Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7993
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

አብይ አህመድ አብይ አህመድን "ሸለመ"!!

Post by Wedi » 19 Feb 2021, 20:02


:lol: :lol: :mrgreen: :mrgreen:
አብይ አህመድ አብይ አህመድን "ሸለመ"!!

OBN አማርኛ

ኦቢኤን የካቲት 12/2013 - ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለሶስተኛ አመት የእንኳን አደረሰዎት ሽልማት ሊበረከትላቸው ነው

ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለሶስተኛ አመት እንኳን አደረስዎ ሽልማት ሊበረከትላቸው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሾሙበትን ሶስተኛ አመት ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው ሽልማት ዶክተር አብይ አህመድን ወጣቶች እንዲያመሰግኑም ጭምር የታቀደ ፕሮግራም መሆኑ ተገልጿል።

የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማቱ የሚበረከትላቸው ለሀገራችን ላበረከቱት የሰላምና የአንድነት በጎ ሥራ ነው ተብሏል።

"ጎህ 2013 የሰላም እና የአንድነት ሽልማት" የሚል ስያሜ የተሰጠው ይሄ ሽልማት በሰላምና አንድነት ዙርያ መልካም የሰሩ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ ማህበራት፣ ሽማግሌዎች ፣ ወጣቶች እና ህፃናት የሚሸለሙበት ነው።

ኢፕድ እንደዘገበው ሽልማቱን ኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይመንትና ኢቨንት ከሰላም ሚንስትር ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጁት