Page 1 of 2

ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 18 Feb 2021, 23:34
by Horus

የዚህ ግዙፍ ጂኦፖልቲካ እምብርት ያባይ ግድብ ነው ። ማለት ኢትዮጵያ ነጻ ታዳጊ ሃያል አገር እንዳትሆን ለመግታት የተቀመረ ንቅናቄ ነው።

ኢዮትጵያን ለመግታት ፣ ለማዳከም፣ ለማምበርከክ ወይም ያን ለመቋቋም የተሰለፉት አገሮች በሶስት ይመደባሉ ።

1. ሃያላን አገሮች፤ አሜሪካ፣ ሩሲያ እና ቻይና

2. ሪጅናል አገሮች (ሃይሎች)፤ ግብጽ፣ እስራኤል፣ ቱርክ፣ ኢራን፣ ሳዉዲ አረቢያ፣ አረብ ሊግ፣ ህንድ፣ ያፍሪካ አንድነት

3. ጎረቤት አገሮች፤ ኤርትራ፣ ጂቡቲ፣ ኬኒያ፣ ሱማሌ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ናቸው።

የኢትዮጵያ አላማ ግብጽን ቆርጦ መለየት፣ ማግለል፣ አይሶሌት ማድረግ ነው። ግብጽ ከላይኞቹ 6 አገሮች ማግለልና ያላቸውን ትስስር መበጠስ ነው። ብሎም የግብጽም ሆነ የሱዳን ጦር የመውጋት ችሎታ ማክሰም ነው።

ፖለቲካ ሁልግዜ ዞሮ ዞሮ ሎካል ወይም የሰፈር ጦርነት ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያ ከኤርትራ፣ ጂቡቲ፣ ኬኒያ፣ ሱማሌ፣ ደቡብ ሱዳን ጋር ጥብቅ ትብብር ወይም ቅንብር መፍጠሯ እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ የዲፕሎማሲ ድል ነው።

ቀጥሎ ሪጅናል ሃይሎች በተመለከተ ኢትዮጵያ ከቱርክ፣ አስራኤል፣ የአፍሪካ አንድነትና ህንድ ጋር ሰፊ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ሴኩሪቲ ትብብር፣ ቅንብር በማድረግ የግብጽ፣ ኢራን፣ የስዉዲ እና ያረብ ሊግ ግፊት መመከት አለብን።

ቀጥሎ የሶስቱ አለም ሃያላኖችን አሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩሲያ ፍክክር እና ትብብር ረቂቅ በሆነ መንገድ ለመጠቀም መቻል አለበን ። ከማንኛቸውም ጋር በጋብቻ መተሳሰር የለብንም። አንዱ ሲያጠቃን ወደ ሌላው በመዞር፣ እርስ በርሳቸው በማጋጨት ጨዋታውን ማርቀቅ ግድ ይለናል።

ይህም ማለት እነዚህ ሃያላኖች አንዱ ከግብጽ ጋር ወግኖ አኛን የሚጎዳ ነገር ሲሰራ ባፍሪካ ቀንድ፣ በቀይ ባህርና በህንድ ውቂያኖስ ያላቸን ጥቅም በማናጋት ጨዋታውን ማክረር አለብን

አጠቃላይ እስትራተጂው ይህን ይመሰላል !

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 19 Feb 2021, 01:11
by Horus
ለምሳሌ ያክል አንዳንዶቹን ጉዳዮች እንመልከት፤

ቱርክ፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ እና ሳውዲ አረቢያ አራቱም የአረብ አለም መሪ ለመሆን ይፎካከራሉ ። ያ ማለት ደሞ ያካባቢው አለቃና ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ለመሆን ይፎካከራሉ ። አሁን እንደ ምናየው ኢትዮጵያ ከነዚህ አራት የሰፈር አለቆች መሃል ከቱርክ ጋር በጣም እየተቃረበች ነው።

ሳዉዲና ግብጽ ጓደኞች ናቸው። ቱርክና ኢራን ያብራሉ ። ኢራን ግን ከኢትዮጵያ ጋር ምንም ቅርበት የላቸውም፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሺአ ስላልሆኑ ።

አሜሪካና ቱርክ ጠበኞች ናቸው። የእስራኤል ቦታ ግልጽ አይደለም።

ቱርክና ሩሲያ ገጥመዋል ። አሜሪካ ወደ ግብጽ ካዳላች ኢትዮጵያ ወደ ሩሲያ መጠጋት አለባት ።

ቻይና በኛ ላይ ብዙ እዳ ስላላት በግድ እኛን መደገፍ አለባት ።

አሜሪካ ቻይናን ካፍሪካ ሊያስወጣ የኢኮኖሚ ፉክክር ያደርጋል ። ያ ፉክክር ለእኛ በጣም ጠቃሚ ነው።

እያለ የካራምቦላው ጨዋታ ይቀጥላል !

