Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የለውጡ ትሩፋቶች - ከየልደቱ አያሌው አዲስ መፅሐፍ ፤ 27 ሲደመር 2 ....

Post by sarcasm » 01 Mar 2021, 21:07

(መፅሐፉን ገዝታችሁ አንብቡት )

1 አምባገነናዊ መንግሥትን እየፈራን ከምንኖርበት ሀገር ( የመንደር የጎበዝ አለቆችንም እየፈራን ወደምንኖርበት ሀገር ተሸጋግረናል፤
2 መንግሥትን መቃወም ወንጀል ከሆነበት ሀገር ( መንገድ መዝጋትና ቆንጨራወደ ይዞ መሰለፈ መብት ሆነበት ሀገርም ተሸጋግረናል፤
3 ስለልዩነት እየሰበከ ከሚያዳክመን መንግስት ( ስለ አንድነት እያወራ ወደሚበትነን መንግስት ተሸጋግረናል፤
4 ንጹሐን በፖለቲካ አመለካከታቸው ከሚታሰሩበት ሀገር − በአደባባይ ሰውን ዘቅዝቀው ሰቅለው የሚገሉ ወንጀለኞች ተጠያቂ ወደማይሆኑበትም ሀገር ተሸጋግረናል፤ ሀገር
5 በምርጫ ወቅት ‘ድምጽ ይሰረቃል’ ብለን ከምንሰጋበት ሀገር ( በሕዝብ ቆጠራ ወቅት ራሱ ‘ሕዝብ ይሰረቃል’ ብለን ወደምንሰጋበትም ተሸጋግረናል፤
6 በጥቅም በመደለልና በማስፈራራት ምርጫን ለማሸነፍ ጥረት ከሚደረግበት ሀገር ( የሕዝብ ስብጥርን በመቀየር ምርጫን ለማሸነፍ ሙከራ ወደሚደረግበትም ሀገር ተሸጋግረናል፤
7 ከጎረቤት ሀገራት ጋር ጦርነት ውስጥ እንዳንገባ ከምንሰጋበት ሀገር ( ፌደራል መንግሥታችን ከአንዱ ክልላችን፣ ወይም አንዱ ክልላችን ከሌላው ክልላችን ጋር እንዳይዋጋ ወደምንፈራበትም ሀገር ተሸጋግረናል፤ እንድትሆን
8 የሀገር ዳር ድንበር እንዲከበር ከምንጠይቅበት ሀገር ( ከአዲስ አበባ ቡራዩና ለገጣፎ ደርሶ መምጣት ወደሚፈራበትም ሀገር ተሸጋግረናል፤
9 ኢትዮጵያ የሁላችንም ከምንጠይቅበት ሀገር ( አዲስ አበባ የጋራችን እንድትሆንና የመኖሪያ ፍቃድ እያደስን የምንኖርባት ከተማ እንዳትሆንሀገር ወደምንጠይቅበትም ሀገር ተሸጋግረናል፤
10 ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚዎች የከረረ ፍጥጫ ውስጥ ከሚኖሩበት ሀገር ( የገዢው ፓርቲ አባላት የእርስ በርስ ፍጥጫና መገዳደል ውስጥ ወደገቡበትም ተሸጋግረናል፤
11 ህወሓት ‘የበላይ ሳልሆን እኩል ነኝ’ እያለ ሲያሾፍ ከነበረበት ሀገር የሕግ ( ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በይፋና በድፍረት ‘ቤተ መንግሥቱ የኦሮሞ ነው’ ወደሚልበትም ሀገር ተሸጋግረናል፤
12 ‘ሰው የገደልኩት ሰላምና የበላይነትን ለማስፈን ነው’ ብሎ ከሚመጻደቅ መንግሥት ( ሰላምና የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብር ሲጠየቅ ‘ሰው ግደል ነው ወይ የምትሉኝ?’ በማለት ሃላፊነትን ያለአግባብ ወደሚሸሽም መንግሥት ተሸጋግረናል፤ ማወቅ
13 የመን ድረስ ሄዶ ተቃዋሚውን አፍኖ የሚያመጣ መንግሥት ከነበረበት ሀገር ( ልጆቻችንን ከዩንቨርስቲ አፍኖ የሚወስድ ሽብርተኛን የት እንዳለ እንኳን ወደማንችልበትም ሀገር ተሸጋግረናል፤
14 ስለግድብና መንገድ በየቀኑ በመገናኛ ብዙኀን መስማት ከሰለችንበት ሀገር ( በየቀኑ ስለ አራት ሳይንቲስቶች- ኪሎ ፓርኮች መስማት ወደሰለቸንበትም ሀገር ተሸጋግረናል፤
15 ባለሃብቶችን ኪራይ ሰብሳቢና ሙሰኞች ብሎ ከሚጸየፍ መንግሥት ( የሀገራችን ባለሃብቶች ከሀገራችን የኢኮኖሚና የፖለቲካ በላይ አዋቂዎች ዓለም ናቸው በማለት በድፍረት ወደሚናገርም መንግሥት ተሸጋግረናል፤
16 የምዕራቡንና የምሥራቁን ርዕዮተ ዓለም እያምታታ ሲያደናግረን ከኖረ መንግሥት ( የሚራምደውን ርዕዮተ በግልጽ መናገር አልፈልግም በማለት በአደባባይ በድፍረት ወደሚናገርም መንግሥት ተሸጋግረናል፤
17 የሽግግር መንግሥት ጥያቄን ሥልጣንን በአቋራጭ የመቀማት ጥያቄ ነው በማለት ከሚያሾፍ መንግሥት ( በሽግግር መንግሥት ጠያቂዎች ላይ ርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅቻለሁ በማለት ወደሚዝት መንግሥትም ተሸጋግረናል፤
18 በፖለቲካ አመለካከታችን ምክንያት መንግስት ሊገለን ጠያቂዎች ብለን ከምንሰጋበት ሀገር ( በማናውቀው ምክንያት፣ በማናውቀው ኃይል ልንገደል ወደምንችልበት ሃገር ተሸጋግረናል፤
19 ለመልካም አስተዳደር መኖር ስንታገል ከኖርንበት ሀገር ( ሥርዓት አልበኝነት ተወግዶ የአገዛዝ ሥርዓት እንዲኖረን ወደምንጠይቅበትም ሀገር ተሸጋግረናል፤
20 በአጠቃላይ፥ የዴሞክራሲ፣ የእኩልነትና የልማት ተጠቃሚነት መብት እንዲኖረን ከምንጠይቅበት ሀገር ( በድህነትና በጭቆናም ቢሆን በሰላም የምንኖርበት ሀገር እንዲኖረን ወደምንመኝበትም ሀገር ተሸጋግረናል።"

https://www.facebook.com/Eskias99/posts/244005770439336