Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5625
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Shimeles' genocider committee promised it is going to destroy genocideers wink wink

Post by TGAA » 07 Apr 2021, 06:44

:wink: :wink: https://mereja.com/amharic/v2/486968

If the sheeps are get eaten up during the day and night ,you can be sure it is not the fox but the sheepherder the culprit.

የአማራና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች የሰላም እና የጸጥታ ችግሮችን ተቀናጅቶ ለመከላከል እየመከርን ነው አሉ የአማራ እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በሁለቱ ክልሎች የጋራ ሠላም እና የልማት አጀንዳዎች ላይ እየመከሩ ነዉ፡፡ በምክክር መድረኩ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በተደጋጋሚ የሚከሰቱ የሰላም እና የጸጥታ ችግሮችን ተቀናጅቶ ለመከላከል በትብብር መሥራት የሚቻልበትን ሁኔታ መፍጠር ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

በሁለቱም ክልሎች የሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን ተከትሎ በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለዉን ሞትና መፈናቀል በፍጥነት ማስቆም፣ የግጭቱ ጠንሳሾች እና ተዋናዮች ላይ አስፈላጊዉን እርምጃ መዉሰድ፣ በተከሰቱ ግጭቶች ጉዳት የደረሰባቸዉ ወገኖች ፍትሕ እንዲያገኙ እና ወንጀለኞች ለሕግ እንዲቀረቡ ማድረግ፣ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው በፍጥነት መመለስና ማቋቋም እንዲሁም በክልሎቹ ዘላቂ ሰላም ከማስፈን አኳያ በትብብር ለመሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሁለቱ ክልሎች አመራሮች በመወያየት ላይ ይገኛሉ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የኦሮሞ እና የአማራ ወንድማማች ሕዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ትስስርና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከር፣ አጎራባች ዞኖች ላይ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶችን በተቀናጀ ሁኔታ መከላከል፣ በሁለቱ ክልሎች መካከል እየተሠሩ ያሉ የመሰረተ ልማት ሥራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የዉይይቱ አንኳር ጉዳዮች ናቸዉ፡፡ በመድረኩ የሁለቱም ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በጋራ እየመሩት ነዉ፡፡