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 19 Feb 2021, 01:28
by Aurorae Borealis
Horus,

Great analysis. You should join some kind of Ethiopia think tank for foreign policy. However, you can not be a friend to everyone. It is not possible. Becoming independent is perhaps the best way to go. How can you be a friend to Kenya and Somalia at the same time ? Iran vs. Saudi Arabia, etc.... I think Ethiopia should find a way to make peace with all of its neighbors. Ethiopia needs to make great relationship with the Middle Eastern countries. The Middle Eastern issues , the owners of the corridor in the Red Sea is far more relevant than the AU unity affairs in which Ethiopia seems to bombard its foreign relations of the past. If Ethiopia wants good relations with the West in general, human rights need to be intact. The war with TPLF has tarnished a lot of that image. Abbiy can not afford to play Mengistu. Ethiopia needs to strive to become a very democratic country. It would be nice if Ethiopia preserves federalism and negotiate Ethnic politics. You throw away federalism, you invite war. But, I can understand minimizing the ethnic nature of politics. Remember, first and for most is human right. Avoid dictatorship, otherwise, Ethiopia will be no more.

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 19 Feb 2021, 02:00
by Horus
አውሮራ፣
አይዲል በሆነ ሁኒታ ያገርና የውጭ ፖሊሲ ተመሳሳይና ተደጋጋፊ ናቸው። እንዲያውም የውጭ ፖሊሲ የውስጥ ፖሊሲ ተቀጥያ ነው ። ግን ይህ ሁልግዜ የሚሳካ አይደለም ።

ዲፕሎማሲ የሚነዳው አገሩ ባለው ሃይልና በዚያ አገር ጥቅም መሰረት ነው።

ከላይ ያሉት አገሮችና ቅንጅቶች ሁሉም የርሳቸው ብሄራዊ ጥቅምና የተለያየ የሃይል መጠና ሚዛን አላቸው። ስለዚህ ጨዋታው የሚካሄው በያዝከው ካርታ ልክ ነው።

ያልካቸው ነገሮች ትክክል ቢሆኑም ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሃይልና ችሎታ ጋር ማገናዘብ አለብህ ።

ለምሳሌ እኛ ከሁሉም ጋር ጓደኛ መሆን ሳይሆን የሁሉም ተጫዋች ጥቅም ምን እንደ ሆነ አውቀን በዚያ መሰረት መጫወት መቻል አለብን ። ቅርብ ምስራቅ አገሮች ሁሉ ወዳጅ መሆን የማንችለው እነሱ ጥለኞች ስለሆኑ ያንዱ ወዳጅ ስትሆን የሌላው ጠላት ትሆናለው።

መሆን ያለበት ትቅማቸው ከአገራችን ትቅም ጋር የሚመሳሰል ጋር ወዳጅ መሆን፣ ከማይመሳሰሉት ጋር ኒውትራል ወይም ሰላም መሆን ነው።

የኢትዮጵያ ጠላት ከሆኑት ጋር ለምሳሌ ግብጽ ጋር የሱዳን ጄኒራሎች ጋር ሞት ቀረሽ ትግል ማድረግ ነው። ዲፕሎማሲ የጥቅምና የጉልበት ጨዋታ ስለሆነ ።

የቀይ ባህር ማለፊያ ትልቅ የጂኦሚሊታሪ በር ቢሆንም አለም ከፔትሮሊየም ነዳጅነት እየተላቀቀ ስለሆነ ወደፊት ኮሪደሩ ያለው ዋጋ ሚሊታሪ ነው የሚሆነው ።

አፍሪካ ግን የዚህ ሴንቸሪ ኢኮኖሚ ሞተር ስለምትሆን እጅግ እጅግ ግዙፍ ያለም ትግል የሚካሄደው ባፍሪካ ላይ ነው። ኢትዮጵያ ሁለተኛ ታላቅ አገር ስለሆነው የዚህ ሞተር መሪ ነው የምትሆነው ። ናይጄሪያ ምራብ ኢትዮጵያ ምስራቅ አፍሪካን ይመራሉ ።

