Page 1 of 1

ጁባ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በመንከባለልና በመጮህ ሁከት ለመፍጠር ሞክረዋል ብለዋል ፡፡

Posted: 23 Feb 2021, 10:50
by BAGAMIDOASS
The “ EMBER TEGADALAY “ Drama continues 😀😀


ሰሞኑን በጁባ 15 የጁንታው ተላላኪዎች ወደ ሀገራችን አንሄድም በማለት ጁባ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ሁከት ለመፍጠር ሞክረዋል - ሜ/ጄ መሃመድ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በአህጉር አቀፍና በአለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ግዳጅ አኩሪ ተግባር እየፈፀመ እንደሚገኝ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄ መሃመድ ተሰማ ገለፁ፡፡

ከሰሞኑ የ15ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በጁባ የሚገኘውን ቆይታውን ላጠናቀቀው ሰላም አስከባሪ ሀይል በመቀየር ላይ እያለ ፣ 15 የሰራዊት አባላት የጁንታው ተላላኪዎች ወደ ሀገራችን አንሄድም በማለት ጁባ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በመንከባለልና በመጮህ ሁከት ለመፍጠር ሞክረዋል ብለዋል ፡፡

በመሆኑም እነዚህ የጁንታው ቅጥረኞች ፣ የሰራዊታችንን እና የሀገራችንን መልካም ስምና ዝና ለማጠልሸት ፣ በዩኤን የተለያዩ ቦታዎች ተቀጥረው የሚሰሩ የሰራዊት አባላት UNHCR የተባለውን ግብረ ሰናይ ድርጅት የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ በማመቻቸት ጉዳዩን አለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲሰማው ለማደረግ የተሞከረ እንደነበርና ፣ በዚህም UNHCR ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ያስተጋባው ዘገባ ያልተገባ መሆኑን በመግለፅ ይቅርታ ሊጠይቅ እንደሚገባ ሜ/ጄ መሀመድ ተሰማ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊታችን የጁንታውን ርዝራዦች አድኖ ለመያዝ በከፍተኛ ሞራልና ወኔ እየሰራ ባለበት ፣ በግለሰቦች እንዲህ አይነት ድርጊት መፈፀሙ ሰራዊታችንን የማይወክልና የግለሰቦች ብቻ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባዋል ብለዋል፡፡

እነኝህ የሰራዊት አባላት ሌሎችን የማይወክሉ እንደሆኑና ፣ አሳፋሪ ተግባር የፈፀሙ ስለመሆናቸው ገልፀዋል፡፡

ይህንን ተግባርም እንደ ትልቅ ነገር እያራገቡ የሚገኙ የሚዲያ አውታሮችና ተከፋይ አምደኞችም ድርጊቱን በተገቢው በመረዳት ሚዛናዊነትን በመጠቀም ሊዘግቡት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን