Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የምናኔ ህይወትም ተከለከልን!

Post by sarcasm » 11 Apr 2021, 09:36

ከአቅም በላይ ነው፥ የምናኔ ህይወትም ተከለከልን!
(Eshi የት እንሂድ?) 😠😡

ከፀጥታ:

እንደ ማንታመን ተቆጥረን ከመከላከያ ጨምሮ ከሁሉም የፀጥታ ተቋማት* እየተለቀምን ተባረርን፣ ታሰርን፣ ተገደልን... የተቀረነውም በየካምፑ የዕርድ ቀኗ እንደምትጠብቅ የበግ መንጋ ያለ ምንም ጥፋት "ተጋሩ" በመሆናችን ብቻ ታጉረን እንድንቀመጥ ተደረግን... (በብዙ የጋራ መኖርያ አከባቢዎች፣ ካምፖች እና እስር ቤቶች በመዘዋወር በማጥናትና ማረጋገጥ ይቻላል!)

ከስራ:
ከተለያዩ የስራ ክፍሎች (እንደ ኤርፖርት ያሉ ድርጅቶች) "ትግሬ" እየተባልን በቤት እንድንቀመጥ ብሎም ጨርሶ እንድንባረር ተደረግን... በውሸት ክሶች ተወንጀልን ታሰርን ተገላታን...

ከፓለቲካ:
በነፃነት ስለ መጪው ዕድላችን ይሁን ስለ አሁናዊ ሁኔታ ተደራጅተን እንዳንንቀሳቀስ "ጁንታ" እየተባልን ተሳደደን፣ ታሰርን፣ ተገደልን... በዚህ ዓለም ለማንም የሰው ልጅ የተሰጠ መብት ተጠቅመን የራሳችንን ዕድል በራሳችን እንዳንወስንና የተረጋጋ ስርዓተ መንግስት እንዳናንፅ... የውይይት መድረክ ተዘግቶ የውጭ ቂመኛ ስርዓት በመጋበዝ በጦርነት መንግስትና ስርዓት አልባ ህዝብ እንድንሆን ተደረግን...

ሃብት:
ሃብት ንብረቻን በወራሪዎች ተዘረፍን፣ ነደደ-ተቃጠለ፣ እንስሳቶቻችን ተነዱ፣ ታረዱ፣ ተጨፈጨፉ... የመኖርያ ቤቶቻችንም ሆን ተብሎ ወደሙ፣ የእርሻ መሳርያዎቻችን በእሳት ተማገዱ... purposely የዘር እህላቻችን ካለ ዘሩ እንዳይለይ ተደርጎ ተቀላቀለ*... ተቃጠለ ከፈር ጋር ተደባለቀ፤ የቢሮና የቤት ንብረታችን ከፋብሪካ፣ ዩንቨርስቲ፣ መኪኖች፣ ፌሮ ጀምሮ እስከ ደቃቃ ቅያሬ ልብስ፣ ጫማ፣ መርፌ፣ ማንክያና ድስት ጭምር ተወረረን... በስርዓት ተጭነው ተጓጓዙ...

ሰብአዊ መብት ጥሰት:
እህቶችችን ተደፈሩ፣ ንፁሃን ወገኖቻችን ያለምህረት ተጨፈጨፉ፣ ተገድለውም ወደ ገደል ተወረወሩ፣ ህፃናት፣ ሴቶች እናቶች አባቶች ያለ ምንም ልዩነት በገዛ ቤታቸው በጥይት ተቆሉ፣ በእሳት ነደዱ... ህመማችን ሃዘናችንም እንዳንገልፅ ሁሉም መብት ተከለከልን፤ እንዳናለቅስ እምባችን እንዳናወጣ እንኳን በግልፅ ተካድን...

ግዛት:
እትብታችን የተቀበረበት ተወልደን ካደግንበት ቄያችን ተዘርፈን ተባረርን፣ ግዛታችን ወራሪዎች ሰፈሩበተ፣ በዚህ ዘመን በዓለም በየትኛውም ሃገር ህዝብ ይደረጋል ተብሎ የማይገመት: ህዝባችን አባርረው፤ ቤቶቹ የበር ቁልፉን ሰብረው ገብተው ኖሩበት፣ ምጣዱን አሟሽተው ያቦካውን ሊጥ ጋገሩበት፤ በሳህኑ አቅርበው በሉበት፣ በአልጋው ተኙበት፤ ባለጉበት፣... (ቅኝ ግዛት በዓለም የተወገዘ በህግም የተከለከለ ነው፣ ግን የቅኝ ገዢዎች እንኳን እንዲህ ያለ የወረደ ተግባር ያደርጋሉ፤ ይህን የሚስተካከል ሰይጣናዊ ጭካኔ ይፈፅማሉ የሚል አላነበብኩም! አልሰማሁም... እንዴት የሰው ልጅ ሌላውን ወገኑ ኣባርሮ በቤቱ ገብቶ አልጋው ላይ ይተኛል?!☝)

የማንነት ጥቃት ሰለባ
ፓስፖርት ይሁን መታወቅያ: የማንም ዜጋ መብት የሆነው ማንነትን የሚገልፅ ፓስፖርት ለማግኘት እንኳን "ትግሬ ስለ ሆነ ይጣራ" እየተባልን ከዜጋ በታች ተቆጥረን እየተንገላታን ነው

ምናኔ:
በስተ-መጨረሻም በአያሌ የውሸት ትርክቶችና በየጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ብዛት... በማንነታችን ምክንያት የምናኔ ህይወት: የዓለም በቃኝ ይህወትም ጭምር ተከለከልን... የጭካኔ የክፋት ጽግ ነው☝... በምንም ዓይነት መለክያ ማስተባበል እንኳን የማይቻል ግፍ 😠 አንድ ሰው ዓለም በቃኝ ብሎ ቢመንን ምኑንን ልትዘርፍ? የትኛውን ሃብቱ ልትወርስ ነው የምታባርረው? መንናንያንስ ዘር አላቸው እንዴ?
ቧእእእ! 😡
እሺ ምን እናድርግ... ምን እንሁን... የትስ እንሂድ?!
.

.
.
👉 (መንእሰይ ትግራይ: ትግራይ ዝበፅሐላ ብሕታዊ መለኮታዊ ሓይሊ እንተልዩ ኣብ ሕልናኻ እዩ ዘሎ፣ ከምዚ እንትደክም ዝሽከማ እንተልዩ እንግዳዓኻ እዩ፣ ጎይዩ ዝፅሐላ ዝድግፋ እንተሎ ብርክኻ እዩ፤ ካብ ትግራይ ኣይትህደም! እምቢ ንጭቆና በል፥ ብልቢ ተጓዓዝ፣ ሓድነትካ* ኣስጥም፤ ብኩሉ ኣብ ኩሉ ግጠም፣ ኣይትሰኮን ኣይትህደም፣ just ግጠም!)
.
.
.
🙅ወራሪ ሃይሎች በሰራዊት ብዛትና ባላቸው የመሳርያ ብዛት ለጊዜው ጨቁነው ሊይዙህ ይችላሉ ግን ሐቅ እና ፍትህ የያዘ ህዝብ* ምንም አይሸነፍም፤ በጭቆና ስርም አይኖርም! በዚህ ዘመን ይህ ፍፃሜ ትግራይ ለዓለም አብነት ሆና የምታስተምረው እውነተኛ ታሪክ ነው! ቃል ለምድር ቃል ለሰማይ...
#ንፅናዕ_ትግራይ_ትስስዕር ✊
Please wait, video is loading...