Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Roha
Member
Posts: 2122
Joined: 17 Feb 2011, 00:38

Eritrea accepts entirely PM Abiy's news release of the Asmara meeting

Post by Roha » 26 Mar 2021, 21:40

The Eritrean government has released the full translation of PM Abiy's communique of the Asmara meeting as released by the PM's Office in Addis Ababa on Eritrean government TV, websites and newspapers.
Here the official government ERi TV:



በጥቅምት 25፣ 2013 በሕወሐት ውስጥ የተሰባሰበው የወንጀል ቡድን፣ በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የከሸፈ ክህደት ፈጽሟል። በዚህም ሀገርን ወደ ሁከት በመምራት ሥልጣንን ለመያዝ መሞከሩ ይታወሳል። የሀገሪቱ ትልልቅ የጦር መሣሪያ ማከማቻዎች በሚገኙበት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙ እና የመከላከያ ሠራዊታችንን አባላት ያለ ርኅራኄ መግደሉ እና ማፈኑ የፌዴራል መንግሥት ሳይፈልግ ወታደራዊ ርምጃ እንዲወስድ አስገድዶታል።

በሰሜን እዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የሕወሐት ወንጀለኛ ቡድን በባሕር ዳር እና በጎንደር ከተሞች ላይ ሮኬቶችን መተኮሱ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይም በኤርትራ ላይ ተደጋጋሚ ሮኬቶችን ተኩሷል። ይህም የኤርትራን መንግሥት የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጦ በመግባት ከተጨማሪ ጥቃቶች ራሱን እንዲከላከል እና ብሔራዊ ደኅንነቱን እንዲጠብቅ አነሣሥቶታል፡፡

መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ወደ አሥመራ ተጉዤ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ባደረግነው ውይይት፣ የኤርትራ መንግሥት ጦሩን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት ተስማምቷል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት ወዲያውኑ ተክቶ የድንበር አካባቢዎችን ይጠብቃል፡፡

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው እና በኢኮኖሚ ትብብር ፍላጎታቸው ላይ አብረው መሥራታቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ በ2010 ዓ.ም. በተጀመረው መሠረት በሁለቱ ሀገራት መካከል በመተማመን መንፈስ መልካም የጉርብትና ግንኙነታችንን መገንባታችንን እንቀጥላለን፡፡ በተለይም፣ በትግራይ ክልል እና ከድንበር ማዶ ባሉ ኤርትራውያን ወገኖቻችን መካከል በመተማመን ላየ የተመሠረተ ግንኙነትን መመለስ በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