Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4191
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Russsia said that it has interest to help Ethiopia to use nuclear

Post by Abaymado » 11 Apr 2021, 07:10

Only 10 years is enough to use it for specific purpose.

ከመረጃ ምንጩ እንደተረዳነው ኢትዮጵያ የኒኩልየር ተጠቃሚ ለመሆን አስር ይበቃታል ነው የተባለው:: ግን የኒኩልየር አገራት አባል መሆን ይጠበቅባታል::

https://www.facebook.com/AmharaMediaCor ... 9631626359


Amhara Media Corporation

ሩሲያ የቀጣናውን ደኀንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች፡፡
የኒውክሊየር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ተግባር ለማዋል ከኢትዮጵያ ጋር እንደምትሠራም ገልጻለች፡፡

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ የራሷን እና የቀጣናውን ደኀንነት ለመጠበቅ በምታደረገው ጥረት የሩሲያ መንግሥት ድጋፉ እንደማይለያት የሩሲያ አምባሳደር ያቭጋኒ ተርክን አስታወቁ። ሀገራቸው የኒውክሊየር ቴክኖሎጂን ለሠላማዊ ተግባር ለማዋል ከኢትዮጵያ ጋር እንደምትሰራ ገለጹ።
አምባሳደሩ እንዳስታወቁት፣ የሩሲያ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ደኀንነትን ለማጠናከር በተለያየ መንገድ ድጋፍ እያደረገ ነው። የቀጣናውን ደኀንነት በተሻለ መልኩ ማጠናከር የሚቻለው ፖሊቲካዊ መፍትሄዎችን በማጠናከር እንደሆነ ያመለከቱት አምባሳደሩ፣ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያና ሩስያ ለበርካታ ዓመታት በትብብር ሢሠሩ መቆየታቸውን አመልክተዋል ።
በተለይ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል በነበረችበት ወቅት በጉዳዩ ላይ የተለየ ትኩረት በመስጠት መሥራታቸውን ጠቁመዋል።
የሀገሪቱን ደኀንነት እና ፀጥታ በዋናነት ማስጠበቅ የሚችለው የኢትዮጵያ መንግሥት ነው፤ ይህንን መቀበል አለብን ነው ያሉት፡፡ማንኛውም ሀገር የራሱን ደኀንነት ለመጠበቅ ከሁሉም ቅድሚያ የኢኮኖሚ አቅሙን ማሳደግ እንዳለበት የጠቆሙት አምባሳደሩ፣ በዚህም የሀገራችው መንግሥት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሩሲያ የቀጣናውን ደኀንነት ለማጠናከር የምታደርገው ጥረት ሁለንተናዊ መልክ እንዳለውም አመልክተዋል። በቀጣናው ሠላምና መረጋጋትን ለማምጣት ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ እያደረጉት ያለው ጥረት የሶስቱ ሀራት ጉዳይ ቢሆንም ፤ የሀገራቱን ጥረት ሩሲያ እንደምትደግፍ አስታውቀዋል።

"ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና ግዙፍ ሀገር ናት፤ የቀጣናው ሀገራት የደኀንነት ጉዳዮች የሚወስኑት በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ነው" ያሉት አምባሳደሩ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም እና ደኀንነት የሚሰፍን ከሆነ የቀጣናው ሰላም እና ደኀንነትም የተሻለ ይሆናል ብለው እንደሚያምኑም አብራርተዋል።
ሀገራቸው የኔውክሌር ኀይልን ለሠላማዊ ተግባር ለማዋል ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እንደምትሠራ የጠቆሙት አምባሳደሩ፤ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ተጠቃሚ ሀገሮች አባል ከሆነች እኛ ለመርዳት ዝግጁ ነን ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እ.አ.አ 2019 በሩሲያ ባደረጉት የሥራ ጉብኝት እንዲሁም በቅርቡ በተካሄደው በአፍሪካ-ሩሲያ መድረክ ላይ ተገኝተው እንደገለፁት በኒውክሌር መስክ መሰረታዊ ፍላጎት እንዳላቸው መረዳታቸውን ጠቁመዋል።


የሁለቱ ሀገራት ወቅታዊ የኔውክሌየር የትብብር ስምምነት በዚህ ዓመት ታህሳስ ላይ የኢትዮጵያ ፓርላማ የኒውክሌር ኀይልን ለልማት መጠቀም የሚያስችለውን ስምምነት ካፀደቀ በኋላ ተግባራዊ መሆኑን አመልክተዋል።

በዘርፉ ተጨማሪ አዳዲስ የመግባቢያ ሰነዶችን ለመፈራረም መዘጋጀታቸውን የጠቆሙት አምባሳደሩ፤ ስምምነቶቹ የኒውክሌር ኀይል አጠቃቀም በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚረዱ በአቅም ግንባታ ላይ ያተኮሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

የኒውክሌር ትብብር በኀይል ማመንጫ ብቻ የሚወሰን እና በአጋጣሚ የሚደረግ አለመሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ፣ የኒውክሌየር የኀይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ ውስብስብ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም፤ ጊዜ፣ ጥረትና ገንዘብ የሚጠይቅ ነው ብለዋል።

የተለመደው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ የጊዜ ገደብ ወደ አስር ዓመት የሚጠጋ ነው። ግንባታው እስኪከናወን ሌሎች ተያያዥ እቅዶችን ወደ ተግባር በመለወጥ ተጠቃሜ መሆን ይቻላል ብለዋል።

የኀይል ማመንጫ ጣቢያው ከመጠናቀቁ በፊት በሕክምና ዘርፍ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ቢተገበር ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስታውቀዋል።
“በተጨማሪ በየዓመቱ ከሚሰበሰበው የሰብል ምርት ሃያ አምስት ከመቶ በበሽታዎች እና በተለያዩ ምክንያቶች ይባክናል ይህንን ለመቀነስና በሌሎችም ኢንዱስትሪዎች ላይ የኒውክሌር ኀይል ልማት ጠቀሜታ ከፍተኛ እንደሆነ አስታውቀዋል።


የኢትዮጵያ እና የሩሲያ የቴክኖሎጂ ትብብር በሌሎች የቴክኖሎጂ ማበልጸግ ዘርፎችም እንደሚቀጥል አምባሳደሩ መጠቆማቸውን ኢትዮ ፕረስ ዘገቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን