር ሰላምና መረጋጋትን የምትለምነው የትግራይ ወጣቶች በሚሊየን የሚቆጠረው ህዝቦቿ ችግር ላይ የወደቁባት የትግራይ ፖለቲከኞች መመገብ መልበስ እና ሰላማዊ የመኖሪያ ስፍራን የናፈቁ እናት አባት ያሏት በመድሐኒት እጦት ነብሳቸውን እያጡ እና

እየተሰቃዩ የሚገኙ የበርካታ ታካሚዎች የነብሴን አድኑኝ ጥሪ የሚሰማባት ትግራይ ክልል

#ስለምን ወጣቶቿ እና ምሁራኖቿ ምርጫቸውን ጫካ እና ውጊያ አደረጉ???

ይህንን የክልሉን ወጣት ፍላጎት እና ድርጊትስ "ተው " ብሎ አገራዊ መግባባትን እና የህዝቦች ውይይት እና ምክክር በማድረግ አገርንም ሆነ የአንድ ክልልን ህዝብ ከመፈራረስና ከመበታተን ለመታደግ ሁኔታዎችን የሚያመቻች እና ሃሳብ የሚያቀርብ የአገራችን ፖለቲከኞች ምሁራኖች አገር ወዳድ ዜጎች እና ከፍተኛ የመንግስት አካላትስ ለምን ጠፉ???

የትግራይ ጉዳይ የመላ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ነውና አሁንም ለመመካከር እና መግባባት ላይ ለመድረስ አልረፈደም ። #ፖለቲከኞቻችን ምሁራኖቻችን እና የመላው ኢትዮጵያ ክፍል የምትገኙ ወጣቶች ንቁ ትግራይ ከዚህ በላይ ይበቃታል እንመካከር አንድ መሆናችንን የማንለያይ ህዝቦች መሆናችንን በተግባር እናሳይ!!!!!





Yonas Junta Hagos
Well, መንግስት ይህንን ችግር ሊፈታው እንደማይችል ግልፅ ነው። ምክንያቱም የችግሩ ሁሉ ጠንሳሽና ዋና ስራ አስኪያጅ እሱ ስለሆነ። እነ ኤርትራም ሆነ እነ ፋኖ እዚያ ያሉት መንግስት ስለፈቀደላቸው መሆኑን አለመርሳት ቢያንስ ወደ እውነታው በጥቂት ኢንቾች መጠጋት ነው።
ሕፃናትን ጨምሮ ምሁራን ሁሉ ጠቅልለው ወደ ጫካ እየወረዱ ያሉት ከዚያ የተሻለ መፍትሔ ስለጠፋ ነው። አንቺ መፍትሔውን ከችግሩ ፈጣሪ ከመንግስት እየጠበቅሽ ነው። እነርሱ ደሞ ከዚያ ግድም ተጨማሪ ችግር እንጂ መፍትሔ እንደማይመጣ ደምድመዋል።
· 5 h


Author
Frewoini G Tsadik
Yonas Junta Hagos ዮኒ መፍትሄውን ከመንግስት ብቻ አልጠብቅም። ከክልሉ ተወላጅ ውጪ የሆኑትም መላው ፖለቲከኛ እና ምሁራን መፍትሄ አፍላቂ እና አጋዥ መሆን እንዳለባቸው እንዲሁም እንዲያስቡበት ነው የፃፍኩት ነገ እንዳይቆጨን ነው።
· 5 h
Yonas Junta Hagos
Frewoini G Tsadik ነገ ዛሬ እየሆነ ካለው መዓት የከፋ ምን ይመጣል ብለሽ ፈራሽ?
ሕፃናት ወንዶች በየቦታው ተፈልገው እየተገደሉ ነው።
አንድ ቤተሰብ በሙሉ በረሐብ ያለቀበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
መሰረተ ልማቱን ተይውና ከአርሷደር ማሳ እንኳ ምህረት ሳታገኝ በየቦታው እየተቃጠለ ነው።
ከዚህ የባሰ ዘር ማጥፋት ወንጀል የከፋ ምን ይመጣልና ይቆጨናል ብለሽ ነው?
· 4 h

Author
Frewoini G Tsadik
Yonas Junta Hagos የሆነውና የተፈፀመው ግፍ ከዚህ በላይ መቀጠል የለበትም አሁንም ሚሊየኖች አሉ ቢያንስ ስላለው እናስብ መወቃቀሱና እልህ መጋባቱ የባሰ ጉዳት ነው ቢያንስ የተፈፀመውን በደል ለመጠየቅም ህዝብ መኖር አለበት አሁንም አልረፈደም በየቀኑ የሚሰማውና ግዜው በረዘመ ቁጥርም ጉዳቱ አይደለም እንደ ክልል እንደ አገርም ኪሳራና ጥላሸት ነው!


Dejat Kahsay
ሃሳቡ የዘገየ ቢሆንም መልካም የሚባል ነው።
ነገር ግን ወጣቶች ለምን ጫካ መውጣት ምርጫቸው ኣደረጉ የሚለው ትክክለኛ መልሱ
"የነፃነት እና ሉኣላዊነት" ጉዳይ ነው።



Biniam Girmay
ምንም ያልታጠቁ አያሌ ገበሬዎች እና ወጣቶች ከበላይ አካል መምርያ የተሰጠ በሚመስል መልኩ ከቤታቸው እያወጡ በአሰቃቂ ሁኔታ የሚረሽኑ የኤርትና የኢትዮጵያ አረመኔ ወታደሮች ባሉበት ስፍራ ወጣቶች ወደ ጫካ ባይሄዱ ነበር የሚገርመው ምንስ ሌላ አማራጭ አላቸው ።

https://www.facebook.com/fre.woini.9/po ... 3859444710