ለምሳሌ ብዙ ግዜ የኢዜማ ምሁራን ስለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ሲያወሩ በካቲድራል ቋንቋ ነው። እኛ የጀመርነው ልጆች፣ የልጅ ልጆቻችን የፈጽሙታል ይላሉ! ያ ነው የካቲድራል አስተሳሰብ የሚባለው።
እኔ እንደ ሆረስ የሚታየኝ የኢትዮጵያ ጉዞ፣ የኢትዮጵያ አጀንዳ፣ የኢትዮጵያ እድገትና ሃያልነት ያን መሰል የካቲድራል ራዕይ ነው !!
ያ ነው የኢትዮጵያ ሳዳ፣ ያገራችን እጣ ፋንታ፣ ያገራችን ወደ ፊት ቁማ ፌት !!
ይህ የኢትዮጵያ አጀንዳ ምንድን ነው?
አንድ፣ ኢትዮጵያ የተዋሃደች፣ የተረጋጋች፣ ጠንካራ ያፍሪካ አንደኛ ወይም ሁለተኛ ሃያል አገር ትሆናለች ።
ሁለት፣ ኢትዮጵያ ዴሞክራሳዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊ ማህበረ ሰብ ትሆናለች ።
ሶስት፣ ኢትዮጵያዊያን የበለጸጉ፣ ሃብታም፣ የተማሩ፣ ጤናቸው የተጠበቀ ሕዝብ ይሆናሉ። በ2100 አንድ ቢሊዮን ሕዝብ እንሆናለን !!
አራት፣ ኢትዮጵያዊያን በፈጠራ የረቀቀ፣ ክባቢውን ያለማ፣ መንፈሳዊ ካልቸርና ስልጣኔ ይገነባሉ !!!
ይህ ነው የሚሆነው በልጆቻችንና በልጅ ልጆቻችን ዘመን !!!