ዴሞክራሲና የሰው መብት ምዕራቦች ስለፈለጉት ሳይሆን ለራሳችን ስንል ዘመናዊ ዴሞክራሲ መሆን አለብን ።

የጎሳ ፖለቲካ ካንሰር ነው፣ ኢትዮጵያ ከጎሳ ቀውስ ሳትወጣ እንኳንስ ታላቅ አገር ትንሽ አገርም መሆን አትችልም ።

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 19 Feb 2021, 06:58
by Horus

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 19 Feb 2021, 11:36
by Horus
የአትዮ ኤርትራ ወታወራዊ ጥምረት ቁጥር አንድ እርምጃ ነው
https://www.youtucbe.com/watch?v=XHP8UPPfkSs

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 19 Feb 2021, 11:50
by Horus

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 19 Feb 2021, 20:42
by Horus
ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ሴራ ግዙፍ ዋጋ እንዲያስከፍላት የምናደርገው እንዴት ነው? ይህ ነው ትልቁ ብሄራዊ ጥያቄያችን ??

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 20 Feb 2021, 07:43
by Sabur

Aurorae:

I am sure it is a slip on your side to state the following:

"Horus,
Great analysis. You should join some kind of Ethiopia think tank for foreign policy"

Horus is a weak dergue apologist with an infantile old guard hope of Greater Ethiopia which includes Eritrea. She still moans and groans for the Mengistu's Era of "ተነሳ ተራመጅ ክንድህን ኣንሳ" against Eritrea's Independence. Deep down her feelings never changed.

Horus, like the TPLF Junta, is weak and sycophant who does not believe in self worth and self-sufficiency. She crumbles like house of cards under pressure when things get tough.

She gets excited and jumps up when news like "Ethiopia and Israel Agree in The Field of Intelligence" surfaces, and she will get depressed if she reads news about "Egypt and Israel Economical and Political Relations".

You see; No self worth !

She pımps for political and economical expediency the easy way. She believes in other countries help to solve Ethiopia's Problems. Basically she is a pımp.

On the issues of Ethio-Egypt and the Nile GERD dam, I have to agree with the dictator Isayas on finding a solution on detailed technical matters; such as "Will the water used for hydroelectric power affect the flow of the Nile ?" and other things. No need for other countries to mediate which complicate the matter for their own benefits. Delegation is not required.

If all parties are genuine in finding a lasting win-win a solution, the issue can be solved by technical matters by themselves without involving other parties.

There is this saying "If you do not want issues to get resolved, delegate them".

Aurorae Borealis wrote:
19 Feb 2021, 01:28
Horus,

Great analysis. You should join some kind of Ethiopia think tank for foreign policy. However, you can not be a friend to everyone. It is not possible. Becoming independent is perhaps the best way to go. How can you be a friend to Kenya and Somalia at the same time ? Iran vs. Saudi Arabia, etc.... I think Ethiopia should find a way to make peace with all of its neighbors. Ethiopia needs to make great relationship with the Middle Eastern countries. The Middle Eastern issues , the owners of the corridor in the Red Sea is far more relevant than the AU unity affairs in which Ethiopia seems to bombard its foreign relations of the past. If Ethiopia wants good relations with the West in general, human rights need to be intact. The war with TPLF has tarnished a lot of that image. Abbiy can not afford to play Mengistu. Ethiopia needs to strive to become a very democratic country. It would be nice if Ethiopia preserves federalism and negotiate Ethnic politics. You throw away federalism, you invite war. But, I can understand minimizing the ethnic nature of politics. Remember, first and for most is human right. Avoid dictatorship, otherwise, Ethiopia will be no more.

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 23 Feb 2021, 15:25
by Horus
ይህን ሃረግ ስጀምር ኢትዮጵያ ከቱርክና ህንድ ጋር ጥብቅ ዝምድና ማድረግ አለባት ብዬ ነበር ። ይሀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራችን ቱርክና ህንድ ሄደው የፖለቲካም፣ የኢኮኖሚ ሌላም ሌላም ዲፕሎማሲ አድረገው ተመለሱ ። ይህ ቅንቅ ነገር ነው። ልክ ከላይ እንዳልኩት ነው ። የውጭ ጉዳያችን ከጎረቤት አገሮች ፣ ከሪጅናል ሃይሎች፣ ከሱፐር ሃይሎች ጋር እንደ አስፈላጊነቱ ማሰናሰን ነው ያለብን!!

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 23 Feb 2021, 16:11
by Roha
ወንድም ሆረስ፥
ካቀረብከው የኢትዮጵያና የቀጠናው በሳል የፖለቲካ ትንታኔና ዘገባ: በእጅጉ እስማማበታለሁልኝ። ስለዚሁ ብዙ የሚጨምርበት ባይኖርም፡ የኔን ኣስተያየት ግዜ ባገኘሁ ቁጥር እምለስበታለሁኝ።
ከሁሉም የሚገርመኝ ግን፡ የፖለቲካው ጥልቀትና መረጃህን ብቻ ሳይሆን፡ በኢትዮጵያውነት ያለህ የማያወላውል ጽናትና ባንተ ማንነት ያለብህ ኩራት ነው። ለዚህም ነው፤ እዚህ ስለ ጉራጌ ማህረሰብ ስነጥበብ እና ስርዓት ነክ ጉዳዮች በጥሞና እምከታተለው።
ለምሳሌ እኛ ከሁሉም ጋር ጓደኛ መሆን ሳይሆን: የሁሉም ተጫዋች ጥቅም ምን እንደ ሆነ አውቀን በዚያ መሰረት መጫወት መቻል አለብን
ቅርብ ምስራቅ አገሮች ሁሉ ወዳጅ መሆን የማንችለው እነሱ ጥለኞች ስለሆኑ ያንዱ ወዳጅ ስትሆን የሌላው ጠላት ትሆናለው

መሆን ያለበት: ትቅማቸው ከአገራችን ትቅም ጋር የሚመሳሰል ጋር ወዳጅ መሆን፣ ከማይመሳሰሉት ጋር ኒውትራል ወይም ሰላም መሆን ነው።
የኢትዮጵያ ጠላት ከሆኑት ጋር ለምሳሌ ግብጽ ጋር የሱዳን ጄኒራሎች ጋር ሞት ቀረሽ ትግል ማድረግ ነው። ዲፕሎማሲ የጥቅምና የጉልበት ጨዋታ ስለሆነ ።

አፍሪካ ግን የዚህ ሴንቸሪ ኢኮኖሚ ሞተር ስለምትሆን እጅግ እጅግ ግዙፍ ያለም ትግል የሚካሄደው ባፍሪካ ላይ ነው። ኢትዮጵያ ሁለተኛ ታላቅ አገር ስለሆነው የዚህ ሞተር መሪ ነው የምትሆነው ። ናይጄሪያ መራብ ኢትዮጵያ ምስራቅ አፍሪካን ይመራሉ ።
ዴሞክራሲና የሰው መብት ምዕራቦች ስለፈለጉት ሳይሆን ለራሳችን ስንል ዘመናዊ ዴሞክራሲ መሆን አለብን ።

የጎሳ ፖለቲካ ካንሰር ነው፣ ኢትዮጵያ ከጎዳ ቀውስ ሳትወጣ እንኳንስ ታላቅ አገር ትንሽ አገርም መሆን አትችልም ።

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 23 Feb 2021, 21:02
by Horus
ሮሃ
ሃረጉን ስጀምር አውሮጃን የተውኩት ባኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ላይ ተጽዕኖ የላቸውም ብዬ አይደለም፤ ግ ን ያውሮጃ ህበትም ሆነ ግለሰብ አገሮች ያፍሪካ ቀንድን የሚያዩት የስደተኞች መፍለቂያ ቦታ አድረገው ነው። ያው ወይ ንግድ ወይ በስደተኛ እንወረራለን የሚል ሞቲቭ ነው ሚገፋቸው። አሁን በትግሬ ጉዳይ ገብተው የሚንጫጩት ለዚያ ነው። እስከ ተወሰነ ድረስ ያፍሪካ ቀንድ በወደቁ አገሮች ከተሞላ ያለም ቴረሪስቶች ምሽግ እንዳይሆንም ይፈራሉ ።

ከዚያ ባለፈ ኢትዮጵያ ተመጽዋች እንጅ ታላቅ ሃያል አገር እንድሆን፣ አንድነቷ እንዲረጋገጥ አየፈልጉም ። የሰሜን አውሮጃ ትናንሽ አገሮች ዋና የጎሳ ፖለቲካ ደጋፊዎች ናቸው። እኛ ያጣነው ውስጣዊ አንድነት ብቻ ነው ። ለዚያ ደሞ ተጠያቂዎቹ የትግሬና ኦሮሞ ልሂቃን ናቸው ።

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 25 Feb 2021, 04:42
by Horus

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 01 Mar 2021, 23:01
by Horus
በኦባማ ዘመን ከዎያኔ ጋር ሲሞዳሞዱ የነበሩት ያሜሪካ አስተዳደር ጥቁሮች፣ ነጮች፣ ይሁዲዎች በሙሉ ከባይደን ጋር ተመልሰው ያው የኦባማ ዘመን ፖሊሲን እየዘፈኑ ነው!!

ግን ማወቅ ያለባቸው የዛኔ ኢትዮጵያ ዛሬ የለችም !! የኢትዮጵያ ሃይል ሚዛን ሺፍት አድርጓል። የዛሬ ኢትዮጵያ ይበልጥ አንድነትና ጥንካሬ አላት!! ስለዚህ እነ ሱዛን ራይስና ብሊከን በግድ ከኢትዮጵያ ጋር መተባበር እንጂ የምኒክ አገር እንዲያ በቀላሉ የነጭ ታዛዥ እንዳይደለን ይወቁት !!

ኢትዮጵያዊያን በአድዋ መንፈስ የውስጥም የውጭም ጠላት ለመመከት አንድ መሆን ግዴታችን ነው !!

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 02 Mar 2021, 01:34
by Horus
Remember, America sided with Fascism against Ethiopia at the League of Nations and ever since USA holds more or less same line of diplomacy regarding Ethiopia. Today, as we speak, instead of sending us a word of congratulation on most holy of holidays, they use same African American idiotic voices to attack and disrupt Ethiopia trying to interfere into our independence.

Tigray is an Ethiopian internal matter !!! US stop meddling into out affairs !!!

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 03 Mar 2021, 06:23
by Horus

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 04 Mar 2021, 16:22
by Horus
ሰላማዊ ሰልፍ አሜሪካ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓም በግድ መደረግ አለበት ። በዉሸት ክስ የጀመሩት እነሱ ናቸው !

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 05 Mar 2021, 00:12
by Horus
ልክ እንዳልኩት ሩሲያ ዛሬ ስራዋን ሰራች ሴኩሪቲ ካውንስል ውስጥ።

ትግሬ ለማንም እስትራተጂክ ዋጋ ያለው ቦታ አይደለም ።

ኢትዮጵያና ኤርትራ ሃያል የሆነ የጦር አንድነት መፍጠር ብቻ ነው ።

ሱዳን የግብጽ አሽከር ሆና የኢትዮጵያ ጠላት ከሆነች 4 ቦታ እንድተከፋፈል ማድረግ ነው እንደ ሱማሌ ማለት ነው።

አሜሪካ ባፍሪካ ቀንዳና በቀይ ባህር አለቃ መሆን ከፈለገ ከታላቋ ኢትዮጵያ ጋር መሻረክ ይኖርበታል።

ኤርትራን በሪሶርስ ደግፎ ቀይ ባህርን አላስነካ ማለት አለባት ።

በቃ ባፍሪካ ቀንድ የምንኖር እኛ ነው። ወሳኞቹ እኛ ነው !!

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 05 Mar 2021, 00:52
by Horus
አሁን ከላይ ያልኩትን መልሳችሁ አንብቡት !

ያፍሪካ ቀንድ ላይ አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ቻይና ሙሉ ፉክክር ያደርጋሉ !

ቀጥሎ ህንድ፣ ግብጽ፣ ቱርክ፣ ኢራንም፣ እነሳውዲም ውድድር ይገባሉ ።

ኢትዮጵያ በጥበብ ይህን ማስተናገድ ብቻ ነው ያለባት ።

በዛሬ እለት አሜሪካ ኢትዮጵያን መክሰሱ የወደቀው ለዚህ ነው !!

Re: ኢትዮጵያ የአለም ጂኦፖለቲካዊ ጦርነት ማዕከል ነች፤ ሕዝባችን ባንድነት የሚነሳው እንዴት ነው?

Posted: 05 Mar 2021, 23:08
by Horus